ፈልግ

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳን “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳን 

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” ክፍል አራት

ወደ ቅድስና እንድናመራ የሚያደርጉን በርካታ እና የተለያዩ መነግዶች አሉ

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ”

ክፍል አራት

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳን ቸው በአምስት በምዕራፎች እና በ177 አንቀጾች የተዋቀረ እንደ ሆነ ቀደም ስል መግለጻችን ይታወሳል። በእዚህም መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ለቅድስና የቀረበ ጥሪ በሚል አርእስት የቀረበ ሲሆን በሥሩ የሚከተሉትን ንዑስ አርእስቶች አቅፎ ይዙዋል።

 

ምዕራፍ አንድ

ለቅድስና የቀረበ ጥሪ

 

እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል

ይህ ንዑስ አርእስት 3 በስሩ 4 አንቀጾችን አቅፎ የያዘ ንዑስ አርእስት ነው።

ከአንቀጽ 10 ላይ ይህ ኑስ አርእስት በጣም አስፈላጊ ኣንደ ሆነ በመግልጽ እግዚኣብሔር እያንዳንዳችንን በግለሰብ ደረጃ ማለት ነው “እኔ ቅዱስ እንደ ሆንኩኝ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” (1ጴጥሮስ 1:16) በማለት እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ጥሪ እንደ ምያቅርብልን ያትታል። በተጨማሪም ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ሰንደ ውስጥ እንደተጠቀሰው “ወደ ቅድስና እንድንማረ የሚያደርጉን በርካታ እና የተለያዩ መነግዶች እንዳሉ ስለምጠቅስ በእዚህ ሐሳብ በመበረታታት ሁሉም አማኞች የአኑኗር ዘይቤያቸው ምንም ይሁን ምን በጌታ ወደ ቅድስና የሚጠሩት እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ እንደ ሆነ -የጠራቸው እግዚኣብሔር ቅዱስ እንደ ሆነ እነርሱም በየተጠሩበት መነግድ ከእርሱ ቅዱስ እንደ ሚሆኑ ይገልጻል።

አንቀጽ 11 ላይ ከደም ሲል በአንቀጽ 10 ላይ “እያንዳንዳቸው በየራሳቸው መንገድ “ ወደ ቅድስና እግዚኣብሔር እንደ ሚጠራቸው የሚገልጸውን አንቀጽ በድጋሚ በምጥቀስ ቅድስና በፍጹም ሊደረስበት የማይችል አስቸጋር ጉዳይ አድርገን መቁጠር እንደ ሌለብን በእዚህም የተነሳ ተስፋ መቁረጥ እንደ ሌለብን የሚመክር አንቀጽ ነው። አንዳንድ ከእዚህ ቀደም የነበሩት ቅዱስን የሰጡት ምስክርነት እኛ ወደ ወደ ቅድስና መንገድ እንድንራመድ ልያግዙን ኣና ልያበረታቱን ይችሉ ይሆናል፣ ይህ ማለት ግን እነርሱ የሰሩትን ነገሮች ሙሉ በሙሉ በመቅዳት በመኮረጅ መኖር  ያስፈልጋል ማለት እንዳልሆነ ነገር ግን በትቃራኒው ይህንን በምናደርገበት ወቅት እግዚኣብሔር ለእያንድናድችን ካለው የደኽንነት እቅድ ውጭ እንድንጓዝ ልያደርገን ይችላል የሚል ጭብጥ የያዘ አንቀጽ ነው። በጣም አስፈላጊው ነገር እያንዳንዱ አማኝ የራሱን ወይም የራሷን መንገድ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ምርጫ በማድረግ መምረጥ እነ ሚገባቸው፣ የየራሳቸው መንገድ ምን እንደ ሆነ እንዲገነዘቡ፣ ከእነዚህም ወደ ቅድስና እንድንጓዝ ከሚያደጉን መንገዶች ውስጥ ምርጥ የሆነውን በመምረጥ፣ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያስቀመጠውን የግል ስጦታ በመጠቀም ራሳቸውን ማብቃት ይኖርባቸዋል የሚል ሐስተሳሰብ የሚንጸባረቅበት አንቀጽ ነው። ይህ እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል በሚል የምዕራፍ አንድ ንዑስ አርእስት 3 አንቀጽ 11 ላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ በይበልጥ ለማብራራት በማሰብ ቅዱስነታቸው 1ቆሮንጦስ 12: 12-31 የተጠቀሰውን አንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉ የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጠቀሙ ሲሆን በተለይም ደግሞ በእዚሁ በ1ቆሮንጦስ 12፡17-20 ላይ ያለውን “ አካል በሙሉ ዐይን ቢሆን ኖሮ፣ መስማት ከየት ይገኝ ነበር? አካል በሙሉ ጆሮ ቢሆን ኖሮ፣ ማሽተት ከየት ይገኝ ነበር? ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ እያንዳንዱን በየቦታው መድቦአል። ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር? እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው” የሚለውን ጥቅስ በመጠቀም እያንዳንድችን አንድ አካል የሆነው እግዚኣብሔር እኛን ወደ ቅድስና የሚጠራው በተለያየ መነግድ እንደ ሆነ ይተነትናል። እኛ ሁላችንም ምስክሮች እንድንሆን ተጠርተናል ነገር ግን ምስክርነትን የምንሰጥባቸው ብዙ መንገዶች አሉ። መናኝ የነበረው ቅዱስ ዩሐንስ ዘ መስቀል ለተከታዮቹ ጠንካራ እና ፈታኝ የሆኑ  ህጎችን ከመደንገግ ለመቆጠብ ወሰነ። ስለዚህም ለተከታዮቹ ባወጣው ሕግጋት ላይ ሕጉን ሁሉም ሰው "በራሱ መንገድ እንዲጠቀም" አሳስቦ ነበር። የእግዚአብሔር ሕይወት "ለአንዳንዱ ሰው በተለያየ መነግድ እና ሁኔታ በመሰጠቱ” የተነሳ እግዚኣብሔር እያንዳንዱን ሰው ወደ ቅድስና የሚጠራው በተለያየ መንገድ እንደ ሆነ በስፋት የሚገል አንቀጽ ነው።

 እግዚኣብሔር ሁሉንም ይጠራል በሚል ንዑስ አርእስት 3 ስር ማብቂያ ላይ የሚገኘው አንቀጽ 13 ላይ ይህ ከላይ የተጠቀሰው የቅድስና ጥሪ ሁላችንንም ለእርሱ እንድንሰጥ እና እግዚአብሔር ለዘለአለም ከእኛ የሚፈልገውን ያንን እቅድ እንዲድንይዝ እና እንድነመርት በማበረታታት “በማሕፀን ሳልሠራህ ዐወቅሁህ፤ ከመወለድህ በፊት መረጥኩህ፤ለሕዝቦችም ነቢይ እንድትሆን ሾምሁህ።” (ኤርሚያስ 1፡5 ) የተጠቀሰውን በማመልከት እግዚኣብሔር እያንዳንዳችንን ወደ ቅድስና የሚጠራን በተለያየ መነገድ እንደ ሆነ በስፋት ይገልጻል።

09 April 2018, 10:01