ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በእንዶኔዢያ በሦስተ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በአሸባሪዎች የተቃጣውን የቦንብ ጥቃት አወገዙ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. ዓ.ም “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት በእንዶኔዢያ በሦስተ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በአሸባሪዎች የተቃጣውን የቦንብ ጥቃት ማውገዛቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና!” ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 05/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁን  በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚደረጉ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን እና በፋሲካ በዓል ሰሞን ባሉ ቀናት ውስጥ የሚደገመውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 05/2010 ዓ.ም በእንዶኔዢያ ሀገር ሱራብያ በተባለበት ስፍራ በሦስተ አብያተክርስቲያናት ላይ በአሸባሪዎች በተቃጠው የቦንብ ጥቃት እጅግ ማዘናቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በአደጋው ነብሳቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን ከገለጹ በኃላ በጸሎት ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። እንደ እነዚህ ዓይነት ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ እስኪወገዱ ድረስ ጸሎታችንን አጠናክረን ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለው የጥላቻ መንፈስ ተወገዶ የእርቅ እና የወንድማማችነት መንፈስ ይሰፍን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በግንቦት 5/2010 ዓ.ም.  52ኛው ዓለማቀፍ የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ቀን አስመልክተው እንደ ተናገሩት ይህ ቀን “የሐሰት ዜና፣ ጋዜጠኛ ለሰላም” በሚል መሪ ቃል እንደ ተከበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ላይ የሚሰሩ ሰዎችን በተለይም ጋዜጤኞች እውነትን ፈልጎ ለዓለም ለማሳየት የሚያደርጉትን ጥረት እንደ ሚደግፉ እና ለእዚህ ጥረታቸው ከፍተኛ የሆነ አድንቆት እና ድጋፍ እንዳላቸው ቅዱስነታቸው ገለጸው ሰላም የሰፈነበት እና ማኅበራዊ ፍትህ የሚታይበት ማኅበረሰብ እስኪመሰረት ድረስ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል።

በትላንትናው ቀን ማለትም በግንቦት 05/2010 ዓ.ም የተከበረወን የእናቶች ቀን አስመልክተው የተናግሩት ቅዱስነታቸው “በመላው ዓለም ለምትገኙ እናቶች በሙሉ የከበረ ሰላምታዬን አቀርባለሁ” ካሉ በኃላ ቤተሰብን ለመንከባከብ እናቶች የሚያደርጉት ጥረት ቅዱስነታቸው እንደ ሚያደንቁ ገልጸዋል። ከእዚህ ምድር በሞት የተለዩን እናቶቻችን ከሰምይ ሆነው እንደ ሚመለከቱን የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዛ ሆነው ለእኛ መጸለያቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል። ሰማያዊ እናታችን ለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በሕይወት ጉዞዋችን ሁሉ ከእኛ ጋር ትሆን ዘንድ ልንማጸናት እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ለሁላችሁም መልካም ቀን ይሁንላችሁ “አባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ` ካሉ በኃላ ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ሰላምታን ካቀረቡ በኃላ መሰናበታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

13 May 2018, 12:05