ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ምስጢረ ጥምቀት ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ወይም ደግሞ እንዳስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በሚያዝያ 03/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ያደረጉት በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ ባተኮረው የክፍል አንድ የትምህርተ ክርስትሶስ አስተምህሮ “ምስጢረ ጥመቀት የክርስትና ሕይውት መሰረት ነው” ማለታቸውን መገለጻችን ይታወሳል። ባልፈው ሳምንት ማለትም በሚያዝያ 10/2010 ዓ.ም. በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሁለት አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ምስጢረ ጥምቀት የክርስትና እምነት ምልክት ነው” ማለታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለት አሁንም በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ባደርጉት ክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ምስጢረ ጥምቀት “ክፉ መንፈስን የማሸንፊያ መሳሪያ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።
የእዚህ ዝግጅት አጠናቃሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን
በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል “ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብም፣ ባገኝም ሆነ ባጣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ። ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ” (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፡12-13)።
ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በምስጢረ ጥምቀት ዙሪያ ላይ አድርገውት የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