ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት ከሚሰጡ ከ70ሺ ወጣቶች ጋር በቫቲካን ተገናኙ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ባልንጀሮቻችሁን አገልግሉ፣ ቅድስናን በብርታት ፈለጉ” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን ቀደም ሲል ያስነበብናችሁን  የተናገሩት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከ19 ሀገራት የተውጣጡ ከ70 ሺ በላይ የሚሆኑ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ከ13-23 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ጋር በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደ ነበረ  ለቫቲካን ሬዲዮ ከደርሰው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኋይሌጊዮርጊስ- ቫቲካን

እነዚህ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ታዳጊ ወጣቶች ማኅበር በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም በቫቲካን የዳረጉት መንፈሳዊ ጉብኝት ማኅበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ ወደ ቫቲካን የተደርገው 12ኛ መንፈሳዊ ጉብኚት እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በነበራቸው ቆይታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት ለቅዱስነታቸው 5 ጥያቄዎችን ማቅረባቸው እና ቅዱስነታቸውም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠታቸውን ከቫቲካን ሬዲዮ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት (በሐምሌ 24/2010 ዓ.ም) በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት ከሚሰጡ ወጣቶች ጋር በተገናኙበት ወቅት ያደርጉትን የመግቢያ ንግግር በቅድሚያ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

ውድ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የምትሰጡ ታዳጊዎች ወጣቶች

በቀለማት ያጌጡ ሰንደቃላማዎችን ይዛችሁ እንዲህ በጣም ብዙ ሁናችሁ እዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘታችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። የዚህ የእናንተ መንፈሳዊ ንግድት ምልክት የሆነውን አርማ ስለሰጣችሁኝም አመሰግናለሁ። እኔም ከእናተ ጋር በመሆን መንፈሳዊ ንግደት እያደርኩኝ እገኛለሁ። ሁላችሁም ከተለያዩ ሀገሮች ተውጣጣችሁ የመጣችሁ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ሁላችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አንድ ሆነናል። ሰላማችን ከሆነው ከእርሱ ጋር በጋር በመጓዝ ላይ እንገኛለን። እናንተን በመወከል እዚህ ተገኝተው የሰላምታ ንግግር ያደርጉትን የዚህ ማኅበር ፕሬዚዳን የሆኑትን አቡነ ነሜትን ለማመስገን እወዳለሁ። አሁን ከእናንተ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ውይይት ለማድረግ ያስችለኝ ዘንድ መድረኩን ለእናንተ እተዋለሁ።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የመግቢያ ንግግር

በወቅቱ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት የሚሰጡ ታዳጊዎች ወጣቶች ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያቀረቡላቸውን አምስት ጥያቄዎችን እና ቅዱስነታቸውም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ተገቢ ምላሽ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን። ተከታተሉን።

1.     የመጀመሪያው ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን እንደ አንድ በስርዓተ አምልኮ ወቅት የመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልጋይ እና እንደ አንድ አማኝ ሰው በመሆን በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት እርስ በእርሳችን ሰላምታ እንደ ምንሰጣጥ ይታወቃል። ይህንን ሰላም ከቤተክርስትያኖቻችን ግድግዳዎች ባሻገር በወሰድ በቤተሰቦቻችን፣ በሀገሮቻችን እና በዓለማችን ውስጥ ይህ ሰላም እንዲሰራጭ እንዴት አሰተዋጾ ማድረግ እንችላለን?

