ፈልግ

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳን “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳን  

ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ ክፍል ሦስት

ንዑስ አርእስት ሦስት፡ እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል ይህ “እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል” የሚለው ንዑስ አርእስት በስሩ 4 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ንዑስ አርእስት ነው።

ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ

(GAUDETE ET EXSULTATE)

ክፍል ሦስት

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳናቸው አምስት በአምስት ምዕራፎች እና በ177 አንቀጾች የተዋቀረ እንደ ሆነ ቀደም ስል መግለጻችን ያታወሳል። በእዚህም መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ለቅድስና የቀረበ ጥሪ በሚል አርእስት የቀረበ ሲሆን በሥሩ የሚከተሉትን ንዑስ አርእስቶች አቅፎ ይዙዋል።

 

ምዕራፍ አንድ

ለቅድስና የቀረበ ጥሪ

 

 

ንዑስ አርእስት ሦስት፡ እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል

ይህ “እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል” የሚለው ንዑስ አርእስት በስሩ 4 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ንዑስ አርእስት ነው። በአንቀጽ 10 ላይ ይህ ንዑስ አርእስት በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ በመግልጽ እግዚኣብሔር እያንዳንዳችንን በግለሰብ ደረጃ ማለት ነው “እኔ ቅዱስ እንደ ሆንኩኝ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” (1ጴጥሮስ 1:16) በማለት እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ጥሪ እንደ ሚያቅርብልን ያትታል።

በተጨማሪም ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰንደ ውስጥ እንደተጠቀሰው “ወደ ቅድስና እንድናመራ የሚያደርጉን በርካታ እና የተለያዩ መንገዶች እንዳሉ ስለምጠቅስ በእዚህ ሐሳብ በመበረታታት ሁሉም አማኞች የአኗኗር ዘይቤያቸው ምንም ይሁን ምን በጌታ ወደ ቅድስና የሚጠሩት እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ እንደ ሆነ የጠራቸው እግዚኣብሔር ቅዱስ እንደ ሆነ እነርሱም በየተጠሩበት መንገድ እንደርሱ ቅዱሳን እንደ ሚሆኑ ይገልጻል።

አንቀጽ 11 ላይ ቀደም ሲል በአንቀጽ 10 ላይ “እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ “ ወደ ቅድስና እግዚኣብሔር እንደ ሚጠራቸው የሚገልጸውን አንቀጽ በድጋሚ በመጥቀስ ቅድስና በፍጹም ሊደረስበት የማይችል አስቸጋር ጉዳይ አድርገን መቁጠር እንደ ሌለብን፣ በእዚህም የተነሳ ተስፋ መቁረጥ እንደ ሌለብን የሚመክር አንቀጽ ነው። አንዳንድ ከእዚህ ቀደም የነበሩት ቅዱስን የሰጡት ምስክርነት እኛ ወደ ወደ ቅድስና መንገድ እንድንራመድ ልያግዘንና ልያበረታታን ይችል ይሆናል፣ ይህ ማለት ግን እነርሱ የሰሩትን ነገሮች ሙሉ በሙሉ በመቅዳት (በመኮረጅ) መኖር  ያስፈልጋል ማለት እንዳልሆነ፣ ነገር ግን በተቃራኒው ይህንን በምናደርገበት ወቅት እግዚኣብሔር ለእያንዳንዳችን ካለው የደኽንነት እቅድ ውጭ እንድንጓዝ ልያደርገን ይችላል የሚል ጭብጥ የያዘ አንቀጽ ነው። በጣም አስፈላጊው ነገር እያንዳንዱ አማኝ የራሱን ወይም የራሷን መንገድ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ምርጫ በማድረግ መምረጥ እነ ሚገባቸው፣ የየራሳቸው መንገድ ምን እንደ ሆነ እንዲገነዘቡ፣ ከእነዚህ ወደ ቅድስና እንድንጓዝ ከሚያደጉን መንገዶች ውስጥ ምርጥ የሆነውን በመምረጥ፣ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያስቀመጠውን የግል ስጦታ በመጠቀም ራሳቸውን ማብቃት ይኖርባቸዋል የሚሉ ሐስተሳሰቦች የሚንጸባረቅበት አንቀጽ ነው።

