ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የግንቦት 01/2010 ዓ.ም.  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል”

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ረቡዕ በግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ገለጹት “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ወይም ደግሞ እዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ትኩረቱን ባደረገው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በሚያዝያ 18/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ቀደም ባሉት ዝግጅቶቻችን መዘገባችን ይታወሳል። በሚያዝያ 24/2010 ዓ.ም. አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደረጉት ክፍል አራት የትምህርተ ክርስትሶስ አሰትምህሮ እንደ አገለጹት “አንድ ሰው ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ክርስቶስን መከተል በፍጹም አይችልም” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው በግንቦት 01/2010 ዓ.ም. ደግሞ አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ መሰረቱን ባደርገው የክፍል አምስት አስተምህሮ እንደ ገለጹት “ምስጢረ ጥምቀት ዳግም እንድንወለድ ያደረግናል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 01/2010 ዓ.ም.  በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!”

“በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ዛሬ የምናደርገው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቅዱስ በሆነ የእጥበት ስነ-ስረዓት ውስጥ የክርስቶስ የፋሲካ ምስጢር መልክ በመያዝ ለኃጢኣት የመሞት ምልክት ከመሆኑ ጋር እርሱን እውን በማድረግ ወደ ቅድስት ሥላሴ ሕይወት መግባትን የሚገልጽ መሆኑን በስፋት እንመለክታለን (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 1239)። ይህንን ምልክት በተመለከተ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለሮም ክርስቲያኖች “ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንድንሆን የተጠመቅን፣ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? በማለት የመጀመሪያውን ጥያቄ አቅርቦላቸው የነበረ ሲሆን በመቀጠልም “ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከእርሱ ጋር ተቀብረናል” (ሮም 6:3-4) በማለት ሲመለስላቸው እናያለን። ስለእዚህ ምስጢረ ጥምቀትን የሚሰጥበት የማጥመቂያ ስፍራ (ገንዳ) ከክርስቶስ ጋር ፋሲካን የምናከብርበት ሥፍራ ነው። “ቀድሞ የነበረን በሚያታልል ምኞት የጎደፈውን አሮጌ ሰውነታችን ይቀበራል” (ኤፌሶን 4፡22) ምክንያቱም እንደ አዲስ ፍጥረት ዳግም እንወለዳለን፣ ስለዚህ አሮጌው ነገር አልፉአል፤ እነሆ፣ አዲስ ሆነናል (2ቆሮንጦስ 5:17)። የኢየሩሳሌሙ ቅዱስ ቄርሎስ ለንዑስ ክርስቲያኖች የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን ይሰጥ በነበረበት ወቅት በምስጢረ ጥምቀት ውሃ ውስጥ ምን እንደ ሚገጥማቸው ባስተማረበት ወቅት ምስጢረ ጥምቀት ውሃ ውስጥ ስትገቡ “በዚያው ቅጽበት ትሞቱና ዳግም ትወለዳላችሁ፣ በተመሳሳይ መልኩም ከመቃብር በመውጣት እና ወደ እናታችሁ ውስጥ በመግባት ጤንነታችሁን ታረጋግጣላችሁ” በማለት ያስትምር እንደ ነበረ ይታወቃል። የአዲስ የተወለደው ሰው በኃጢአት የተበከለውን ማንነቱን በአፈር ውስጥ በመተው ከኃጢኣት የጸዳ አዲስ ሰው መሆን ይገባዋል። ከላይ የተጠቀሱት የምስጢረ ጥምቀት መስጫ ሥፍራን በተመለከተ በምሳሌያዊ አነጋገር