ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “መንፈስ ቅዱስ አብያተ ክርስቲያናትን አንድ ያደጋል”

“ተከፋፍለው የሚገኙ አብያተክርስቲያናትን መንፈስ ቅዱስ አንድ ያደርጋቸዋል

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “መንፈስ ቅዱስ አብያተክርስቲያናትን አንድ ያደርጋቸዋል!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 27/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቀሌሜንጦስ የስብሰባ አዳራሽ ከሉቴራን ቤተክርስቲያን ተወካዮች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን አሁኑም ቢሆን “ተከፋፍለው የሚገኙ አብያተክርስቲያናትን መንፈስ ቅዱስ አንድ ያደርጋቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ከሉቴራን ቤተክርስቲያን ተወካዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ስላለው አንዳንድ ገጽታዎች፣ ስለ ቤተክርስቲያን፣ ስለቅዱስ ቁርባን እና ስለ ቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት አንስተው መወያየታቸው የገለጸ ሲሆን ትክክለኛ መንገድ የተካሄደ እና ገንቢ የሆኑ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት ወይይት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን የሐይማኖ ሕብረት ለመፍጠር የሚደርገው እንቅስቃሴ በተወሰኑ ከፍተኛ ቦታ ባላቸው ሰዎች መካከል ብቻ ውይይት ማድረግ ማለት ሳይሆን  ነገር ግን በተቻለ መጠን በእምነት ጠንካራ በሆኑ ብዙ ወንድሞችን እና እህቶችን ባሳተፈ መልኩ ማድረግ ማለት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በቀጣይነት በሉቴራን እና በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል እይተደረገ የሚገኘው ውይይት ገንቢ፣ በመግባባት ላይ የተመሰረተ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ የሚገኝ ውይይት እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ ፍጥነት እና በእዚህ አግባብ ከቀጠለ ደግሞ ለወደፊቱ መልካም ፍሬን ማስገኘቱ እንደ ማይቀር ከወዲሁ ተስፋ ተጥሎበታል። እንደ ክርስቲያኖች፣ እንደ ካቶሊኮች እና እንደ ሉተራኖች በአጠቃላይ እኛ ሁላችን በቀዳሚነት ማድረግ የሚጠበቅብን “እርስ በእርሳችን አጥብቀን መዋደድ፣ በእውነተኛ ልብ እርስ በእርሳችን መፈላለግ መሆን እንዳለበት በመጥቀስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከእዚያም ባሻገር በመሄድ የደም ትስስር ወይም ሕብረት በመፍጠር፣ በችግር ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች እና እንዲሁም በስደት ላይ ያሉትን ሰዎች ሳይቀር በተቻለን አቅም በተቀናጀ መልኩ ልንረዳቸው እና ልናግዛቸው የገባል ብለው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል . . .”በዛሬው ጊዜ በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት ብቻ በከፍተኛ ጭቆና ስር በሚገኙ ወንድሞች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ እኛ ተጨባጭ እና ግልጽ የሆነ አንድነት ላይ እንድንደርስ ጥሪ የሚቀርብልን አጋጣሚ ነው” ማለታቸውም ተገልጹዋል።

በተለይም ኅብረትን ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጉዞ በተመለከተ ብዙ ሊባሉ የሚችሉ የተመዘገቡ ውጤቶች እና ግቦች መመዝገባቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . . “ለአለፉት 500 አመታት ያህል በተደጋጋሚ በተደርጉ ግጭቶች፣ በጣም አሳዛኝ የሚባሉ ክስተቶች ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም ለአምላካችን ምስጋና ይግባውና ይህ ጉዳይ ተወግዶ በምትኩ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ደግሞ ወደ ሕብረት ጎዳና የምናደርገው ጉዞ እያደገ መምጣቱን ለማየት ችለናል”  ማለታቸውም ተገልጹዋል።

ውይይት የተደረገባቸው መንገዶች በጣም አስፈላጊ እና መልካም የሆኑ ፍሬዎችን እንድንሰበስብ አስችሎናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .“ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይግባውና ተገናኝተን በወንድማማችነት መንፈስ ለመወያየት በመብቃታችን እና ስብዓዊ የሆኑ ስሌቶችን ተጠቅመን ሳይሆን በወንጌል እሴቶች ላይ በተመስረተ መልኩ ኦፊሴላዊ በሆነ መልኩ የካቶሊክ እና የሉቴራን አብያተ ክርስቲያናት የቀድሞውን ጭፍን ጥላቻዎቻችንን ማሸነፍ ችለናል” ብለዋል።

“ኅበረት የመፍጠር ስሜት በጣም አስፈላጊ እና ፍላጎታችን እንዲጨምር እያደርገ የሚገኝ ክስተት” እንደ ሆነ በግንኙነቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ይህም በጎ የሆነ ጅማሬ የመጭውን ጊዜ ሁኔታ የሚያመላክት በጎ ጎን ያለው ጅማሬ እንደ ሆነ” ጠቅሰው “የወደፊቱን ልዩነት ለማሸነፍ የሚያስችል የወደፊት ጊዜ ተስፋ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . . “ምንም ጊዜ ቢሆን ውይይታችንን በጸሎት መጀመር መዘንጋት በፍጹም የለብንም፣ ምክንያቱም ይህንን መንገድ ሊያመላክተን የሚችለው የሰው ልጆች እቅድ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው፡  እርሱ ብቻ ነው መንገዳችንን የሚከፍተው እና የሚወሰደውን እርምጃ የሚያበራው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው” ማለታቸውም ተገልጹዋል።

“ይህንን የጀመርነውን የውይይት መንፈስ አጠናክረን መቀጠል ይገባናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ጉዞ መጓዝ የሚኖርብን ፍላጎቶቻችን ብቻ በመከተል በፍጥነት ወደ ፊት መጓዝ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን ነገር ግን ወደ ፊት መጓዝ የሚገባን በትዕግስ ተሞልተን እና በእግዚኣብሔር እይታ ታግዘን ሊሆን የገባል ካሉ በኃላ ማንኛውም ዓይነት ውይይት ባለበት ቦታ ከቆመ ግን በላበት ቦታ ከቆመ ይቀራል ከእዚያ እንዲነቃነቅ እና ወደ ፊት እንዲጓዝ ማድረግ በጣም ከባድ የሆነ ተግባር ይሆናል ካሉ በኃላ “መንፈስ ቅዱስ ሆይ በእኛ ላይ ወረድ ተከፋፍለው የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናትን አንድ አድርግ” በማለት ከተማጸኑ በኃላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 

04 June 2018, 10:54