ይህ እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል በሚል የምዕራፍ አንድ ንዑስ አርእስት 3 አንቀጽ 11 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በይበልጥ ለማብራራት በማሰብ ቅዱስነታቸው 1ቆሮንጦስ 12: 12-31 የተጠቀሰውን አንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉ የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጠቀሙ ሲሆን በተለይም ደግሞ በእዚሁ በ1ቆሮንጦስ 12፡17-20 ላይ ያለውን “ አካል በሙሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ፣ መስማት ከየት ይገኝ ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ፣ ማሽተት ከየት ይገኝ ነበር? ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቦአል። ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር? እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው” የሚለውን ጥቅስ በመጠቀም እያንዳንድችን አንድ አካል የሆነው እግዚኣብሔር እኛን ወደ ቅድስና የሚጠራው በተለያየ መነግድ እንደ ሆነ ይተነትናል። እኛ ሁላችንም ምስክሮች እንድንሆን ተጠርተናል ነገር ግን ምስክርነትን የምንሰጥባቸው ብዙ መንገዶች አሉ። መናኝ የነበረው ቅዱስ ዩሐንስ ዘ መስቀል ለተከታዮቹ ጠንካራ እና ፈታኝ የሆኑ  ህጎችን ከመደንገግ ለመቆጠብ ወሰነ። ስለዚህም ለተከታዮቹ ባወጣው ሕግጋት ላይ ሕጉን ሁሉም ሰው "በራሱ መንገድ እንዲጠቀም" አሳስቦ ነበር። የእግዚአብሔር ሕይወት "ለአንዳንዱ ሰው በተለያየ መነግድ እና ሁኔታ በመሰጠቱ” የተነሳ ቕግዚኣብሔር እያንዳንዱን ሰው ወደ ቅድስና የሚጠራው በተለያየ መንገድ እንደ ሆነ በስፋት የሚገል አንቀጽ ነው።

        

እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል በሚል ንዑስ አርእስት 3 ስር ማብቂያ ላይ የሚገኘው አንቀጽ 13 ላይ ይህ ከላይ የተጠቀሰው የቅድስና ጥሪ ሁላችንንም ለእርሱ እንድንሰጥ እና እግዚአብሔር ለዘለአለም ከእኛ የሚፈልገውን ያንን እቅድ እንዲድንይዝ እና እንድነመርት በማበረታታት “በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤ ከመወለድህ በፊት መረጥኩህ፤ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።” (ኤርሚያስ 1፡5 ) የተጠቀሰውን በማመልከት እግዚኣብሔር እያንዳንዳችንን ወደ ቅድስና የሚጠራን በተለያየ መነገድ እንደ ሆነ በስፋት ይገልጻል።

 

ንዑስ አርእስት አራት ቅድስና ለሁሉም ሰው የቀረበ ጥሪ እንደ ሆነ በሥሩ 5 አንቅጽ 14-18 ያሉትን አቅፎ የያዘ ነው።  በእነዚህ አንቅጾች ውስጥ ቅድስና ለጳጳሳት፣ ለካህናት ለገደማዊያን ገድማዊያት ብቻ የቀረበ ጥሪ አለምሆኑን፣ ብዙን ጊዜ ስለቅድስና ስናወራ ለየት ባለ ሁኔታ ለጸሎት በጣም ብዙ የሆነ ጊዜ የሚያውሉ ለተመረጡ ጥቂ ሰዎች ብቻ የሚቻል ነገር አድግረን እንደ ምናስብ የሚገልጽ ሲሆን ነገር ግን ሁላችን በፍቅር የተሞላ ሕይወት በመኖር፣ በምንሰራቸው እለትዊ ተግባራት ሁሉ መልካም የሚባሉ ነገሮችን በማከናወን የቅድስና ሕይወት መኖር እንደ ሚቻል በሰፊ የሚገልጽ አንቅጽ ነው። በጠቅላይ ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች እንደየኖሮዋቸው ሁኔታ በተቻለቸው መጠን እርስ በእርስ በመደጋገፍ ወደ ቅድስና መንገድ እንዲያመሩ ይጋብዛለ። ለየት ባለ ሁኔታ ራሳችሁን  ለቤተ ክርስትያን አግልግሎት የሰጣችሁ ሰዎች ከሆናችሁ፣ የገባችሁትን የአገልግሎት መኃላ በደስታ ተግባራዊ አድርጉ፣ በትዳር ሕይወት ውስጥ የምትኖሩ ሰዎች ከሆናችሁክርስትሶ ለቤተ ክርስትያኑ የሚያደርገውን ዓይነት እንክብካቤን በመመልከት እናንተም በባል እና በሚስት መካከል አንዱ ለአንዱ እንክብካቤን ማድረግ በፍቅር ለመኖር ሞክሩ፣ በሥራ ላይ የተሰማራችሁ ሰዎች ከሆናችሁ ባላችሁት ሙያ እና ክህሎት እህት ወንድሞቻችሁን አገልግሉ። ወላጆች ወይም አያቶች ከሆናችሁ ደግሞ በመካከላችሁ የተፈጠሩትን ሕጻናት ልጆች ክርስቶስን በመከተል ያድጉ ዘንድ በተዕግስ አስተምሩዋቸው። ባለስልጣን ከሆናችሁ ደግሞ የግል ጥቅሞቻችሁን ከማሳደድ ይልቅ ለማኅበራዊ አገልግሎት ራሳችሁን ዝግጁ በማድረግ በመልካም ስነ-ምግባር የታገዘ ኑሮ ኑሩ። እነዚህን እና እንዚህን የመሳሰሉ መልእክቶችን አቅፎ የያዘ አንቀጽ ነው።

