ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 6/2010 ዓ.ም ከሮም ሀረስብከት ካህናት ጋር በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ዩሐንስ ዘ ላቴራን ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 6/2010 ዓ.ም ከሮም ሀረስብከት ካህናት ጋር በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ዩሐንስ ዘ ላቴራን ቤተክርስቲያን  

ር.ሊ.ቃ. ፍራንቸስኮስ፡ መንፈሳዊ ዝለቶችን ማስወገድ ይገባል

መንፈሳዊ ዝለቶችን ማስወገድ ይገባል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 06/2010 ዓ.ም  ከሮም ሀገረ ስብከት ካህናት፣ ገዳማዊያን ገዳማዊያት እና ከምዕመናን ተወካዮች ጋር በሮም ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ዩሐንስ ዘ ላቴራን ባዚሊካ በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው ያደርጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

መንፈሳዊ በሽታዎች ወይም በመንፈሳዊ ዝለት በተመለከተ የተሠራው ሥራ ሁለት ፍሬዎች አሰገኝቱዋል። በመጀመሪያ ደረጃ ችግሮቻችን በጣም እያደጉ መሄዳቸውን የሚያስዩ እውነታዎች የሚታዩ ሲሆን ይህም በየቁምስናዎች ውስጥ የሚታዩ መንፋሳዊ ዝለቶች ወይም መንፈሳዊ በሽታዎች ውስጥ ሰጥመው የሚገኙ ሁሉ እና እነዚህን መንፈሳዊ በሽታዎችን ወይም ዝለቶችን እውነተኛ በሆነ መልኩ ለመቋቋም የሚያስችሉትን በብጹዕ የኔታ ዴ ዶናቲስ አማካይነት የተቀመጡትን መፍትሄዎችን እናገኛለን። በሁለተኛ ደረጃ በእነዚህ እውነተኛ በሆኑት እና በተጠቀሱት እውነተኛ ተመክሮዎች የተነሳ ይህ ጉዳይ ተስፋ የመቁረጥ ወይም የብስጭት ሁኔታ ውስጥ የሚከተን ሳይሆን ነገር ግን ጌታ ሁልጊዜም ቢሆን ምሕረቱን እያደረገልን እንደ ሚገኝ በመገንዘብ ወይም በመረዳት በእዚህ ጉዞዋችን ጌታ አእምሮዋችንን በማብራት፣ እኛን በመደገፍ፣ በጉዞዋችን ውስጥ በመካከላችን ታይቶ የማይታወቅ ኅብረትን በመፍጠር እንድንጓዝ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም ያደርገው እኛ በጉዞዋችን ሂደት ሁሉ እርሱን አስቀድመን እኛ ከኃላው እንድንከተለው ስለፈለገ ነው።

እነዚህን የመሳሰሉ መሰረታዊ ሐሳቦች በጥንት ጊዜ በነበሩ የቃል ኪዳን ሕዝቦች የእርሱ ሕዝብ እንዲሆኑ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመሩት በእርሱ ቃል ብቻ እንደ ሆነ በድጋሚ እንድናስብ ያደርገናል። እኛም ብንሆን በኦሪት ዘፀአት ውስጥ በተገለፁት ንድፈ ሐሳብ ውስጥ ራሳችንን በማስገባት ይህም ጌታ የመረጣቸውን ሰዎች እንዴት እንደ መረጠ እና እንዳስተማራቸው፣ በተጨማሪም በመካከላቸው እንዴት ሕበርት እንዲፈጠር እንዳደረገ የእርሱን በዓለም ውስጥ እንደ ሚገኝ የሚያረጋግጡ መሳሪያዎች እንዲሆኑ እንድናስብ አእምሮዋችንን እንዲያበራልን መፍቀድ ይኖርብናል።

