ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ነው”

የመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ጸሎት

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳሄ ሰንበት ቀጥሎ የሚገኘው ሰንበት የመልኮታዊ ምሕረት ሰንበት በመባል  የምታወቅ ሲሆን ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድጎ የሰው ልጆችን ኃጢያት በመለኮታዊ ምሕረት ያስተሰረዬበት ቀን በማስታወስ ይከበራል። በእዚህም መሰረት ይህ ቀን በታላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት በተካሄደ መስዋዕተ ቅዳሴ በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት ተከብሮ ማለፉ ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ነው ማለታቸው ተገልጹዋል። 

የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

“ ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ዩሐንስ 20:19-31) “ተመልከት” የሚለው ግስ በተደጋጋሚ ተጠቅሱዋል። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። ደቀ-መዛሙርቱም ለቶማስ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። ነገር ግን ይህ የወንጌል ክፍል “ጌታን እንዴት እንዳዩት አይግልጽም፣ ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ይሁን አይሁን በደንብ አያብራራም። ነገር ግን ቀለል ባለ ሁኔታ “እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው” በማለት ይገልጻል። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ደቀ-መዛሙርቱ ኢየሱስን ያወቅቱ ቁስሎቹን ካዩ በኃላ እንደ ሆነ አድጎ በማቅረብ ቀለል ባለ ሁኔታ ይገልጻል። ቶማስንም የገጠመው ተመሳሳይ የሆነ ነገር ነው። እርሱ ራሱ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ” አላምንም ብሎ ተናግሮ ነበር፣ ነገር ግን የእጆቹን ቁስል በተመለከተ ወቅት አመነ። ምንም እንኳን ቶማስ እምነት ጎድሎት የነበረ ሰው ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ቶማስ ምስጋና ልቸረው ይገባል፣ ምክንያቱም እርሱ ኢየሱስ በሕይወት መኖሩን ከሌሎች መስማቱ ወይም ደግሞ ኢየሱስ እንዲሁ በሥጋው ብቻ መገለጹ አላስደሰተው ነበር። ወደ ውስጥ ዘልቆ መመልከት ፈልጎ ነበር፣ የፍቅር ምልክት የሆኑትን የኢየሱስን ቁስሎች በእጆቹ ለመንካት ፈልጎ ነበር። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ቶማስን “ዲዲሞስ” በማለት የገለጸው ሲሆን ይህም “መንትያ” የሚል ትርጉም የሚያሰማ ሲሆን በእውነት እርሱ የእኛ መንታ ወንድማችን ነው። ምክንያቱም ለእኛም ቢሆን እግዚኣብሔር መኖሩን ብቻ ማወቁ በራሱ በቂ አይደለም። ጌታ ከሙታን መነሳቱ እና ከእኛ ርቆ መገኘቱ በራሱ ሕይወታችንን የተሟላ አያደርጋትም፣ ምንም እንኳን ፍትሀዊ እና ቅዱስ ቢሆንም ከእኛ ርቆ የሚገኝ እግዚኣብሔር ብዙም ትኩረታችንን አይስብም። በፍጹም! እኛም ብንሆን “እግዚኣብሔርን ለመመልከት” በእጃችን ለመዳሰስ እና በእውነት ከሙታን መነሳቱን እና ለእኛ ሲል መነሳቱን ሳይቀር መመልከት ይገባናል። ታዲያ እንዴት ነው እርሱን ለመመልከት የምንችለው? እርሱን ልክ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ በቁስሎቹ አማክይነት ልንመለከተው እንችላለን። ደቀ-መዛሙርቱ ቁስሎቹን አትኩረው በተመለከቱ ጊዜ እርሱ የነበረውን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ተመለከቱ። ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ብክዱትና ጥለው ቢሄዱም እርሱ ይቅር እንዳላቸው ተረዱ። ወደ ኢየሱስ ቁስል ለመግባት ከፈለግን ከእርሱ ልቡ የሚፈስውን ጥልቅ ፍቅር ማሰላሰል ያስፈልጋል። ይህም ብቸኛው መንገድ ነው። የእርሱ ልብ ለእያንዳንዳችን እንደ ሚመታ ማወቅ ነው። የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ራሳችንን ክርስቲያኖች አድርገን እንቆጥራለን፣ ራሳችንን ክርስቲያኖች ነን በማለት እንጠራለን፣ ስለ ብዙ የክርስትና እምነት መልካም እሴቶች እንናገራለን፣ ነገር ግን ልክ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ የእርሱን ፍቅር በመንካት ኢየሱስን ማየት ያስፈልገናል። ወደ እምነት ልብ ውስጥ መግባት የምንችለው በእዚሁ መልክ ብቻ ነው፣ ከጥርጣሬ ባሻገር በመሄድ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ ሰላምና ደስታ መግኘት የምንችለው በእዚሁ ሁኔታ ብቻ ነው። ቶማስ የኢየሱስን ቁስ በተመለከተ ወቅት ““ጌታዬ፤ አምላኬ!” አለው። ቶማስ በተደጋጋሚ “ጌታዬ እና አምላኬ” ብሎ የተናገራቸው የቃላት ቅጢያዎች ላይ ለማሰላሰል እፈልጋለሁ። ግላዊ የሆነ ቅርበትን በጣም የሚፈጥሩ ቅጢያዎች ናቸው። በእነዚህ ጉዳይ ላይ ስናሰላስል ይህን ቅጥያ መናልባት ለእግዚኣብሔር መጠቀም ተገቢ ላይመስል ይችል ይሆናል። እንዴት ነው እግዚኣብሔርን የግሌ ማድረግ የምችለው? ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚኣብሔርን እንዴት ነው የግሌ ማደርግ የምችለው? እውነታው የሚያሳየው ግን እግዚኣብሔርን የኔ ነህ በምንልበት ወቅት እርሱን አናረክሰውም ነገር ግን እርሱ ለእኛ ያሳየውን ምሕረት እናክብራለን። ምክንያቱም እግዚኣብሔር ራሱ “የእኛ ለመሆን” ተመኝቱዋል። ልክ በአንድ የፍቅር ታሪክ ውስጥ እንደ ሚገለጸው “አንተ ለእኔ ስትል ሰው ሆነኃል፣ ለእኔ ስትል ሞተህ ከሞት ተነስተሃል፣ ስለእዚህ አንተ እግዚኣብሔር ብቻ ሳትሆን አንተ የእኔ እግዚኣብሔር የእኔም ሕይወት ነህ” ልንለው ይገባል። እኔ እፈልገው የነበረው ዓይነት ፍቅር ከጠበቁት በላይ በአንተ ውስጥ አግኝቻለሁ ልንለው ይገባል። እግዚኣብሔርን የግላችን አድርገን በመቁጠራችን የተነሳ እግዚኣብሔርን አንበድለውም፣ ምክንያቱም ፍቅር መተማመንን ይጠይቃል፣ ምሕረት ደግሞ መታመንን ይፈልጋል። በአስርቱ ትዕዛዛት መግቢያ ላይ እግዚኣብሔር “እኔ እግዚኣብሔር አምላክህ ነኝ” (ኦሪት ዘጸዕት 20:2) ተብሎ እንደ ተጠቀሰ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም በድጋሚ “እኔ እግዚኣብሔር አምላክህ ቅናተኛ ነኝ” በማለት ማረጋገጫ ሲሰጥ እናያለን። እዚህ ላይ እግዚኣብሔር “የአንተ አምላክ ነኝ” በማለት ራሱን ቅናተኛ የሆነ አፋቃሪ አድርጎ ያቀርባል። ከቶማስ ጥልቅ ልብ ውስጥ “ጌታዬ፤ አምላኬ!” የሚል ምላሽ መጣ። ዛሬ በክርስቶስ ቁስል አማክይነት ወደ እግዚኣብሔር ምስጢር ውስጥ በምንገባበት ወቅት እርሱ ካለው ብዙ ነገሮች መካከል ምሕረት አንዱ መሆኑን መረዳት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ጭምር መሆኑን እንረዳለን። ከዚያ በኋላ እንደ ቶማስ እርግጠኛ እና ታማኝ ያልሆንን ደቀ-መዛሙርት ሳንሆን ነገር ግን የሚንበረከክ ደቀ-መዝሙር እንሆናለን። እኛም በእርሱ ፍቅር እንወድቃለን! እኔ ከጌታ ፍቅር ይዞኛል ማለት በፍጹም ልያስፈራን አይገባም። ይህን ፍቅር እንዴት ነው ለማድነቅ የምንችለው? የኢየሱስን ምሕረት በእጃችን ዛሬ ለመንካት የምንችለው እንዴ ነው? በእዚህ ረገድ ቅዱስ ወንጌል በፋሲካ ምሽት በማለት ጠበቅ አድርጎ በመናገር ፍንጭ ይሰጠናል፣ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኃላ ኢየሱስ ለኃጢያት ስርዬት የሚሆን መንፈስ በመስጠት ይጀምራል። ምሕረት ለማግኘት ራሳችንን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ምሕረትን ለማግኘት ራሳችንን አዘጋጅተናል ወይ? በማለት ራሴን እና እናንተን እያንዳንዳችሁን ሳይቀር ለመጠየቅ እፈልጋለሁ። የእርሱን ፍቅር ለመቋደስ ከእዚህ መጀመር ይኖርብናል። ይቅር ለመባል ፋቃደኛ ነኝ ወይ? “አባ እኔ ምስጢረ ንስሓ ለማድረግ መሄድ ያስቸግረኛል” . . .የመሳሰሉ ነገሮችን እንላለን። በእግዚኣብሔር ፊት ቆመን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ደቀ-መዛሙርቱ የገጠማቸው ዓይነት ፈተና ውስጥ እንገባለን፣ ራሳችንን በፍርሃት በአንድ ቤት ውስጥ ቆልፈን እንሸሸጋለን። እነርሱ ይህንን አድርገው የነበረው ከነበራቸው ከፍተኛ ፍርሃት የተነሳ ሲሆን፣ እኛም ከፍርሃታችን የተነሳ ልባችንን መክፈት እና ኃጢኣታችንን ለመናዘዝ እናፍራለን። በፍረሃት ተሽሽገን በተቆለፈ ቤት ውስጥ እንድንቀመጥ ሳይሆን ራሳችንን እንድንቆልፍ ሳይሆን እርሱን ለመገናኘት ወደ ፊት እንድንጓዝ ይረዳን ዘንድ አፍረታችንን መረዳት እንችል ዘንድ ጌታ ጸጋውን ይስጠን። የአፍረት ስሜት በሚሰማን ወቅት ልናመስግን ይገባናል፣ ምክንያቱም ይህ የአፍረት ስሜት ክፉ የሆነ ነገር እንደማንቀበል ያሳያል እናም ይህ ጥሩ ስሜት ነው። አፍረት ክፉ ነገሮችን ማሸነፍ እንችል ዘንድ ነብሳችን ወደ ጌታ በምስጢር የምትልከው ጥሪ ነው። ምንም ነገር የማያስፍረን ከሆነ ይህ ጉዳይ በእውነት አሳሳቢ ነው። የአፍረት ስሜት በሚሰማን ወቅት መፍራት የለብንም! ከአፍረት ወደ ምሕረት እንሻገራለን። ስለእዚህ አፍረትን አትፍሩ! በፍጹም እንዳትፈሩ! ነገር ግን ከእግዚአብሔር ምሕረት በፊት አሁንም አንድ መተው የሚገባን በር አለ። አንድን ነገር ለመተው አለመፈልግ ማለት የተዘጋ በር እንደ ማለት ነው። ይህም ደቀ-መዛሙርቱ በፋሲካ ምሽት የገጠማቸው ተመክሮ ሲሆን ሁሉም ነገር እነርሱ በጠበቀቱ መልኩ ባለማከናወናቸው ተስፋ ቆርጠው ወደ ቀድሞ ኑሮዋቸው ለመመለስ ፈለጉ። ተስፋ ቆርጠው በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፣ በሕይወታቸው ውስጥ የነበረው የኢየሱስ ምዕራፍ የተዘጋ መስሎዋቸው የነበረ ሲሆን ምንም እንኳን ከእርሱ ጋር ብዙ ጊዜ አስልፈው የነበረ ቢሆንም ቅሉ ይህ ቆይታ ምንም ነገር አልቀየረም ነበር፣ በእዚህም የተነሳ ወደ መጡበት ወደ ቅድሞ ሕይወታቸው መመለስ ፈለጉ። እኛም ራሳችን “ለብዙ ጊዜ ክርስቲያን ነበርኩኝ፣ ነገር ግን በሕይወቴ ውስጥ የተቀይረ ምንም ነገር የለም፣ ሁሌም ቢሆን ተመሳሳይ የሆነ ኃጢያት እሠራለሁ፣ ምንም ለውጥ የለም” ልንል እንችል ይሆናል። በእዚህም ተስፋ ቆርጠን ለእግዚኣብሔር ምሕረት የነበረን ተስፋ ይጨልማል። ነገር ግን በእዚህ ረገድ “የእኔ ምሕረት ከአንተ ኃጢያት እንደ ሚበልጥ አታምንምን? ተመለስ እና ይቅርታን ጠይቅ፣ ማን አሸናፊ ሆኖ እንደ ሚወጣ ይታያል! በማለት እግዚኣብሔር ራሱ ይጋፈጠናል። ምስጢረ ንስሓን የሚያዘወትር አንድ ሰው ይህንን በሚገባ ይረዳዋል፣ ሁሉም ነገር በነበረበበት እንደ ማይቀጥል ይረዳል። ምሕረትን በሚደርግልን ጊዜያት ሁሉ፣ እንበረታታለን፣ ምክንያቱም በየጊዜው የፍቅር ስሜት ይሰማናል፣ በእግዚኣብሔር አባታችን እቅፍ ውስጥ እንዳለን ይሰማናል። ተመልሰን በምንወድቅባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ይህም የተከሰተው በመወደዳችን ምክንያት እንደ ሆነ እንረዳለን፣ በእዚህም ምክንያት ይበልጡኑ የሐዘን ስሜት ያሰማናል፣ ይህም ሐዘን ቀስ በቀስ ከኃጢኣት እንድንላቀቅ ያደርገናል። ከእዚያም በኃላ ሕይወታችን የሚበረታው የእግዚኣብሔርን ምሕረት ስንቀበል ብቻ መሆኑን እና ከአንድ ምሕረርት ወደ ሌላ ምሕረት መጓዝ አስፈላጊ እንደ ሆነ እንረዳለን። መሆን ያለበትም ይህ ነው ልንክተለው የሚገባው ሂደት ከአፍረት ወደ አፍረት ከምሕረት ወደ ምሕረት መጓዝ ነው። ከአፍረት እና የቀድሞ የሕይወት መስመራችን መቀየር ቀጥሎ የሚመጣው ኃጢኣታችን ነው። እኔ አንድ ከባድ ኃጢኣት በምፈጽምበት ወቅት በታማኝነት ራሴን በራሴ ይቅር የማልል ከሆነ፣ ታዲያ እግዚኣብሔር እንዴት ይቅር ይለኛል? በእዚህ ረገድ ይህ በር የተቆለፈው በአንድ በኩል ብቻ ነው፣ ይሄውም በእኛ በኩል፣ ነገር ግን ለእግዚኣብሔር ሙሉ በሙሉ የተዘጋ በር ሊኖር አይችልም። በዛሬው እለት ቅዱስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው የተዘጋ በሚመስል በር ውስጥ ሳይቀር መግባት ይወዳል። ከእዚያም እግዚኣብሔር ድንቅ ነገሮችን ይፈጽማል። እርሱ እኛን ብቻችንን ለመተው በፍጹም አይፈልግም፣ እኛ ግን እርሱን ችላ እንለዋለን። ነገር ግን ምስጢረ ንስሓ በምንገባ ወቅት ከእርሱ ያለያየን ኃጢኣት ሁሉ ተወግዶ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት እንችላለን። በእዚያም ለእኛ ፍቅር ሲል የቆሰለው እኛን ለመገናኘት ይመጣል። የእኛን ቁስሎች ወደ እርሱ ክብር ወደ ተሞላው ቅስል ይቀይረዋል። የእኛ የተጎሳቆሉ ቁስሎች ወደ እርሱ በክብር የተሞላ ቁስል ይለወጣሉ።ምክንያቱም እርሱ ራሱ ምሕረት ስለሆነ የእኛን የተጎሳቆሉ ቁስሎች በምሕረቱ ይቀይረዋል። እንደ ቶማስ እውነትን ለማግኘት የሚያስችለንን ጸጋ ከእግዚኣብሔር እንጠይቅ፣ በእርሱ ምሕረት ደስታን እንድናገኝ፣ በእርሱ ምሕረት ተስፋችን እንዲለመልም እንደ ሐዋሪያው ቶምስ የእግዚኣብሔርን ጸጋ እንማጸን።የመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” ጸሎት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት የፋሲካ ወይም የትንሳሄ ሰንበት ቀጥሎ የሚገኘው ሰንበት የመልኮታዊ ምሕረት ሰንበት በመባል የምታወቅ ሲሆን ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድጎ የሰው ልጆችን ኃጢያት በመለኮታዊ ምሕረት ያስተሰረዬበት ቀን በማስታወስ ይከበራል። በእዚህም መሰረት ይህ ቀን በታላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት በተካሄደ መስዋዕተ ቅዳሴ በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት ተከብሮ ማለፉ ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ነው ማለታቸው ተገልጹዋል። የእዚህ ዜና አጠናቃሪ፡ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 30/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያስሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን። ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል ውስጥ (ዩሐንስ 20:19-31) “ተመልከት” የሚለው ግስ በተደጋጋሚ ተጠቅሱዋል። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። ደቀ-መዛሙርቱም ለቶማስ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። ነገር ግን ይህ የወንጌል ክፍል “ጌታን እንዴት እንዳዩት አይግልጽም፣ ከሙታን የተነሳው ኢየሱስ ይሁን አይሁን በደንብ አያብራራም። ነገር ግን ቀለል ባለ ሁኔታ “እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው” በማለት ይገልጻል። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ደቀ-መዛሙርቱ ኢየሱስን ያወቅቱ ቁስሎቹን ካዩ በኃላ እንደ ሆነ አድጎ በማቅረብ ቀለል ባለ ሁኔታ ይገልጻል። ቶማስንም የገጠመው ተመሳሳይ የሆነ ነገር ነው። እርሱ ራሱ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ” አላምንም ብሎ ተናግሮ ነበር፣ ነገር ግን የእጆቹን ቁስል በተመለከተ ወቅት አመነ። ምንም እንኳን ቶማስ እምነት ጎድሎት የነበረ ሰው ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ቶማስ ምስጋና ልቸረው ይገባል፣ ምክንያቱም እርሱ ኢየሱስ በሕይወት መኖሩን ከሌሎች መስማቱ ወይም ደግሞ ኢየሱስ እንዲሁ በሥጋው ብቻ መገለጹ አላስደሰተው ነበር። ወደ ውስጥ ዘልቆ መመልከት ፈልጎ ነበር፣ የፍቅር ምልክት የሆኑትን የኢየሱስን ቁስሎች በእጆቹ ለመንካት ፈልጎ ነበር። ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ቶማስን “ዲዲሞስ” በማለት የገለጸው ሲሆን ይህም “መንትያ” የሚል ትርጉም የሚያሰማ ሲሆን በእውነት እርሱ የእኛ መንታ ወንድማችን ነው። ምክንያቱም ለእኛም ቢሆን እግዚኣብሔር መኖሩን ብቻ ማወቁ በራሱ በቂ አይደለም። ጌታ ከሙታን መነሳቱ እና ከእኛ ርቆ መገኘቱ በራሱ ሕይወታችንን የተሟላ አያደርጋትም፣ ምንም እንኳን ፍትሀዊ እና ቅዱስ ቢሆንም ከእኛ ርቆ የሚገኝ እግዚኣብሔር ብዙም ትኩረታችንን አይስብም። በፍጹም! እኛም ብንሆን “እግዚኣብሔርን ለመመልከት” በእጃችን ለመዳሰስ እና በእውነት ከሙታን መነሳቱን እና ለእኛ ሲል መነሳቱን ሳይቀር መመልከት ይገባናል። ታዲያ እንዴት ነው እርሱን ለመመልከት የምንችለው? እርሱን ልክ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ በቁስሎቹ አማክይነት ልንመለከተው እንችላለን። ደቀ-መዛሙርቱ ቁስሎቹን አትኩረው በተመለከቱ ጊዜ እርሱ የነበረውን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ተመለከቱ። ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ብክዱትና ጥለው ቢሄዱም እርሱ ይቅር እንዳላቸው ተረዱ። ወደ ኢየሱስ ቁስል ለመግባት ከፈለግን ከእርሱ ልቡ የሚፈስውን ጥልቅ ፍቅር ማሰላሰል ያስፈልጋል። ይህም ብቸኛው መንገድ ነው። የእርሱ ልብ ለእያንዳንዳችን እንደ ሚመታ ማወቅ ነው። የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ራሳችንን ክርስቲያኖች አድርገን እንቆጥራለን፣ ራሳችንን ክርስቲያኖች ነን በማለት እንጠራለን፣ ስለ ብዙ የክርስትና እምነት መልካም እሴቶች እንናገራለን፣ ነገር ግን ልክ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ የእርሱን ፍቅር በመንካት ኢየሱስን ማየት ያስፈልገናል። ወደ እምነት ልብ ውስጥ መግባት የምንችለው በእዚሁ መልክ ብቻ ነው፣ ከጥርጣሬ ባሻገር በመሄድ እንደ ደቀ-መዛሙርቱ ሰላምና ደስታ መግኘት የምንችለው በእዚሁ ሁኔታ ብቻ ነው። ቶማስ የኢየሱስን ቁስ በተመለከተ ወቅት ““ጌታዬ፤ አምላኬ!” አለው። ቶማስ በተደጋጋሚ “ጌታዬ እና አምላኬ” ብሎ የተናገራቸው የቃላት ቅጢያዎች ላይ ለማሰላሰል እፈልጋለሁ። ግላዊ የሆነ ቅርበትን በጣም የሚፈጥሩ ቅጢያዎች ናቸው። በእነዚህ ጉዳይ ላይ ስናሰላስል ይህን ቅጥያ መናልባት ለእግዚኣብሔር መጠቀም ተገቢ ላይመስል ይችል ይሆናል። እንዴት ነው እግዚኣብሔርን የግሌ ማድረግ የምችለው? ሁሉን ቻይ የሆነውን እግዚኣብሔርን እንዴት ነው የግሌ ማደርግ የምችለው? እውነታው የሚያሳየው ግን እግዚኣብሔርን የኔ ነህ በምንልበት ወቅት እርሱን አናረክሰውም ነገር ግን እርሱ ለእኛ ያሳየውን ምሕረት እናክብራለን። ምክንያቱም እግዚኣብሔር ራሱ “የእኛ ለመሆን” ተመኝቱዋል። ልክ በአንድ የፍቅር ታሪክ ውስጥ እንደ ሚገለጸው “አንተ ለእኔ ስትል ሰው ሆነኃል፣ ለእኔ ስትል ሞተህ ከሞት ተነስተሃል፣ ስለእዚህ አንተ እግዚኣብሔር ብቻ ሳትሆን አንተ የእኔ እግዚኣብሔር የእኔም ሕይወት ነህ” ልንለው ይገባል። እኔ እፈልገው የነበረው ዓይነት ፍቅር ከጠበቁት በላይ በአንተ ውስጥ አግኝቻለሁ ልንለው ይገባል። እግዚኣብሔርን የግላችን አድርገን በመቁጠራችን የተነሳ እግዚኣብሔርን አንበድለውም፣ ምክንያቱም ፍቅር መተማመንን ይጠይቃል፣ ምሕረት ደግሞ መታመንን ይፈልጋል። በአስርቱ ትዕዛዛት መግቢያ ላይ እግዚኣብሔር “እኔ እግዚኣብሔር አምላክህ ነኝ” (ኦሪት ዘጸዕት 20:2) ተብሎ እንደ ተጠቀሰ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም በድጋሚ “እኔ እግዚኣብሔር