ፈልግ

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳናቸው “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳናቸው  

ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ ክፍል ሁለት

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳናቸው በአምስት በምዕራፎች እና በ177 አንቀጾች የተዋቀረ ነው

ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ

ክፍል ሁለት

“ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በምል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ለንባብ ያበቁት ሦስተኛው ቃለ ምዕዳናቸው በአምስት በምዕራፎች እና በ177 አንቀጾች የተዋቀረ እንደ ሆነ ቀደም ስል መግለጻችን ይታወሳል። በእዚህም መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ለቅድስና የቀረበ ጥሪ በሚል አርእስት የቀረበ ሲሆን በሥሩ የሚከተሉትን ንዑስ አርእስቶች አቅፎ ይዙዋል።

 

ምዕራፍ አንድ

ለቅድስና የቀረበ ጥሪ

 

የምያበረታቱን እና አብረውን የምጓዙ ቅዱሳን አብረውን አሉ።

3.ወደ ዕብራውያን የተጻፈው መልዕክት "ከፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጡ" (12:1) በማለት በርካታ ምስክርነቶችን ያቀርብልናል። በእዚህም የመጻሐፍ ቅድሱ ክፍል ላይ ስለአብራሃም፣ ስለሳራ፣ ስለሙሴ፣ ስለጌዲዮን እና ስለሌሎችም ይናገራል (ዕብራዊያን 11:1-12:3)። ከሁሉም በላይ ደግሞ  "እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን አሉን” (ዕብራዊያን 12:1) በማለት ይህንን እንድንገነዘብ በመጋበዝ ያለማቋረጥ ወደ ግባችን መጓዝ እንደ ሚኖርብን ይነግረናል። ይህ ምስክርነት ደግሞ እናቶቻችንን፣ አያቶቻችንን ወይም ደግሞ ወዳጆቻችንን ልያጠቃልል ይችል ይሆናል (2ጢሞ. 1:5)። ሕይወታቸው ሁልጊዜ ፍፁም የሆነ ሕይወት ላይሆን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን ከወድቀቶቻቸው እና ከስህተቶቻቸው ጋር ሳይቀር እንኳን ወደፊት እየገሰገሱ ጌታን ደስ አሰኝተውት ነበር።

4. አሁን በእግዚአብሔር ፊት የሚገኙት ቅዱስን ከእኛ ጋር ያላቸውን የፍቅር ቁርኝት እና ሕብረት አሁንም ቢሆን ጠብቀውት ይገኛሉ። የዩሐንስ ራዕይ ስለ ሰማዕታት ምልጃ ሲናገር እንዲህ ይላል “ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁትም ምስክርነት የታረዱትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ። እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? አሉ (ራዕይ 6:9-10)። እያንዳንዳችን "በእግዚአብሔር ወዳጆች ተከበን” እንዲህ ልንል እንችላለን: እኔ ብቻዬን ይህንን ለመሸከም አልችልም፣ በእውነት ብቻዬን ለመሸከም አልችልም ለማለት እንችል ይሆናል። ሁሉም የእግዚኣብሔር ቅዱሳን እኔን ለመጠበቅ፣ እኔን ለማበርታትት እና ለመሸከም ዝግጁዎች ናቸው።

 