ይህንን የእስራኤል ሕዝብ የሕይወት ልምድ እንደ ቋንቋ አድርገን በመውሰድ፣ ይህም ማለት ይህንን መረዳት እና ማስፋፋት ያስችለን ዘንድ ይህንን ተመክሮ ዛሬም እኛ የማስተጋባት ኃላፊነት አለብን። የእግዚኣብሔር ሥራ፣ የጌታ ተግባር የሚሆነው በሕይወታችን ውስጥ ሰዎችን ማገናኘት እና አንድ ማድረግ ነው። እግዚኣብሔር አሁንም ቢሆን በቀድሞ ጊዜ የነበሩ ሕዝቦቹን ነጻ እንዳወጣቸው እና ወደ አዲስ ምድር እንደ መራቸው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዛሬ ከእኛ ጋር ይንቀሳቀሳል።

የኦሪት ዘፀአት ታሪክ ስለ ባርነት፣ ስለመውጣት፣ ሰለመጓዝ፣ ስለቃል ኪዳን፣ ስለፈተና፣ ስለማጉረምረም እና ስለመግባት ይገልጻል። የፈውስ ጉዞ ነበር አይደል?

ሮም የክርስትናን መንገድ በአዲስ ምዕራፍ ከጀመረች ሁለት ሺህ አመታት ቢያልፉም፣  በእነዚህ አመታት ውስጥ ሮም ያደረገችው ጉዞ እንዴት እንደ ተጓዘች፣ ለባርነት የዳረጓት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ፣ የገጠሟት መንፈሳዊ በሽታዎች ምን እንድሆኑ፣ ነጻነቱዋን የገፈፉ እና ለባርነት የዳረጉዋት ነገሮች ምን እንድ ሆኑ፣ ፈርሆን የእስራኤል ሕዝብ ልጆች እንዳይኖራቸው እንዳደረግ ሁሉ እኛም ፍሬያማ እንዳንሆን መሃን የደርጉን ነግሮች ምን እንደ ሆኑ በማሰብ ራሳችንን መጠየቅ አስፈላጊ ነው። ይህ “ልጅ የሌለው” የሚለው ሐረግ የክርስቲያን ማኅበርሰቡ ለማፍራት ያለውን ብቃት እንድናስብ ያደርገናል አይደል? ይህ ለእናንተ ልተወው የምፈልገው ጥያቄ ነው። የዛሬ ዘመን ፈርሆኖች እነማን እንደ ሆኑ ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፣ ይህ መለኮታዊ የሚመስል ኃይል፣ ይህ ፍጹም የሚመስል ኃይል፣ ይህ ሕዝቡ እግዚኣብሔርን እንዳያመልክ የሚያደርግ ኃይል፣ ሕዝቡ የሌለች ነገሮች ባሪያ እንዳይሆን ለሌሎች ኃይሎች እና ሌሎች ጉዳዮች ባሪያ እንዳይሆን ያደርገዋል።

ለእዚህ ጉዳይ ምን አልባት አንድ አመት ያህል ጊዜ መስጠት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፣ ድክመቶቻችንን በትሕትና አምነን በመቀበል እና ደክመቶቻችንን ሌሎች እንዲያውቁት በማድረግ ይህ ተመክሮ እንዲሰማን እና ከእዚህ ተመከሮ ልምድ መቅሰም ይኖርብናል፣ ይህንን በምናደርግበት ወቅት ለእኛም ሆነ በሮም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምሕረትና የእርቅ ስጦታ እናገኛለን ማለት ነው። ይህ ስጦታ በገለሰብ እና በሕዝብ ደረጃ የሚሰጠን መልካም በሆነው በአባታችን በጎ ፈቃድ ነው። ይህንን ተነሳሽነት የወሰደው እርሱ ነው፣ በክርስቶስ አማካይነት እኛን ስለወደደን እና እኛን ስለሚወደን፣ ሕይወታችንን በልቡ ውስጥ አስገብቶ የያዘው፣ እኛ ለባርነት የተዳረግን እና የተረሳን ችላ የተባልን ፍጡራን እንደሆንን  በማሰብ በክርስቶስ አማካይነት ለእኛ ምስክርነቱን ሰጥቶናል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ 8፡28 እንደ ተጠቀሰው “እግዚአብሔር፣ ለሚወዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን” የሚለው እግዚኣብሔር ይህን ሁሉ ነገር የሚያደርግልን እኛ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ እና እኛ መልካም እንድንሆን በማሰብ ነው።