አምላክህ ቅናተኛ ነኝ” በማለት ማረጋገጫ ሲሰጥ እናያለን። እዚህ ላይ እግዚኣብሔር “የአንተ አምላክ ነኝ” በማለት ራሱን ቅናተኛ የሆነ አፋቃሪ አድርጎ ያቀርባል። ከቶማስ ጥልቅ ልብ ውስጥ “ጌታዬ፤ አምላኬ!” የሚል ምላሽ መጣ። ዛሬ በክርስቶስ ቁስል አማክይነት ወደ እግዚኣብሔር ምስጢር ውስጥ በምንገባበት ወቅት እርሱ ካለው ብዙ ነገሮች መካከል ምሕረት አንዱ መሆኑን መረዳት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ጭምር መሆኑን እንረዳለን። ከዚያ በኋላ እንደ ቶማስ እርግጠኛ እና ታማኝ ያልሆንን ደቀ-መዛሙርት ሳንሆን ነገር ግን የሚንበረከክ ደቀ-መዝሙር እንሆናለን። እኛም በእርሱ ፍቅር እንወድቃለን! እኔ ከጌታ ፍቅር ይዞኛል ማለት በፍጹም ልያስፈራን አይገባም። ይህን ፍቅር እንዴት ነው ለማድነቅ የምንችለው? የኢየሱስን ምሕረት በእጃችን ዛሬ ለመንካት የምንችለው እንዴ ነው? በእዚህ ረገድ ቅዱስ ወንጌል በፋሲካ ምሽት በማለት ጠበቅ አድርጎ በመናገር ፍንጭ ይሰጠናል፣ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ በኃላ ኢየሱስ ለኃጢያት ስርዬት የሚሆን መንፈስ በመስጠት ይጀምራል። ምሕረት ለማግኘት ራሳችንን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ምሕረትን ለማግኘት ራሳችንን አዘጋጅተናል ወይ? በማለት ራሴን እና እናንተን እያንዳንዳችሁን ሳይቀር ለመጠየቅ እፈልጋለሁ። የእርሱን ፍቅር ለመቋደስ ከእዚህ መጀመር ይኖርብናል። ይቅር ለመባል ፋቃደኛ ነኝ ወይ? “አባ እኔ ምስጢረ ንስሓ ለማድረግ መሄድ ያስቸግረኛል” . . .የመሳሰሉ ነገሮችን እንላለን። በእግዚኣብሔር ፊት ቆመን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ደቀ-መዛሙርቱ የገጠማቸው ዓይነት ፈተና ውስጥ እንገባለን፣ ራሳችንን በፍርሃት በአንድ ቤት ውስጥ ቆልፈን እንሸሸጋለን። እነርሱ ይህንን አድርገው የነበረው ከነበራቸው ከፍተኛ ፍርሃት የተነሳ ሲሆን፣ እኛም ከፍርሃታችን የተነሳ ልባችንን መክፈት እና ኃጢኣታችንን ለመናዘዝ እናፍራለን። በፍረሃት ተሽሽገን በተቆለፈ ቤት ውስጥ እንድንቀመጥ ሳይሆን ራሳችንን እንድንቆልፍ ሳይሆን እርሱን ለመገናኘት ወደ ፊት እንድንጓዝ ይረዳን ዘንድ አፍረታችንን መረዳት እንችል ዘንድ ጌታ ጸጋውን ይስጠን። የአፍረት ስሜት በሚሰማን ወቅት ልናመስግን ይገባናል፣ ምክንያቱም ይህ የአፍረት ስሜት ክፉ የሆነ ነገር እንደማንቀበል ያሳያል እናም ይህ ጥሩ ስሜት ነው። አፍረት ክፉ ነገሮችን ማሸነፍ እንችል ዘንድ ነብሳችን ወደ ጌታ በምስጢር የምትልከው ጥሪ ነው። ምንም ነገር የማያስፍረን ከሆነ ይህ ጉዳይ በእውነት አሳሳቢ ነው። የአፍረት ስሜት በሚሰማን ወቅት መፍራት የለብንም! ከአፍረት ወደ ምሕረት እንሻገራለን። ስለእዚህ አፍረትን አትፍሩ! በፍጹም እንዳትፈሩ! ነገር ግን ከእግዚአብሔር ምሕረት በፊት አሁንም አንድ መተው የሚገባን በር አለ። አንድን ነገር ለመተው አለመፈልግ ማለት የተዘጋ በር እንደ ማለት ነው። ይህም ደቀ-መዛሙርቱ በፋሲካ ምሽት የገጠማቸው ተመክሮ ሲሆን ሁሉም ነገር እነርሱ በጠበቀቱ መልኩ ባለማከናወናቸው ተስፋ ቆርጠው ወደ ቀድሞ ኑሮዋቸው ለመመለስ ፈለጉ። ተስፋ ቆርጠው በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፣ በሕይወታቸው ውስጥ የነበረው የኢየሱስ ምዕራፍ የተዘጋ መስሎዋቸው የነበረ ሲሆን ምንም እንኳን ከእርሱ ጋር ብዙ ጊዜ አስልፈው የነበረ ቢሆንም ቅሉ ይህ ቆይታ ምንም ነገር አልቀየረም ነበር፣ በእዚህም የተነሳ ወደ መጡበት ወደ ቅድሞ ሕይወታቸው መመለስ ፈለጉ። እኛም ራሳችን “ለብዙ ጊዜ ክርስቲያን ነበርኩኝ፣ ነገር ግን በሕይወቴ ውስጥ የተቀይረ ምንም ነገር የለም፣ ሁሌም ቢሆን ተመሳሳይ የሆነ ኃጢያት እሠራለሁ፣ ምንም ለውጥ የለም” ልንል እንችል ይሆናል። በእዚህም ተስፋ ቆርጠን ለእግዚኣብሔር ምሕረት የነበረን ተስፋ ይጨልማል። ነገር ግን በእዚህ ረገድ “የእኔ ምሕረት ከአንተ ኃጢያት እንደ ሚበልጥ አታምንምን? ተመለስ እና ይቅርታን ጠይቅ፣ ማን አሸናፊ ሆኖ እንደ ሚወጣ ይታያል! በማለት እግዚኣብሔር ራሱ ይጋፈጠናል። ምስጢረ ንስሓን የሚያዘወትር አንድ ሰው ይህንን በሚገባ ይረዳዋል፣ ሁሉም ነገር በነበረበበት እንደ ማይቀጥል ይረዳል። ምሕረትን በሚደርግልን ጊዜያት ሁሉ፣ እንበረታታለን፣ ምክንያቱም በየጊዜው የፍቅር ስሜት ይሰማናል፣ በእግዚኣብሔር አባታችን እቅፍ ውስጥ እንዳለን ይሰማናል። ተመልሰን በምንወድቅባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ይህም የተከሰተው በመወደዳችን ምክንያት እንደ ሆነ እንረዳለን፣ በእዚህም ምክንያት ይበልጡኑ የሐዘን ስሜት ያሰማናል፣ ይህም ሐዘን ቀስ በቀስ ከኃጢኣት እንድንላቀቅ ያደርገናል። ከእዚያም በኃላ ሕይወታችን የሚበረታው የእግዚኣብሔርን ምሕረት ስንቀበል ብቻ መሆኑን እና ከአንድ ምሕረርት ወደ ሌላ ምሕረት መጓዝ አስፈላጊ እንደ ሆነ እንረዳለን። መሆን ያለበትም ይህ ነው ልንክተለው የሚገባው ሂደት ከአፍረት ወደ አፍረት ከምሕረት ወደ ምሕረት መጓዝ ነው። ከአፍረት እና የቀድሞ የሕይወት መስመራችን መቀየር ቀጥሎ የሚመጣው ኃጢኣታችን ነው። እኔ አንድ ከባድ ኃጢኣት በምፈጽምበት ወቅት በታማኝነት ራሴን በራሴ ይቅር የማልል ከሆነ፣ ታዲያ እግዚኣብሔር እንዴት ይቅር ይለኛል? በእዚህ ረገድ ይህ በር የተቆለፈው በአንድ በኩል ብቻ ነው፣ ይሄውም በእኛ በኩል፣ ነገር ግን ለእግዚኣብሔር ሙሉ በሙሉ የተዘጋ በር ሊኖር አይችልም። በዛሬው እለት ቅዱስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው የተዘጋ በሚመስል በር ውስጥ ሳይቀር መግባት ይወዳል። ከእዚያም እግዚኣብሔር ድንቅ ነገሮችን ይፈጽማል። እርሱ እኛን ብቻችንን ለመተው በፍጹም አይፈልግም፣ እኛ ግን እርሱን ችላ እንለዋለን። ነገር ግን ምስጢረ ንስሓ በምንገባ ወቅት ከእርሱ ያለያየን ኃጢኣት ሁሉ ተወግዶ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት እንችላለን። በእዚያም ለእኛ ፍቅር ሲል የቆሰለው እኛን ለመገናኘት ይመጣል። የእኛን ቁስሎች ወደ እርሱ ክብር ወደ ተሞላው ቅስል ይቀይረዋል። የእኛ የተጎሳቆሉ ቁስሎች ወደ እርሱ በክብር የተሞላ ቁስል ይለወጣሉ።ምክንያቱም እርሱ ራሱ ምሕረት ስለሆነ የእኛን የተጎሳቆሉ ቁስሎች በምሕረቱ ይቀይረዋል። እንደ ቶማስ እውነትን ለማግኘት የሚያስችለንን ጸጋ ከእግዚኣብሔር እንጠይቅ፣ በእርሱ ምሕረት ደስታን እንድናገኝ፣ በእርሱ ምሕረት ተስፋችን እንዲለመልም እንደ ሐዋሪያው ቶምስ የእግዚኣብሔርን ጸጋ እንማጸን።”

08 April 2018, 15:13