ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (ANSA)

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮ፡ “ጠንካራ በሆነው በእግዚኣብሔርፍ ኃያል መተማመናችንን እንቀጥል!”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በሰኔ 10/2010 ዓ.ም የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከመድገማቸው በፊት በዕለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ባደርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት “ጠንካራ በሆነው በእግዚኣብሔርፍ ኃያል መተማመናችንን እንቀጥል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በትላንትናው እለት ማለትም ማለትም በሰኔ 10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎ በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ከማርቆስ ወንጌል 4፡26-34 ላይ ትወስዶ በተነበበው የአዳጊው ዘር እና የሰናፍጭ ዘር ምሳሌ ላይ ትኩረቱን ባደርገው አስተንትኖ እንደ ነበረ ለመረዳት ትችሉዋል።

የዚህ ዜና አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያደርጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ማርቆስ ወንጌል 4፡26-34) ኢየሱስ ስለእግዚአብሄር መንግሥት እና የእድገቱን ጥንካሬ በተመለከተ ሁለት አጫጭር ምሳሌዎችን በመጠቀም ለሕዝቡ ይናገራል። በመጀመሪያው ምሳሌ ላይ (ማር. 4፡26-29) የእግዚኣብሔርን መንግሥት ከአንድ ምስጢራዊ በሆነ መልኩ ከምታድግ ዘር ጋር በማነጻጸር አንድ ሰው መሬት ላይ ዘር ይዘራል። ዘሪው ምንም ሳያውቅ ያ ዘር በቅሎ ያድጋል፤ በመጀመሪያ ቡቃያ፣ ቀጥሎ ዛላ፣ ከዚያም በዛላው ላይ የጐመራ ፍሬ ታስገኛለች በማለት ይናገራል። ይህ ምሳሌ የሚያስተላልፍልን መልእክት የሚሆነው ኢየሱስ በስብከቱ እና በተግባሩ አማካይነት ያወጀው እግዚኣብሔርን መግሥት ልክ እንደ ዘር በዓለም ውስጥ በመዘዋወር በራሱ ኃይል እንደ ሚበቅል እና እንደ ሚያድግ፣ በሰውኛ አመለካከት ሊገለጽ በማይችል መልኩ በራሱ እንደ ሚበቅል የሚያመለክት መልእክት ያስተላልፍልናል። በታሪክ ውስጥ የእድገቱ እና የእድገቱ ሂደት በሰው ስራ ላይ ብዙ የማይመረኮዝ፣ ነገር ግን በተቃራኒው በእግዚኣብሔር ኃይል እና መልካምነት ላይ ብቻ የተመረኮዘ እንደ ሆነ፣ በእግዚአብሔር ሕዝብ ውስጥ ክርስቲያናዊ ሕይወትን የሚመራ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑን ያመለክታል። አንዳንድ ጊዜ በእዚህ ታሪክ ውስጥ የተጠቀሱት ተግዳሮቶችን እና ተዋናዮች ሰማያዊ አበታችን ለልጆቹ ሁሉ ያለውን የወንድማማችነት፣ የፍትህ እና የሰላም እቅድ በተቃራኒ አቅጣጫ በመሄድ ይመስላል። ነገር ግን እኛ በእነዚህን ጊዜያት ለመፈተን፣ ተስፋ ማድረግን እና በመጠባበቅ ላይ እንድንቆይ ተጠርተናል። በእርግጥ ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም የእግዚአብሔር መንግሥት በዓለም ውስጥ ምስጢራዊ በሆነ መልኩ እያደገች በሚያስደንቅ መንገድ ትናንሽ በምትባል ዘር ውስጥ በተደበቀ ኃይል አማካይነት ድል እየተቀናጀች ትገኛላች። አንዳንድ ጊዜ በግል ተግዳሮቶች እና በማሕበራዊ ጥፋቶች ምክንያት ተስፋችንን የሚጨለመ ቢመስልም ነገር ግን ኃይለኛ በሆነው የእግዚአብሔር ተግባር ላይ እምነት ሊኖረን ይገባል። በእዚህ ምክንያት በጨለማ እና በችግሮች ውስጥ በምንገባበት ወቅቶች ሁሉ እኛ መርበትበት አይኖርብንም፣ በእግዚኣብሔር በመተማመን በእርሱ ላይ ጸንተን ልንኖር ይገባ፣ ሁልጊዜ በሚያድነው በእግዚኣብሔር ተስፋ መተማመን ይኖርብናል። ይህንን ሁል ጊዜ አስታውሱ፡ እግዚኣብሔር ሁሌም ያድናንል። እርሱ አዳኝ ነውና። በሁለተኛው ምሳሌ ላይ (ማርቆስ 4፡30-32) ኢየሱስ የእግዚኣብሔርን መንግሥት ከአንድ የሰናፍጭ ዘር ጋር በንጽጽር ሲያቀርብ እናገኛለን። በምድር ላይ ከሚዘራው ዘር ሁሉ እጅግ ያነሰችውን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤ ተዘርታ ካደገች በኋላ ግን፣ ያልተጠበቀ አስገራሚ ዕድገት እንደ ምታሳይ ይናገራል። ለእኛ በእዚህ የእግዚኣብሔር አስተሳሰብ ውስጥ መግባት ወይም ይህንን መረዳት በጣም ቀላል የሆነ ነገር እና በሕይወታችን ውስጥ ይህንን እውነተ መቀበል በጣም ቀላል የሆነ ነገር አይደለም። ነገር ግን ዛሬ የእኛን እቅዶች፣ ስሌቶች፣ ትንበያዎቻችንን የሚያሸንፍ የእምነት አቋም እንዲኖረን ጌታ ያበረታታናል። እግዚአብሔር ሁሌም ያልታሰበ ነገር የሚያደርግ አምላክ ነው። ጌታ ሁሌም ያስገርመናል። በግለሰብ እና በማህበረሰብ ደረጃ ለእግዚኣብሔር የርኅራኄ እቅዶች በይበልጥ ራሳችንን እንድንከፍት የቀረበልን ግብዣ ነው። በማኅበርሰባችን ውስጥ ለሚገኙ ደካማ ለሆኑ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባን እና ጌታ ለእኛ ባሳየው በጎነት እንደ ታላቅ አጋጣሚ በመጠቀም በእርሱ ፍቅር፣ መስተንግዶ እና በሁሉም የምህረት ተግባራት ተነሳሽነት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል። የቤተክርስቲያኗ ተልዕኮ እውነተኛነት የሚረጋገጠው ስኬታማ በመሆኗ ላይ ወይም ደግሞ አስደሳች የሆነ ውጤት በማስመስገቧ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ነገር ግን በታላቅ ብርታት በእግዚኣብሔር በመተማመን እና በእርሱ በመታቀፍ ወደ ፊት በመጓዟ ላይ የተመሰረተ ነው። እርሱን በመምሰከር እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ ፊት መጓዝ። የእርሱ ትንሽ እና ደካማ መሳሪያ መሆናችንን ከግንዛቤ በማስገባት ራሳችን በእግዚኣብሔር እጅ ውስጥ በማድረግ እና በእርሱ ጸጋ በመተማመን ታላላቅ የሚባሉ ተግባራትን በመፈጸም የእርሱ መንግሥት መገለጫ የሆኑትን “ፍትህ፣ ሰላም፣ እና በመንፈስ ቅዱስ አማክይነት የሚገኘውን ደስታ” ለማስፋፋት እንችላለን። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትሁት እና ጠንቃቆች በመሆን ከእምነታችንን ጋር በመተጋገዝ የእግዚኣብሔር መንግሥ በልባችን እና በታሪክ ውስጥ እንድታድግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ እመቤታችን ትርዳን። ”

17 June 2018, 11:54