በእነዚህ መነፍሳዊ የሆኑ በሽታዎች ላይ የተደርጉ ጥናቶች እንደ ሚያሳዩት በአጠቃላይ አንድ ጤናማ የሆነ የቁምስና ድካም ወይም ዝለት የሚመነጨው መሄጃ መንገድ ሲጠፋን እና ወይም ደግሞ ብቻችንን በባዶነት ስንጓዝ እንደ ሆነ ጥናቱ ያሳያል። እነዚህ ሁለቱ ባህሪይት በጣም መጥፎ የሆኑ ነገሮች እና መጥፎ የሆኑ ልምዶች ናቸው። በባዶነት መንፈስ የሚደረግ እንቅስቃሴን በተመለከተ  በተወሳሰበ እና መላቅጡ በጠፋው መነገድ ላይ እንደ መጓዝ የሚቆጠር ሲሆን መጓዝ እንጀምራለን ነገር ግን የተሳሳቱ መንገዶችን አጣምሮ የያዘ በመሆኑ የተነሳ እንጠፋለን።

ምን አልባት ጌታ እዚህ እና አሁን ራሱን በሚገለጥበት ጊዜ ራሳችንን በራሳችን ቆልፈን በቁምስናዎች ውስጥ እኛ በለመድነው የአስራር ዜይቤ ብቻ ተወስነን ሊሆን ይችላ ይሆናል፣ ይህ ደግሞ በዚህ ዘመን እጅግ በጣም ውስብስብ እና ከእግዚአብሄር ርቆ የሚገኘው እጅግ በጣም ውስብስብ ነገር ነው፣ ምክንያቱም እኛ በየክልላችን ውስጥ እና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ብቻ ተጠምደን፣ ለእኛ በአደራ የተሰጡንን ሰዎች ሕይወት ቸል ብለናል ማለት ነው። በእዚህን ጊዜ እና ከእነዚህ ፈተናዎች እና ተግድሮቶች ፊት መቆማችን ስህተት የሆነ ነገር አይደለም።

ምናልባትም እኛ ራሳችንን ባርነት ውስጥ እንደሆንን፣ ማለትም የጌታ ባልሆኑ ነገሮች ላይ ጥገኛ ሆነን መቆየታችን፣ ምናልባትም ይህ ብቻ በቂ እንደሆነ ወይም እርሱ እንድናደርግ የሚፈልገው ነገር የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ ነው ብለን በማሰባችን የተነሳ፣ በስጋ መስሪያ ድስት አጠገብ በመቆየት እና የፈርኦን ግምጃ ቤቶችን ለማጥገብ የሚያገለግሉ ጠቦቶችን በመስራት ተመሳሳይ የባርነት ወጥመድ ውስጥ ገብተን ሊሆን ይችል ይሆናል።

በራሳችን እና በድስቶቻችን (በምነመገባቸው ነገሮች ማለታቸው ነው) አለተደስትንም ይሆናል። አሁን ባለው የአሰተዳደር መዋቅር እና ሕልውና ስጋት ውስጥ ጥሎን ሊሆን ይችል ይሆናል።  “ነገር ግን ካህናቱ በሥራ የተጠመዱ ናቸው፣ ከእዚህ ሊለዩ ይገባል፣ ይህንንም፣ ያንንም ይህንንም ማድረግ አለባቸው” ሲባል ስንት ጊዜ ሰምተናል። ሕዝቡ መልካም እረኛ ማን እንደ ሆነ በሚገባ ስለሚረዳ ከእነዚህ ዓይነት አዙሪቶች ውስጥ መውጣት ይኖርብናል።

እነዚህ ሁኔታዎች እኛን ሊያደክሙን ይችላሉ፣ ነገር ግን ይህ ድካም ለኛ መለካም አጋጣሚ ነው፣ ይህ ድክመታችን በራሱ የእግዚኣብሔር ጸጋ ነው፣ ምክንያቱም መድከማችንን መረዳታችን በራሱ ከእዚህ ድካም እንድንወጣ ያነሳሳናል።

ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ ለመውጣት ደግሞ የእግዚኣብሔር ጥሪ እና የባልንጄሮቻችን እገዛ እና ድጋፍ ያስፈልገዋል። ለእግዚአብሔር ያለን ጥማታችንን ለመግለጽ ከሮም ሕዝቦቻችን ውስጥ ለሚወጣው ጩኸት ምንም ፍርሃት ሳይኖረን ማዳመጥ አለብን; ይህ መለኮታዊ መዳን እንደሚያስፈልገው የሚናገረው በምን መልኩ ነው? እግዚአብሔር ያንን ጩኸት እንዴት ይመለከተዋል? ከእነዛ ሁኔታዎች መካከል እናንተ ካረጋገጣችሁት እውነታ ሳይቀር ያንን ጩኸት የሚገልጹ ሁኔታዎች የተኞቹ ናቸው! እግዚአብሔር ራሱ (ከማጉረምረም መንፈስ ከሚመጣው መራራ ልምድ) ሕይወታችን ጥቅም የሌለው እንደ ሆነ በመቁጠር በሥራ ብዛት የሚያፈናፍኑን ነገሮች እና በእዛ ውስጥ እያንዳንዳችን የሚያመልጥ ጊዜ በመሆኑ የተነሳ፣ እምነትን በተጨናነቀ መንገድ የሚከናወን ተግባር ነው ከሚል መንፈስ በመነጨ መልኩ ከምንኖረው ኑሮ እንድንወጣ እና እንድንጸጸት በማድረግ በሕይወታችን ደስተኞች እና ደስተኛ የሚያደርጉንን ተግባራት ብቻ በመስራት እንድንኖር ያደርገናል።

በተወሰነ መልኩ በአዲስ ጅማሬ እና በአዲስ መልኩ በመውጣት የእግዚኣብሔር ልጆች መሆናችንን በሚያሳይ መልኩ በመታደስ፣ ወደ ኃላ ጥለን በምንሄደው ነገር ሳናዝን ወደ ፊት ብቻ በመጓዝ በሮም ከተማ ውስጥ ያለችውን ቤተክርስቲያን አዲስ በሆነ ጎዳና ላይ እንድትራመድ ማድረግ እንደ ሚገባችሁ እየጋበዝኩዋችሁ እንደ ሆን የሚገባችሁ  የመስለኛል።

ቀደም ሲል እንዳልኩት ሙሴ በበረሃ እንዳደረገው ሁሉ የሰዎችን ጩኸት በመስማት በእግዚአብሄር ቃል ብርሃን በመታገዝ እንዴት መተርጎም እንዳለብን በማወቅ፣ ሕዝቡ የሚኖረውን ማኅበራዊ እና ባህላዊ ሁኔታ እንዴት መተርጎም እንዳለብን ሳይቀር ማወቅ አስፈላጊ ይሆናል። ያም ማለት እነርሱ ወይም ሕዝቡ በየተኛው የቅድስና ዓይነት ውስጥ እና ከእርሱ ጋር በኅብረት እንደሚገኝ ማስተዋል ጥበብ በተሞላው መልኩ ማወቅ ማለት ነው። በቅዱስ ወንጌል እሴቶችን በመጠበቅ እየኖሩ የሚገኙ ሰዎች እና ከጌታ ጋር ወዳጅነት የፈጠሩ ሰዎችን በማበረታታት ከእነርሱ ጋር አብሮ መኖር እና መጓዝ ማለት ነው። በሮም ከተማ ውስጥ በእየለቱ የሚከናውኑትን ሥራ ለሌላ ሰው የሕይወት ሕልውና ምንጭ አድርገው በመቁጠር የሚኖሩ፣ ምንም ዓይንት ድብቅ የሆነ አጀንዳ ሳይኖራቸው ይህንን መልካም ሥራቸውን ወይም ተግባራቸውን እግዚኣብሔርን በመፍራታቸው የተነሳ በጎ ተግባራትን የሚያከናውኑ ብዙ ሰዎች በሮም ከተማ ይገኛሉ። በውል በስም የማይታወቁ፣ የታሪክ ልጆች የሆኑ፣ ከቅዱሳን ሰዎች ዘር የተገኙ፣ እኛ በውል በማናውቃቸው ሰዎች አማካይነት እስከዛሬ ድረስ ተጠብቆ እስከኛ ዘመን ድረስ እንዲደርስ ያደርጉ፣ የማይታወቁ ሰዎች፣ የተደበቁ ነገር ግን ሁሉም ነገር ወደ ፊት በሰላም እንዲሄድ የሚያደርጉ ብዙ ሰዎች አሉ።