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልስ

አመሰግናለሁ! ሰላምን እና መስዋዕተ ቅዳሴን በአንድነት በማቀናጀት ጥያቄውን በተገቢው መንገድ አስቀምጠሃል። ሰላምታ ከመለዋወጣችን በፊት ጌታ ሰላሙን እና አንድነቱን ለቤተክርስትያን ማኅበርሰብ እንዲሰጥ እናማጸነዋለን። ሰላም ስጦታ ነው፣ እኛን የቀይረናል፣ ሰለዚህ የኢየሱስ አንድ አካል በመሆናችን የተነሳ የእርሱን ስሜቶች እንጋራለን፣ እርሱ እንደ ምያስበው እናስባለን፣ እርሱ እንደ ሚወድ እኛም እንወዳለን። መስዋዕተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኋላ “በሰላም ሂዱ!” በሚለው ቃል ተሸኝተን ወደ እየቤቶቻችን እንሄዳለን። ለሠላማዊ ትስስር ያለን ቁርጥ ሐሳብ በእውነት የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት መሆናችንን የሚያሳይ እውነተኛ ማረጋገጫ ነው። ሰላምን ማረጋገጥ የሚጀመረው ከጥቃቅን ነገሮች በመነሳት ነው። ለምሳሌ ያህል . . . በቤታችን ከአንድ ሰው ጋር ከተጨቃጨቅን በኋላ በጣም ተናድጄ ራሴን እጎዳለሁ ወይ? ወይስ ወደ ኋላ ተመልሼ ይቅርታን ለመጠየቅ እሞክራለሁ? በእዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ “ኢየሱስ የእኔ ቦታ ቢሆን ምን ያደርግ ነበር?” ብዬ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ነኝ ወይ? ይህንን በእውነቱ ተግባራዊ ካደረግን እና በተግባር ከገለጽን የክርስቶስ ሰላም እለታዊ በሆነ ሕይወታችን ውስጥ እንዲሰፍን ማድረግ እንችላለን።

የመጀመሪያ ጥያቄ እና የቅዱስነታቸው መልስ

2. ሁለተኛ ጥያቄ

ቅዱስ አባታች እኛ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልጋዮች የሆንን ታዳጊ ወጣቶች ጌታን በመሠዊያው ዙሪያ እናገለግላለን፣ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ደግሞ እናሰላስለዋለን። የማርያምን ምሳሌ እና አርዓያ በመከተል መንፈሳዊ የሆነ አስተንትኖ በማድረግ፣ እንዴት ነው ታዲያ ኢየሱስ በሕይወታችን ከእኛ የሚፈልገውን ነገር ለይተን ለማወቅ የምንችለው?

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልስ

በትክክለኛው መንገድ ካየነው በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልጋዮች የሆናችሁ ታዳጊ ወጣቶች እንደ መሆናችሁ መጠን እናንተም የማርታ እና የማርያም ልምድ ወይም ተመክሮ ተካፋዮች ናችሁ። በስርዓተ አመልኮ ሰነ-ስረዓት ወቅት ከምትሰጡት አገልግሎት ባሻገር በቁምስና ሕይወት ውስጥ ይበልጡኑ ተሳታፊ በመሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጌታ ፊት በዝምታ በመቀመጥ እና የእርሱን በእኛ መካከል መኖር ልናጣጥም ይገባል። በዚህ እንቅስቃሴ እና አስተንትኖ አማካይነት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን እቅድ ለመገንዘብ እንችላለን። እግዚአብሔር የሰጠንን ስጦዎችና ፍላጎቶች. . . እነርሱን እንዴት ማዳበር እንደ ምንችል እንመለከታለን። ከሁሉም በላይ እራሳችንን በትህትና በእግዚአብሔር ፊት ካሉን መልካም ከሚባሉ በሐሪይዎቻች እና ከውስንነታችን ጋር ለእርሱ በትህትና በማቅረብ እርሱን እና ጎረቤቶቻችንን እንዴት በተገቢው ሁኔታ ማገልገል እንደ ምንችል ልንጠይቀው ይገባል። “እግዚኣብሔርን እንዴት ማገልገል እችላለሁ?” በሚል አስተሳሰብ የተነሳ የግራ መጋባት መንፈስ ካደረብን የእርሱን የእግዚኣብሔርን ምክር እና ርዳታ ከመጠየቅ መባዘን የለብንም፣ ምክንያቱም በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የእኛን ርዳታ ይሻሉና። ይህንን አስታውሱ! እራሳችሁን ለሌሎች በምትሰጡበት መጠን የበለጠ በዚያው ልክ በሕይወታችሁ እርካታ እና እውነተኛ ደስታ ታገኛላችሁ!

ሁለተኛው ጥያቄ እና የቅዱስነታቸው መልስ

3. ሦስተኛ ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልጋዮች እንደ መሆናችን መጠን በእኛ የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች መካከል በመስዋዕተ ቅዳሴ ወይም በቁምስና ሕይወት ውስጥ ለመሳተፍ የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ስንመለከት በጣም እናዝናለን። በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ቤተክርስትያን ብዙ ወጣቶችን እያጣች ትገኛለች። እኛ እና ማኅበረሰባችን እንዴት ነው እነዚህን ሰዎች መገናኘት የምንችለው እና ወደ ክርስቶስ እና ወደ ቤተክርስትያናችን መልሰን ልናመጣቸው የምንችለው እንዴት ነው?

