ፈልግ

በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሰዎች የሚያሰሙትን እሮሮ እናዳምጥ

ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚዳረጉ፣ በዚህ አደጋ ላይ የሚወድቁ በርካታ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስቃዩ በስቶባቸው የሚያሰሙትን ጩሄት ከማዳመጥ ችላ አንበል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሰኞ ሐምሌ 23/2010 የጸረ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀን በማመልከት መልዕክት አስተላለፉ

በተባበሩት መንግሥታት አስተባባሪነት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ. ም. የተከበረውን ጸረ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክታቸው፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በዓለማችን በርካታ ሰዎችን ለባርነት፣ ሴቶችንና ሕጻናትን ለጉልበት ብዝበዛ እና ለጾታ ጥቃት፣ ለሰውነት ክፍል ሽያጭ ማደግ ምክንያት እንደሆነ ገልጸው፣ በሮም ከተማም ሳይቀር በርካታ ወጣቶችን ለልመናና ለወንጀል እንደዳረገ አስረድተዋል። በመሆኑም ይህን አሳፋሪ እና ኢፍትሃዊ ተግባር መዋጋት የሁሉም ማሕበረሰብ ድርሻ እንደሆነ አሳስበዋል። ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚዳረጉ፣ በዚህ አደጋ ላይ የሚወድቁ በርካታ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስቃዩ በስቶባቸው የሚያሰሙትን ጩሄት ከማዳመጥ ችላ አንበል። እነዚህ ሰዎች ሰብዓዊ ፍጡር እንጂ ዕቃ አይደሉምና እንደ ስብዕናቸው ክብር እና እንክብካቤ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ከዚህ ቀጥለውም፣ መንፈሳዊ ጉዞን በማድረግ ከኢጣሊያ የተለያዩ ከተሞች እና ከብራዚልም ሳይቀር የመጡትን ምዕመናንን፣ ከኢጣሊያ ከተማ ከሆነችው ከፓዶቫ እና ከቤተ ልሔም ለመጡት የወጣት ማሕበራት አባላት በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበው፣ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት ምዕመናን በሙሉ በጸሎታቸው እንዲያስታውሷቸው አደራ ብለዋል።    

29 July 2018, 10:21