ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ያስተላለፉት ጥሪ

የደቡብ እና የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየታቸው በጣም ጠቃሚ እና ገንቢ ነው።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ ከሚለው ጸሎት በመቀጠል ያስተላለፉት ጥሪ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 21/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መስረቱን አድርጎ የነበረ አስተንትኖ ካደረጉ በኃላ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከሚቀርቡት የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን እና በፋሲካ በዓል ሰሞን ባሉ ቀናት ውስጥ የሚደገመውን “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበለሽ፣ እንደ ተናግረው ከሙታን ተነስቱዋልና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኃላ ለመላው ዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት ሀና ሕሻኖስካ የተባለች ምዕመን ባለፈው ቅዳሜ በፖላንድ ዋና ከተማ ክራኮው  የብጽዕና ማዕረግ የተሰጣት መሆኑን መግለጻቸው የታወቀ ሲሆን ብጽዕት ሀና ሂሻኖስካ በሕይወት ዘመናቸው በሽተኞችን በመንከባከብ በበሽተኞች ውስጥ ሆኖ የሚሰቃየውን ኢየሱስን በበሽተኞች አማክይነት አገልግለው በማለፋቸው የተሰጣቸው ምዕረግ እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል። የታመሙትን ሰዎች በመንከባከብ የጌታ ደቀ- መዝሙር በመሆን ምስክርነት በመስጠታቸው እና እርሳቸው ያሳዩትን መልካም አብነት እንድንከተል እርሳቸውን በአብነት የሰጠንን እግዚኣብሔርን እናመስግናለን ማለታቸው ተገልጹዋል።

ባለፈው ዐርብ ሁለቱም ማለትም የደቡብ እና የሰሜን ኮሪያ መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየታቸው፣ በሁለቱ ሀገሮች መሪዎች የጋራ ጥረት የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች ተገናኝተው ባደርጉት ገንቢ እና ታሪካዊ ውይይት በኮሪያ ልሳነ ምድር ከኒውክለር መሳሪያ ነጻ የሆነ ቀጠና ለመመስረት መግባባት ላይ በመድረሳቸው ታላቅ እምርታ መሆኑን በመግለጽ ስምምነቱን አወድሰዋል። በቀጣይነትም በሁለቱ ሀገራት ማለትም በደቡብ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል የወንድማማችነት መንፈስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን ተስፋ በማድረግ ወደ እግዚኣብሔር ጸሎታቸውን እንደ ሚያቀርቡ ገልጸው በሁለቱ ሀገራት መካከል መልካም ጉርብትና እናዲፈጥር እና ብሎም ለዓለም ሁሉ ሰላም እንዲሆን የሚረዳ ጥረት በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምኞታቸው እና ጸሎታቸው እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በናይጄሪያ በክርስቲያኖች ላይ የሚቃጣው ጥቃት በአዲስ መልክ መጀመሩ ስጋትን እንደ ፈጠረባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ መስዋዕተ ቅዳሴ በማቅረብ ላይ የነበሩ ሁለት የካቶሊክ ካህናት ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው የሚያሳዝን ተግባር መሆኑን በመልእክታቸው ያወሱት ቅዱስነታቸው የእነዚህን ካህናት ነብስ መሐሪ ለሆነ ለእግዚኣብሔር በአደራ እናስረክባለን ካሉ በኃላ የእዚህ ጥቃት ሰለባ የሆነው ማኅበርሰብ መጽናናትን እና ሰላምን ያገኝ ዘንድ እግዚኣብሔር እንዲረዳቸው ተመጽነዋል።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 1/2018 ዓ.ም. (በኢትዮጲያ የቀን አቆጣጠር በሚያዝያ 23/2010 ዓ.ም ማለት ነው) የሚጀመረው የግንቦት ወር የማሪያም ወር በመባል እንደ ሚጠራ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ወር የመጀመሪያ ቀን ከሰዓት በኃላ በሮም ከተማ አቅራቢይ ወደ ሚገኘው በጣሊያነኛው “ዲቪና አሞሬ” በአማሪኛ መለኮታዊ ፍቅር በመባል ወደ ሚታወቀው የጸሎት ስፍራ ንግደት እንደ ሚደረግ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። በውቅቱም በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለማሪያም ከሚደርጉት የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የሆነው የመቁጠሪያ ጸሎት እንደ ሚደገም፣ ለሰላም በተለይም ለሶሪያ እና በአጠቃላይ በመላው ዓለማችን ሰላም ይወርድ ዘንድ የመማጸኛ ጸሎት እንደ ሚደርግ ገልጸው ሁላችሁም በያላችሁበት በመንፈስ ከእኛ ጋር በጸሎት በመሆን የማሪያም ወር ተብሎ በሚታወቀው በግንቦት ወር ውስጥ በሚደርገው የመቁጠሪያ ጸሎት በንቃት በመሳተፍ ለዓለማችን ሰላም መጸለይ ያስፈልጋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ማጠቃለያ ላይ “ለሁላችሁም መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ” ካሉ በኃላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ብለው ሐዋሪያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መሰናበታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። 

 

29 April 2018, 10:18