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልስ

አሁንም ወጣት እንደመሆናችሁ ሌሎችን ወደ ኢየሱስ የመሳብ ችሎታ ወይም አቅሙ አላችሁ። ይህ ሊረገገጥ የሚችለው በቅድሚያ እናንተ ለእርሱ (ለክርስቶስ) ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ስሲኖራችሁ፣ እርሱን በሚገባ ስተገናኙ፣ እርሱን በግል ሕይወታችሁ ውስጥ ጠንቅቃችሁ ስታውቁ፣ በእርሱ “ለመሸነፈ” ራሳችሁን ስታዘጋጁ ይህ ሁሉ ሊረጋገጥ ይችላል። ስለዚህ እዚህ ጋር እኔ ልንግራችሁ የምፈልገው ነገር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በተቻላችሁ አቅም ለማወቅ እና በይበልጥ እርሱን ለመውደድ ሞክሩ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በጸሎት፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ፣ ቅዱስ ወንጌል በማንበብ፣ ታማኝ በመሆን እና ድኾችን በማገልገል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመገናኘት ሞክሩ። ከጓደኞቻቸው ጋር ለመገናኘት ሞክሩ፣ በዙሪያችሁ በሚገኙ ሰዎች ሁሉ ላይ የክርስቶስ ብርሃን እንዲበራ ልባችሁን በቅድሚያ ከከርስቶስ ጋር አስተሳስሩ። ብዙ ቃላትን መናገር አይገባም፣ ዋናው እና አስፈላጊው ነገር ሊሆን የሚገባው ተግባራችሁ፣ ቅርበታችሁ፣ እና ለማገልገል ያላችሁ ፍላጎት ሊሆን የገባል። ወጣቶች እና እያንዳንዱ ሰው ለሚያደረግለት ነገር ካሳ እንዲከፈላቸው የማይሹ መልካም አብነት ማሳየተ የሚችሉ ጓደኞች ያስፈልጉዋችዋል። በዚህ መንገድ ማኅበርሰቡ አማኞች ምን ያህል ውብ እንደሆኑ እንዲመለከቱም ይረዳል ምክንያቱም እግዚአብሔር በመካከላቸው ስለሆነ ነው። በዚህ ምክንያት የቤተክርስትያን ቤተሰብ አካል መሆን ምን ያህል አስደሳች እንደ ሆነ ጭምር ይመለከታሉ።

ሦስተኛው ጥያቄ እና የቅዱስነታቸው መልስ

4. አራተኛ ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰዎች እግዚኣብሔር፣ ሐይማኖት፣ ቤተክርስትያን በሕይወታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች አይደለም ብለው የሚናገሩ ብዙ ሰዎች አሉ። አንድ ሰው የካቶሊክ እምነት ትክክለኛ ነው ብሎ የሚወስነው ለምንድነው? በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድነው? ለእርሶ እምነት ለምንድነው በጣም አስፈላጊ ነገር የሚሆነው?

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልስ

እምነት በጣም አሰፈላጊ ነገር ነው! ሕይወትን ይሰጣል። እምነት እንደምንተነፍሰው አየር በጣም አስፈላጊ ነው  ለማለት እወዳለሁ። በእያንዳንዱ እስትንፋሳችን አየር እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ አስበነው አናውቅም፣ ነገር ግን አየር የሌለበት ቦታ ከሆንን ወይንም ደግሞ ንጹህ ያልሆነ የተበከለ አየር ስያጋጥመን አውን በዚህን ጊዜ በቀጥታ አየር ምነኛ አስፈላጊ እንደ ሆነ እንገነዘባለን። እመነት የሕይወትን ትርጉም ጠንቅቀን እንድናውቅ ይረዳናል፣ ለዘለዓለም የሚወደን አንድ አካል እናዳለ እንረዳለን፣ ይህ አንድ አካል ደግሞ እግዚኣብሔር ራሱ ነው። እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪያችን እና አዳኛችን አድርገነው ልንገነዘብ እንችላለን፣ እግዚኣብሔርን እንድንወድ እና ሕይወታችን የእርሱ ስጦታ እንደ ሆነች አድርገን እንድንቀበል ይረዳናል። እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመስረት ይፈልጋል። እኛ ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንድንመሰርት ይጋባዘናል፣ እኛም በፊናችን ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር መነሳሳት ይኖርብናል። በእግዚኣብሔር የማያምን አንድ ሰው እርሱ ወይም እርሷ ብቸኛ ልጅ እንድ አሆነ/ች አድርገው ያስባል/ታስባለች! ሁላችንም የእግዚኣብሔር ልጆች ነን! እኛ ሁላችን የተጠራነው የእግዚኣብሔር ቤተሰቦች የሚሰበሰቡባትን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የወንድማማችነት እና የእህታማማችነት ማኅበር አቅፋ የያዘችሁን ቤተክርስትያንን እንድንመሰርት ነው። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እኛ “የእግዚኣብሔ ቤተሰብ አባላት ነን” (ኤፌ. 2፡19) ይለናል። በእዚህ በቤተክርስትያን ቤተሰባዊ ግንኙነት ውስጥ ጌታ ወንድ እና ሴት ልጆቹን በምስጢራቱ እና በቃሉ ይመግባቸዋል።