ይህንን ለማድረግ ማህበረሰቦቻችን ሰዎችን ማፍራት እንዲችሉ ማብቃት ያስፈልጋል፣ ይህ በፍጹም መዘንጋት የሌለበት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፣ ሕዝብ የሌለው ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አይደለችም፡ ሕዝባችንን የማንውቅ፣ ለሕዝባችን እውቅና የማንሰጥ፣ ሕዝባችንን በጥሩ ሁኔታ የማንወድ በአጭሩ ለሕዝቡ እውቅና የምንሰጥ ልንሆን ይገባል።

የክርስቲያኑ ማኅበረሰቡን ለየት ባለ መልኩ እንዲመራ የተሾመው ካህኑ ወይም ቆመሱ  ቢሆንም ነገር ግን የሐዋሪያዊ ሥራ ተልዕኮ እና ሐዋሪያዊ እንክብካቤ ለካህኑ ወይም ለቆመሱ ብቻ የተተወ ተግባር ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ክርስቲያኖች ሳይቀር በሐዋሪያዊ ሥራዎች እና ተልዕኮዎች ውስጥ የመሳተፍ መነፈሳዊ ግዴታ አለባቸው።

ይሄንን በምንተገብርበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስን ተግባር በመካከላችን ለመለማመድ የሚያስችለን መሳሪያ መሆን እንችላለን፣ መነገዶች ሲቀየሩ እናያለን። በሙሴ አምካይነት እግዛኢብሔር በእስራሔል ሕዝቦች ውስጥ ጣልቃ በመግባት እንዳዳናቸው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ እግዚኣብሔር በልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሕዝቡን መልሶ ያነጻቸዋል ወደ እርቅ መነገድ እንዲመለሱም በማድረግ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሞትን በሚያመጣው ከኃጢኣት እና ከኢፍታዊ መነገድ በመራቅ  ትክክለኛ የእግዚኣብሔር ሕዝቦች እንድንሆን ያደርገናል።  

ግን እኛ እራሳችንን ሳይሆን የእግዚኣብሔርን ሕዝብ በቅድሚያ ልንመለከት የገባል። ይህ ነገር ደግሞ በእርግጥ አዲስ ነገር እንዲከሰት ያደርጋል፣ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የጌታን ፊት እንድናይ ያደርገናል። ማንነታችንን እና የተሰጠንን ጸጋ መፍራት ሳይሆን የሚኖርብን ነገር ግን ፍሬያም እንዲሆኑ ማድረግ ነው የሚጠበቅብን። ጉዞዋችን ምን አልባት ረዥም ሊሆን ይችል ይሆናል፣ የእስራኤል ሕዝቦች 40 አመታትን በበረሃ አሳልፈዋል፣ በፍጹም ተስፋ ሳንቆርጥ ወደ ፊት መጓዝ ይገባናል። እግዚኣብሔር እያንዳንዳችን በዩሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 15፡16 “እንድንሄድ እና ፍሬ እንድንፈራ” ይጋብዘናል።

በተጨማሪም በማኅበረሰባችሁ ውስጥ ያጋጠሟቸችሁን አንዳንድ ችግሮች እና መንፈሳዊ በሽታዎች እንድተመለከቱ እንድታጠኑ እጋብዛችኃለሁ፣ አንድ አንድ ለምግብነት የማይሆኑ ነገሮች ካሉ ደግሞ እነዛን ነገሮች ሰው እንዲመገባቸው ማቅረብ የለብንም፣ ይህም ማለት ፍሬያም ሊያድርጉ የሚችሉ ተግባሮች ላይ ብቻ መተኮር ይጋባል ማለት ነው።  በርቱ ወደ ፊት ሂዱ። ጊዜ የእኛ ስለሆነ፣ ወደ ፊት ተጓዙ።

 

14 May 2018, 12:59