ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ራሳችንን ለኢየሱስ አስገዝተን መኖር ይኖርብናል!

በእዚህ በፋሲካ በዓል ስሞን የሚነበቡልን የእግዚኣብሔር ቃላት ከሙታን የተነሳው ጌታ ማኅበር አባል እንድንሆን የሚያስችሉንን የአኗኗር ዝይቤ ያመለክቱናል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ራሳችንን ለኢየሱስ አስገዝተን መኖር ይኖርብናል!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ በስድስተኛው የፋሲካ የትንሳኤ ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ስድስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በሚያዝያ 28/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙት ስብከት መሰረቱን አድጎ የነበረው “በፍቅሬ ኑሩ” በሚለውን ከዩሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15:9 በተጠቀሰው በኢየሱስ ቃል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 28/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!”

“በእዚህ በፋሲካ በዓል ስሞን የሚነበቡልን የእግዚኣብሔር ቃላት ከሙታን የተነሳው ጌታ ማኅበር አባል እንድንሆን የሚያስችሉንን የአኗኗር ዝይቤ ያመለክቱናል። ከእነዚህ ውስጥ ዛሬ በተነበበልን ቅድሱ ወንጌል ውስጥ “በፍቅሬ ኑሩ” የሚለውን ራሳችንን በኢየሱስ ውስጥ አስገዝተን መኖር እንደ ሚገባን የሚገልጸው ቃል የሚገኝበት ሲሆን ይህም ሁልጊዜም ቢሆን እኛ በኢየሱስ ፍቅር ውስጥ ሁነን መኖር እንደ ሚገባን ያመለክታል። በእግዚአብሄር የፍቅር ነበልባል ውስጥ ሆኖ መኖር፣ ውስጥ መኖር፣ ወደ ዘላቂ መኖሪያችን በምናደርገው ጉዞ ላይ ያ ፍቅር በጎዳናው ላይ እንድይጥፈ የሚረዳን ሁኔታ ይፈጥርልናል ማለት ነው። እኛም እግዚኣብሔር በኢየሱስ ውስጥ እንዳለ ከላይ የሚመጣውን መንፈስ በመቀበል፣ እና በእዚህ ፍቅር ውስጥ በመኖር ከራስ ወዳድነት እና ከሀጢያት ራሳችንን ለማላቀቅ እንድንችል ያረዳናል። ይህ ሂደት የእኛን ጥረት የሚጠይቅ ሂደት ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን የማይቻል ነገር አይደለም፣ ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ የክርስቶስ ፍቅር እንዲሁ የይስሙላ ስሜት አይደለም,፣ በፍጹም እንዲህ አይደለም፣ ነገር ግን የልብ ተጨባጭነት ያለው እሱ እንደሚፈልገው መኖር በሚያስችለን ሁኔታ ራሳችንን መገለጥ ማለት ነው እንጂ። ኢየሱስ እንዲህ ይለናል “እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ” (ዩሐንስ 15:10) ይለናል። ፍቅር በዕለት ተዕለት ኑሮ፣ ባህሪይ እና ድርጊቶች የሚገለጽ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን እንዲያው ዝም ብሎ እንደ አንድ ቅዤት ነው የሚሆነው። ዝም ብሎ በቃላት መደጋገም ብቻ የሚገለጽ ከሆነ፣ ይህ ፍቅር አይደለም። ፍቅር ተጨበጫ የሆነ እና በእየለቱ የሚገለጽ ነገር ነው። ኢየሱስ “ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” በማለት በዚህ ውስጥ በአጭሩ የተቀመጡትን ትዕዛዛት እንድንጠብቅ ይጠይቀናል። ታዲያ ከሞት የተነሳው ጌታ ለእኛ የሚሰጠን ይህንን ፍቅር እንዴት ነው ለሌለች ሰዎች ማሳየት የምንችለው? ኢየሱስ ፍቅርን በቃል ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ በሆነ መልኩ መፈጸም እንዳለበት ደጋግሞ አመልክቶናል። በመንገዴ ላይ የማገኛቸው እና ፊቱን ሁል ጊዜ ከእኔ የማይደብቀው በእሱ ታሪክ ውስጥ ገብቼ እንድመላለስ የተጠራው፣ እርሱ ከእኔ ጋር አብሮ በመኖር፣ ከራሴ ግላዊ ጥቅሞችና ደኽንነት በመውጣት እንዲሄድ የሚጠራኝ እርሱ፣ የእርሱን ቃል በሚገባ እንድሰማ የሚጠራኝ እርሱ፣ ከእርሱ ጋር አብሬ በመሆን ወደ ፊት አንድ እርምጃ እንድራመድ የሚጠራኝ እርሱ። ለእያንዳንዱ ወንድምና እህት፣ በየትኛውም ቦታ እና በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢኖር፣ ከቅርብ የቤተሰብ አባለት ጀምሮ፣ ለማኅበርሰቡ፣ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች ጋር ሳይቀር ለመገናኘት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። በዚህ መንገድ እኔ ከኢየሱስ ጋር አንድ ከሆኩኝ፣ ፍቅሩ ወደ ሌላ ሰው ሊሄድና ሌላውን ሰው ለመሳብ ይችላል። እናም ይሄ ለሌሎች ያለን ፍቅር በአንድ አንድ ለየት ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ ብቻ የሚገለጽ ፍቅር ሳይሆን፣ ነገር ግን ከእኛ የሕይወት ህልውና ጋር የተቆራኜ ዘላቂ የሆነ ፍቅር መሆን ይኖርበታል። ለምሳሌ በኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና የተለያዩ ዓየነት ተግዳሮቶች ብፈጥሩብንም እንኳን አረጋውያንን እንደ ውድ ነገር አድርገን በፍቅር ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ የተጠራነው በዚህ ምክንያት ነው። ለዚህም ነው የታመሙ ሰዎችን በተለይም ደግሞ ምንም እንኳ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ቢሆኑም ለሁሉም በሽተኞች የተቻለንን ያህል እርዳት እንድናደርግ ተጠርተናል። ገና ያልተወለዱ ሕፃናት ሁልጊዜ መንከባከብ ይኖርብናል፣ በእዚህም መልኩ ሕይወት ሁልጊዜ ከጽንስ ጀምሮ እስከ ተፈጥሮኣዊ ሞት ድረስ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ የበኩላችንን ጥረት ለማድረግ ተጠርተናል። እኛን እንደወደደን እኛም እርስ በራስ እንድንዋደድ በሚጠይቀን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእግዚአብሔር ፍቅር ተሞልተናል። ነገር ግን እያንዳንዳችን በውስጣችን የእርሱ ዓይነት ልብ ከሌለ ይህንን በፍጹም ማድረግ አንችልም። በእየሳምንቱ በእለተ ሰንበት ቀን እንድንቀበለው የተጠራነው ቅዱስ ቁርባን በውስጣችን የኢየሱስን ልብ የመፍጠር ተልዕኮ አለውም፣ በእዚህም መልኩ ሕይወታችን ሙሉ በሙሉ በእርሱ ባሕሪይ እና በእርሱ ደግነት የተሞላች እንድትሆን የማድረግ ተልዕኮ አለው። በኢየሱስ ፍቅር ውስጥ ሆነን ለመኖር እንችል ዘንድ እና ለሌሎች ያለን ፍቅር እያደገ እንዲሄድ በተለይም ደግሞ በጣም ደካማ ለሆኑ ሰዎች ያለን ፍቅር እያደገ እንዲሄድ፣ የክርስቲያን ሕይወት ጥሪ ጋር የተቀራረበ ወይም የሚዛመድ ፍቅር ይኖረን ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ ትርዳን። ”

 

06 May 2018, 10:29