ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ የሐዋርያት ምስክርነት የጀመረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳሄ በኃላ ነው።
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ የሐዋርያት ምስክርነት የጀመረው ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳሄ በኃላ ነው።
ከኅዳር 29/2008 ዓ.ም እስከ ኅዳር 4/2009 ዓ.ም ድረስ (ለ349 ቀናት ያህል ማለት ነው) በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የታወጀው እና በመላው ዓለም በምገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያንት ዘንድ ቅዱስ ልዩ የምህረት አመት ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል።
በኅዳር 11/2009 ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በይፋ ሲጠናቀቅ የምሕረት ተግባራችንም በዚያ የሚጠናቀቁ አለመሆኑን በወቅቱ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይልቁኑም መላው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመን አካላዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን በምዕመናን ልብ ውስጥ በዘላቂነት ታትመው እስከ ሕይወታቸው ፋጻሜ ድረስ ከእነርሱ ጋር በመዝለቅ መፈሳዊ ገዴታችንን በምገባ እንድንወጣና በማቴዎስ ወንጌል 25.31-40 ላይ እንደ ተጠቀሰው በመጨረሻ የፍርድ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምያቀርብልን ጥያቄ በብቃት መልስ እንድንሰጥ የምያስችለን ክርስትያናዊ ስንቆቻችን ሆነው ከእኛ ጋር እስከ መጨረሻው መዝለቅ ይገባቸዋል ማለተቻው ይታወሳል። በእነዚህ ለ349 ቀናት ያህል በቆዩት ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት “የምሕረት ልዑካን” የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው እና ከመላው የዓለማችን ክፍሎች የተውጣጡ 1000 የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ካህናትን ያቀፈው ልዩ የምሕረት ልዑኽ በቅዱስነታቸው መቋቋሙ የምታወቅ ስሆን እነዚህም ካህናት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተቀበሉት ምስጢረ ንስሐን እና ከምስጢረ ንስሓ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መነፍሳዊ አገልግሎቶች በመስጠት የኃጢኣት ስርዬት የመስጠት ልዩ መንፈሳዊ መብት ተጠቅመው በመላው ዓለም በመጓዝ የምሕረት ተግባርትን ስያከናውኑ ቆይተዋል።
እነዚህ በቁጥር 1000 የሚሆኑ “የምሕረት ልዑካን” የተሰጣቸውን መንፈሳዊ ተልዕኮ አጠናቀው ወደ ሮም ከተማ ተመልሰዋል። በሚያዝያ 02/2010 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ተገኝተው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት የተካሄደውን መስዋዕተ ቅዳሴ መታደማቸው ተገልጹዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት እንደ ሚከተለው አስናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።