አራተኛው ጥያቄ እና የቅዱስነታቸው መልስ

5. አምስተኛ ጥያቄ

ቅዱስ አባታችን እኛ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ እየሰጠን የምንገኘው አገልግሎት በጣም ጥሩ በመሆኑ የተነሳ ይህንን አገልግሎት በጣም ነው የምወደው። ጌታን እና ባልንጀሮቻችን ማገልገል እንፈልጋለን። ነገር ግን እኛ ቅዱሳን ባለመሆናችን የተነሳ ሁል ጊዜ መልካም የሆኑ ነገሮች ለማድረግ አንችልም። አገልግሎታችንን፣ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባራዊ ስራዎች በመግለጽ ጭምር ወደ ቅድስና ሕይወት የሚወስደውን መንገድ ለመያዝ ያስችለን ዘንድ አገልግሎታችንን ተግባራዊ በሆነ መልኩ እንዴት መተርጎም እንችላለን?

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልስ

መልካም ነገር ለመሥራት እና ቅዱሳን ለመሆን ከፍተኛ የሆነ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። በእዚህ ረገድ እናንተ በስረዓተ አምልኮ ወቅት በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልጋይ የሆናችሁ ሁላችሁ ይህንን መንገድ ለመከተል ቆርጣችሁ እንደ ተነሳችሁ ይታየኛል። ጌታ ኢየሱስ በቅድስና መንገድ ለመጓዝ የሚያስችሉንን ቀለል ያሉ መመሪያዎችን ሰጥቶናል፣ እነዚህ መመሪያዎች “እግዚአብሔርን እና ባልንጀራዎቻችንን መውደድ” ያስፈልጋል የሚሉ ትእዛዛትን አቅፎ የያዘ ነው። ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ወይም ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት እናድርግ፣ ስለ ሰጠን ፍቅር እርሱን በማመስገን በሁሉም ነገሮች ውስጥ እርሱን ማገልገል ይገባል። በዚህ መንገድ የእርሱን ፍቅር ለሌሎች ለማካፈል እንችላለን። “እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ” ብሎ የሰጠንን ትእዛዝ ይበልጥ ተጨባጭ በሆነ መልኩ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠን የምሕረት ተግባራት አማካይነት እኛም ይህንኑ ለሌልች መገለጽ ይኖርብናል። እነርሱን ልንፈልግ ይገባል፣ ሆኖም እነዚህ የምሕረት ሥራዎች በሁሉም ሰዎች ውስጥ ይገኛሉ። “የባልንጀሮቻችንን ፍላጎት ለማሟላት ምን ማድረግ አለብኝ?” በማለት ራሳችንን በመጠየቅ መጀመር ይኖርብናል። ምንም እንኳን ባልንጀሮቻችን የሚባሉ ሰዎች ጓደኞቻችን ወይም እንግዳዶች ወይም የባዕድ ሀገር ሰው ቢሆኑም እንኳን ልዩነት አይኖረውም። እመኑኝ ይህን በማድረጋችሁ የክርስቶስን ፍቅር በመኖር ዓለምን የምቀይሩ እውነተኛ ሰዎች ልትሆኑ ትችላላችሁ።

ስለነበረን ቆይታ በጣም አመስግናችኋለሁ!

አምስተኛው ጥያቄ እና የቅዱስነታቸው መልስ

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በመንበረ ታቦት ዙሪያ አገልግሎት ከሚሰጡ ከ70ሺ ወጣቶች ጋር በቫቲካን ተገናኙ
01 July 2018, 10:56