ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴ ባስረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴ ባስረጉበት ወቅት   (ANSA)

ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት የተጻፈ አንድ ቃለ ምዳን በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ማብቃታቸው ተገለጸ።

ምሕረት የእግዚኣብሔር የልብ ምት ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት የተጻፈ አንድ ቃለ ምዳን በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ማብቃታቸው ተገለጸ። ይህ ቃለ ምዕዳን የመጥሪያ ስሙን ያገኘው በማቴዎስ ወንጌል 5፡12 ላይ በተጠቀሰው “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” ከሚለው የወንጌል ክፍል የተወስደ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ የሚያቅርብ ቃል ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በሚል አርእስት ቅዱስነታቸው በዛሬው ቀን በይፋ ለንባብ ያበቁት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በአምስት ምዕራፎች እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነም ለመረዳት ትችሉዋል።

ኢየሱስ በእርሱ ምክንያት የሚስደዱ እና የሚዋረዱ ሰዎችን በሙሉ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በማለት የማበረታቻ ቃል ተናግሮዋቸው እንደ ነበረ፣ እግዚኣብሔር ሁሉም ነገሮቻችን ወደ እርሱ እንድንመልስ ጥሪ እንደ ሚያቀርብልን እና በአንጻሩም እርሱ ለእኛ እውነተኛ የሆነ ሕይወት እንደ ሚሰጠን የሚያወሳ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ሲሆን ትክክለኛውን ደስታ የሚሰጠን እግዚኣብሔር ብቻ እንደ ሆነም በስፊው የሚያትት ቃለ ምዕዳን ነው። የቅድስና ሕይወት እንድንንሮ መጠራታችንን የሚገልጹ መልእክቶች እና ጥሪዎች ከመጽሐፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ገጽ አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ በስፊው መጥቀሱን የሚያትተው ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ’ የተሰኘው የቅድስነታቸው ቃለ ምዕዳን ይህም እግዚኣብሔር ራሱ ለአብርሃም ተገልጦለት እንደ ነበረ እና  “እኔ ኤልሻዳይ” ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ” በማለት እንደ ሚጀምር ያትታል።

ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በሚል አርእስት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተጽፎ በዛሬው እለት በይፋ ለንባብ የበቃው ቃለ ምዕዳን አሁን ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ የሚኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ ቅድስና ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ ከማድረጉ ባሻገር ወደ ቅድስና ሕይወት ለመመለስ የሚያስችሉ መንገዶችን በመጠቆም በእነሩሱ ላይ ማብራሪያ የሚሰጥ ቃለ ምዕዳን ሲሆን የተለያዩ ዓይነት የቅድስና መንገዶችን በመጠቆም በተለይም ደግሞ አሁን ባለንበት በእኛ ዘመን እግዚኣብሔር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና” በማለት ለሚይቀርብልን ጥሪ በቂ የሆነ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉንን መንገዶች የሚያመላክት ቃለ ምዕዳን እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። ይህ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ” በሚል አርእስት በቅዱስነታቸው ተጽፎ በዛሬው እለት በይፋ ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ቀድም ሲል እንደ ገለጽነው በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ እና 177 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ነው።

በምዕራፍ አንድ እግዚኣብሔር በአሁን ወቅት ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እግዚኣብሔር ለእነርሱ ስላቀረበው የቅድሳና ጥሪ ያመለክታል። በምዕራፍ ሁለት ላይ ደግሞ ሁለት ቀንደኛ የቅድስና ጠላቶችን ያትታል። በምዕራፍ 3  በጌታ ብርሃን እይታ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ተቀምጡዋል፣ በምዕራፍ 4 ላይ ደግሞ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ የሚታዩ የቅድስና ምልክቶች የሚል አርእስት የተሰጠው ሲሆን በአምስተኛው እና በመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ መንፈሳዊ ውጊይ ማድረግ፣ ነቅቶ መጥበቅ ኣና በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ይዞ ቀርቡዋል።

ቅዱስነታቸው በእዚህ በአምስት አመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን ሦስት ይህ አሁን “ደስ ይበላችሁም ሐሴትም አድርጉ” በሚል በዛሬው እለት ለንባብ ካበቁት ሐዋሪያው ቃለ ምዕዳን ጨምሮ በአጠቃላይ ሦስት ቃለ ምዕዳኖችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከእዚህ ቀደም የፍቅር ሐሴት በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ሀዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን የመጀመሪያው ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል በወንጌል የሚገኝ ደስታ የሚል ቃለ ምዕዳን አሁን ደግሞ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት ለንባብ የባቁት ቃለ ምዕዳን ደግሞ ሦስተኛው እንደ ሆነ ይታወቃል። 

09 April 2018, 14:33