በተጨማሪም በተጠመቅነበት ወቅት የተቀበልነውን ጸጋ ፍሬያማ እንዲሆን በማድረግ በቅድስና መንገድ እንድንራመድ የሚጋብዘን አንቅጽም ይገኝበታል።

ጌታ የሚያቅርብልንን የቅድስና ጥሪ መተገበር የምንጀምረው በእየእለቱ በምናደርጋቸው ትናንሽ ኣና መልካም ተግባሮች እንደ ሆነም ይገልጻል። ይህም እንደ ሀሜት ያሉትን ነገሮች በማስወገድ ለመትግበር ይችላላል። ለድኾች የተቻለንን በማድረግ መልካም የሚባሉ ቃላትን በመጠቀም. ። . ወዘት መተግባር እንደ ሚችላ ይገልጻል።

ንዑስ አርእስት 5 የእኛ ተልዕኮ በክርስቶስ ውስጥ መሆን እንደ ሚገባው የሚገልጽ ሲሆን በውስጡ ከአንቀጽ 19-24 አቅፎ የያዘ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው።

“የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው” የሚለው አንድ ክርስቲያን በምድር ላይ ያለውን ተልዕኮ ሊሆን የገባል። እያንዳንዱ ተልዕኮ ራሳችንን የምንመስክርበት ሳይሆን የወንገኢኣልን እሴቶች የምንመስክርበት ሊሆን እንደ ሚገባ፣ ኣያንዳንዱ መምንፈሳዊ ተልዕኮ ትክክለኛ ትጉሙን እና ምልኣት የሚያገኘው በክርስቶስ መሆኑን፣ ቅድስና የሚገኘው በክርስቶስ ምስጢር ውስጥ ራሳችንን ተስታፊ በማድርግ መሆኑን፣ በተለይም ደግሞ ክርስትሶስ ያሳየንን ፍቅር እናም ይህንን ፍቅር በመላበስ የፍቅር መሳሪያዎች ስንሆን ብቻ እንደ ሆነ የሚገልጹ አንቀጾች ተካተውበታል። በጠቃላይ በሕይወታችን ክርስቶስን ለዓለም መመስከር እንደ ሚገባ ያትታል።

ንዑስ አርእስት 6 እኛን ንጹሕን የሚያደርጉ ተግባራት በሚል አርእስት የቀረበ ሲሆን የህም ከአንቀጽ 25-31 አቅፎ የያዘ አንቀጽ ነው።

“ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል” (ማቴዎስ 6፡33) በማለት የሚጀምር አንቅጽ የሚገንበት እርእስት ሲሆን ከሁሉም ነገር በላይ በሕይወታችን ቅድሚያ ለእየሱስ መስጠት እንደ ሚገባ ይገልጻል። ይህንንም ማአረጋገጥ የምንችለው በፍትህ፣ በፍቅር ኣና በሰላም እንደ ሆነም ጨምሮ ይናገራል። በማኘውም ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በመሳተፍ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረ እንደ ሚገባን ይገልጻል። ሕይወት ምንም ዓይነት ተልዕኮ የለውም ሕይወት ራሱ ተልዕኮ ነውና በማለት ሕይወታችንን በተገቢው መልኩ መኖር እንደ ሚገባን ይገልጻል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ይህ ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤት አድርጉ” በምል አርእስት በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ የበቁትን ቃለ ምዕዳን ክፍል ሁለት ነበር። በነገው እለት ክፍል ሦስትን እናስደምጣችኃለን አብራችሁን በመሆን እንድተከታተሉን ከወዲሁ እናግዝባለን።

 

09 April 2018, 09:54