ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢየሱስ አማካይነት በጽሎት ወደ አብ መቅረብ እንችላለንአሉ!

ዛሬ ግንቦት 02/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባለፉት ቅርብ ቀናት ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከናውኑት ሁለት አብይት ተግብራት የታሰቡበትን ዕለት በማስታወስ ጸሎት ያደረጉ ሲሆን እነዚህ መታሰቢያዎች ትላንት ማለትም ግንቦት 01/2012 ዓ.ም የተከበረው የአውሮፓ ቀን በዓል እና በቅርቡ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ አስመልክቶ የተከበረውን የመታሰቢያ ቀን በማስታወስ ይህ እድሜ ጠገብ የሆነ የአውሮፓ አህጉር ውስጥ አንድነት እና ህብረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጸሎት ማደረጋቸው ተገልጿል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት ጸሎት ወደ አብ የሚያደርስ መንገድ መሆኑን የተናገሩት ቅዱስነታቸው አንድ ሰው ለመጸለይ እና በጸሎት ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ለማመን የሚያስችል ድፍረት ሊኖረው ይገባል ብለዋል።

የቫቲካን ዜና

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ አምስተኛው  የፋሲካ ሳምንት እሑድ እለት ላይ በተዘጋጀው የዕለቱ ሥርዓተ አምልኮ ላይ መሰረቱን ያደረገ ነበር፣ በመስዋዕተ ቅዳሴው መግቢያ ላይ ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል እንደ ገለጽነው የጸሎት ሐሳባቸውን በአውሮፓ አህጉር ላይ በማደረግ እና የሚከተለውን በመናገር ነበር . . .

በእነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ሁለት መታሰቢያዎችን አክብረናል-የአውሮፓ ህብረት ምሥረታ ጥንሥሥ የጀመረው የሮበርት ሹማን መግለጫ ይፋ የሆነበት 70 ኛ ዓመት እና እንዲሁም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱ የሚታሰብበት ቀናት ናቸው። ዛሬ ሁሉም ህዝቦች በልዩነት መካከል አንድነት በመፍጠር በጋራ እንዲያድጉ፣ ይህ በወንድማማችነት መንፈስ የተፈጠረው አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጌታ እንዲረዳን እንማጸናለን።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ያደረጉት ስብከት በጸሎት ላይ ያተኮረ ነበር። እርሳቸውም በእለቱ ያደረጉት ስብከት ከዩሐንስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው በሚከተለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ ነበር። እንዲህም ይላል “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ  ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። እኔ ወደምሄድበትም ስፍራ የሚያደርሰውን መንገድ ታውቃላችሁ። መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።  እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።” (ዮሐ 14፡1-12) በሚለው እና ኢየሱስ ወደ አብ የሚያደርሰው መንገድ እርሱ እንደ ሆነ በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ምሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሲናገሩ ይህ ቅዱስ ውንጌል ክፍል ወደ አብ የሚያደርስ መንገድ የተኛው እንደ ሆነ የሚገልጽ እንደ ሆነ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው አብ ሁልጊዜ ይንከባከበኛል ብሎ በተናገረው በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ አብ ሁል ጊዜ ይገኛል ብለዋል። “ኢየሱስ በፀሎት ሁሉን ቻይ የሆነውን አብ በሮች እንደሚከፍት ያሳያል፣  ሁሉንም ነገር ማድረግ በሚችለው በአብ ላይ ይተማመናል፣  መጸለይ ድፍረትን ይጠይቃል ፣ ለመስበክም ተመሳሳይ ድፍረትን ይጠይቃል” ብለዋል። አብርሃምን ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት "መደራደር" እንደሚችል ያውቅ ነበር። ሙሴም እንዲሁ በብርታት አድርጎ ነበር።  መጸለይ ከእግዚአብሔር ጋር መታገል ማለት ነው - መጸለይ ማለት ሁሉንም ነገር ወደሚሰጥ ወደ አብ ከኢየሱስ ጋር መሄድ ማለት ነው ብለዋል።

10 May 2020, 10:00
ሁሉንም ያንብቡ >