ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የክርስቲያኖች ፍቅር የመነጨው ከኢየሱስ ነው
የሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ” ጸሎት
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳኤ በዓል ከተከበረ እነሆ አምስተኛው የትንሳኤ ሳምንት ላይ እንደ ምንገኝ ይታወቃል። ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት አምስተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ ታውቁዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የክርስቲያኖች ፍቅር የመነጨው ከርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰብ ሳይሆን ከኢየሱስ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።
ክቡራት እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።
29 Apr 2018, 10:14