ቅዱሳን ለእኛ ቅርቦች ናቸው

6. ስለቅዱሳን ስናስብ የብጽዕና ወይም የቅድስና ማዕረግ ስለተሰጣቸው ሰዎች ብቻ ማሰብ የለብንም። መንፈስ ቅዱስ በቅዱስና በታማኝ ሕዝቦች ላይ ቅድስናን በብዛት ያጎናጽፋል ምክንያቱም "የሰው ልጆችን ማዳን እግዚኣብሔርን የምያስደስተው ነገር በመሆኑ የተነሳ” እንደ ሆነ በመጥቀስ ነገር ግን ይህንን የሚያደርገው በተናጥል በግለሰቦች መካከል ምንም ዓይነት ቁርኝት ወይም ትስስር እንደ ሌለ አድርጎ ሳይሆን ነገር ግን እርሱን በእውነት እና በቅድስና ያገለገሉ ሰዎችን ሁሉ ያጠቃለለ እንደ ሆነ ይገልጻል። በድኽንነት ታሪክ ውስጥ እግዚኣብሔር አንድ ግለሰብ ሳሆን ያዳነው ነገር ግን አንድ ሕዝብ እንዳዳነ ይገልጻል። እኛ የአንድ ሕዝብ አካል እስካልሆኑ ድረስ እኛ ሙሉ በሙሉ እራሳችንን አይደለንም። ለዚህ ነው ማንም ብቻውን መዳን አይችልም በግለሰብ ደረጃ ተነጥሎ ብቻውን መዳን አይችልም። ከእዚህ ይልቅ እግዚኣብሔር ሰዎችን ወደ ራሱ የምያቀርባቸው ወይም የሚስባቸው ማኅበረሰብ ውስጥ ሰዎች የምያደርጉትን ውስብስብ የሰው ለሰው ግንኙነት ላይ መሰረቱን ይደርገ ሲሆን በእዚህም እግዚኣብሔር በሰዎች ሕይወት እና ታሪክ ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል የሚል ሐሳብ የሚንጸባረቅበት ክፍል ነው።

7. በእግዚአብሔር ሕዝብ ጽናት ወይም ትዕግስት ውስጥ ስለሚንጸባረቀው የቅድስና ሕይወት በማመልከት ይህንንም በይበልጥ ለማስረዳት በማሰብ በታላቅ ትዕግስት እና ጥልቅ በሆነ ፍቅር ተሞለተው ልጆቻቸውን ስለሚያሳድጉ ወላጆች፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ለመደጎም፣ ቀን ከሌሊት የሚለፉ የሚኳትኑ፣ የሚሰሩ ወንድ እና ሴቶችን፣ በማያቋርጥ ፈገግታ  በሕመም የሚሰቃዩ ሰዎችን እና አረጋዊያንን የምንከባከቡ ገዳማዊያንን መመልከት ይቻላል። እነዚህን ሁኔታዎ በምንመለከትበት ወቅት ቤተክርስትያን ለቅድስና የሚዋጉ ተዋጊዎች እንዳሉዋት ይሰማኛል በማለት በእዚሁ “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በተሰኘው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ውስጥ የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ብዙን ጊዜ ቅድስና ከእኛ በጣም ርቆ የምገኝ ነገር አድርገን እንቆጥራል ነገር ግን ቅድስና ለእኛ በጣም ቅርብ የሆነ እና በበራችን ላይ የሚገኝ  እንደ ሆነ ጠቅሰው ይህንን እውነታ ጎረቤቶቻችን ከሆኑ እና በመካከላችን ከሚኖር ብዙ መልካም እና ደጋግ ሰዎች ስንመለከት የእግዚኣብሔርን በእዛ መኖር እንረዳለን “በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ቅዱሳን” ወይም ደግሞ የእዚህን ዓይነት ተግባራት የሚፈጹም ሕዝቦችን ያማከለ ቅድስና እንደ ሆነ የሚገልጽ የሐዋሪያው ቃለ ምዕዳን ክፍል ነው።

ማሳሰቢያ፡ ክቡራን የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ይህ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁ “ደስ ይበላችሁ ሐሴት አድርጉ” በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 01/2010 ዓ.ም. ካሳተሙት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን የወስድነው ሲሆን ይህ ቀደም ሲል ያነበባችሁት ትርጉም ይፋዊ እና ቃል በቃል የተተረጎመ ሳይሆን ጠቅለል ባለ ሁኔታ የእዚህን ቃለ ምዕዳን አጠቃላይ ጽንሰ-ሐሳብ በመረዳት ሲሆን በእዚህም መሰረት ስለዝህ ቃለ ምዕዳን ጥቅላላ ይዘት መረጃ ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

 

 

09 April 2018, 09:44