ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ቤተሰብ በሕይወት ቤተ መቅደስ ውስጥ የእግዚኣብሔር ሥራ ተባባሪ ነው
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ፡ ቤተሰብ በሕይወት ቤተ መቅደስ ውስጥ የእግዚኣብሔር ሥራ ተባባሪዎች ናቸው ማለታቸው ተገለጸ።
ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በሰኔ 17/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎ በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ሉቃስ ወንጌል 1፡57-66.80 ላይ ትወስዶ በተነበበው የመጥመቁ ዩሐንስ ውልደት በተመለከተ በሚተርከው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ሆነ ለመገንዘብ ተችሉዋል። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ደንብ መስረት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም እና የመጥቁ ዩሐንስ ልደቶች ብቻ የሚከበሩ ሲሆን የሌሎች ቅዱሳን ልደት በቅዱስ ዩሐንስ ልደት ውስጥ ተጠቃሎ የሚከበር እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉዋል።
ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶስ በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 17/2010 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተምስርተው ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ምከተለው እንቀርበዋለን፣ አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉ ከወዲሁ እናጋዝባዛለን።