የመቃብር ስፍራ እና የእናት ማሕጸን ተብሎ የተጠቀሱት ተምሳሌቶች የሚያመልከቱት ምስጢረ ጥምቀትን ስንቀበል የምናገኘውን ጸጋ ቀለል ባለ ሁኔታ የሚገልጹ ወይም የሚያመልክቱ ነገሮች ናቸው። የምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት አስጣጥን በተመለከተ ከተቀመጡት የቤተ ክርስቲያናችን ሕግጋቶች ውስጥ ከተጠቀሱት ሕግጋት መካከል የሚከተለውን ለመጥቀስ እወዳለሁ “እናት የሆነች ቤተክርስቲያን በምስጢረ ጥምቀት ውሃ አማካይነት በእግዚኣብሔር እስትንፋስ አማካይነት በድንግልና ያረገዘችሁውን ልጆች ትወልዳለች። ከእዚህ ምንጭ የተወለዳችሁ ሁሉ የእግዚኣብሔርን መንስግሥት ተስፋ አድርጉ” በማለት ይገልጻል። ወላጆቻችን በምድር ላይ እንድንኖር ሕይወትን እንደ ሰጡን ሁሉ ቤተክርስቲያንም በምስጢረ ጥምቀት አማካይነት ወደ ዘላለም ሕይወት ዳግም እንድንወለድ ታደርገናለች። በልጁ በክርስቶስ አማካይነት እኛም የእርሱ ልጆች እንሆናለን። እያንዳንዳችን በውኃ እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ዳግመኛ የተወለድን ሁላችን የሰማይ አባታችን በዘላለም ፍቅር በሚያስደንቅ ሁኔታ “አነተ እጅግ የምወድህ ልጄ ነህ” (ማቴ 3:17) የሚለውን ድምፁን ለእኛም ይሰጠናል። ይህ አባታዊ ድምጽ ምናልባት በጆሮዋችን ውስጥ ሊሰማን አይችል ይሆናል፣ ነገር ግን በአንድ በሚያምን ልብ ውስጥ በደንብ ይሰማል፣ በእዚህም መልኩ ይህ በፍጹም ለብቻችን ሳይተወን እስከ ሕይወታችን ፋጽሜ ድረስ ከእኛ ጋር ይሆናል። ዳግም የተወለድን የእግዚኣብሔር ልጆች ነን፣ ለዘለዓለሙ እንዲሁ ነን! በመሠረቱ ምስጢረ ጥምቀት የሚደገም ምስጢር አይደለም፣ ምክንያቱም በማይፋቅ መነፍሳዊ ምልክት ስለታተምን ነው፡ “ምስጢረ ጥምቀት የደኽንነት ፍሬዎችን እንዳያፈራ ኃጢኣት ቢያግደውም እንኳን ይህንን ምልክት ምንም ዓይነት ኃጢኣት ሊፍቀው አይችልም” (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 1272)። ንዑስ ክርስቲያን በምስጢረ ጥምቀት አማካይነት ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን የተጠመቁ ክርስቲያኖች በክርስቶስ አማካይነት “ከብዙ ወንድሞች መካከል የበኵር ልጆች እንድንሆን” (ሮሜ 8፡29) ያደርገናል። በመንፈስ ቅድስ አማካይነት ምስጢረ ትምቀት ያነጻናል፣ ይቀድሰናል ጻድቃን እንድንሆን በማድረግ ሁላችንም የክርስቶስ አንድ አካል እንድንሆን ያደርገናል። በምስጢረ ጥምቀት ስነ-ስረዓት ወቅት “ተጠማቂው የንጉሥ ካህን እና የእግዚአብሔር ህዝብ ማህበረሰብ የሚያደርግንን ቅባ ቅዱስ እንቀባለን። ካህኑ “በክርስቶስ ውስጥ እንድትገባ፣ ንጉሥ፣ ካህን፣ እና ነቢይ እንድትሆን፣ ለዘለዓለም የእርሱ አካል ሆነህ እንድትኖር እግዚኣብሔር ራሱ በእዚህ የደኽንነት ቅባ ቅዱስ አማካይነት ይቀድስሃል” በማለት ካህኑ የእያንዳንዱን ተጠማቂ ግንባር በቅባ ቅዱስ ይቀባል። የክርስቲያን የሕይወት ጥሪ የሚገኘው በእዚህ ውስጥ ነው፣ በቤተክርስቲያን አማካይነት ከክርስቶስ ጋር በሕብረት መኖር፣ በአንድ ተመሳሳይ ተልዕኮ ውስጥ በመግባት በእርሱ ተልዕኮ ውስጥ ተካፋይ መሆን፣ በእዚህ አካሄድ ወይም ሁኔታ ለዘለዓለም የሚቆዩ ፍሬዎችን በማፍራት ሂደት ውስጥ ተሳታፊ መሆን ማለት ነው። በእዚህ መነፈስ በመነሳሳት ሁሉም የእግዚኣብሔር ልጆች በክርስቶስ “የካህት፣ የንግሥና እና የነቢይነት” ተግባር እና ተልዕኮ ውስጥ ተካፍይ ይሆናሉ ማለት ነው፣ ከእነዚህ በሚመነጩ ተልዕኮዎች ውስጥ በኃላፊነት እንዲሳተፉ እና ከእነዚህ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ተግባሮች ውስጥ እንዲሳተፉ ያደርጋቸዋል። በክርስቶስ የንጉሥ ክህነት ተግባር እና በነቢይነት ተልዕኮ ውስጥ መሳተፍ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት “ራሳችንን ለእግዚኣብሔር የተግባ መስዋዕት አድርገን ማቅረብ ማለት ነው” (ሮሜ 12፡1)፣ በእምነት እና በፍቅር በመኖር ለእርሱ ምስክርነትን መስጠት ማለት ነው፣ የክርስቶስን አብነት በመከተል ራሳችንን ሌሎችን ለማገልግል ማዘጋጀት ማለት ነው ።(የማቴ. 20፡25-8, ዩሐንስ 13፡13-17).”

09 May 2018, 11:23