ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጸሎት አደረጉ

ዛሬ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እግዚአብሔር ይባርካቸው ዘንድ ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ኪነ-ጥበብ ውበትን ያሳየናል ያለ ውበት ደግሞ ቅዱስ ወንጌልን በሚገባ ልንረዳ አንችልም ብለዋል።

የቫቲካን ዜና

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ አሁን በምንገኝበት ወቅት አራተኛው የፋሲካ ሳምንት ሐሙስ ቀን ቅዱስነታቸው ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ የጀመሩት በሥርዓተ አምልኮ መግቢያ ላይ ለኪነ-ጥበብ ሰዎች የሚከተለውን ጸሎት በማደረግ ነበር. . .

ትናንት (ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም) ከአንድ የኪነ-ጥበብ ቡድን አንድ ደብዳቤ ደረሶኝ ነበር፣ ለእነሱ ጸሎት በማድረጋችን ተደስተው አመስግነውናል። ውበት ምን ማለት እንደሆነ እና ያለ ውበት ደግሞ ቅዱስ ወንጌልን መረዳት ስለማንችል በእዚህም ምክንያት እነርሱ በሥራቸው ስለ ውበት እንድንረዳ ስለሚያደርጉን ጌታ እንዲባርካቸው እንጸልይላቸው። በድጋሚ ለኪነ -ጥበብ ሰዎች እንጸልይላቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያደረጉት ስብከት በሚከተለው የዕለቱ የመጀመርያ ምንባብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር . . .

“ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጳፉ ተነሥተው በጲስድያ ውስጥ ወዳለችው ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ በሰንበት ቀንም ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ። የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ሕዝቡን የሚመክር ቃል ካላችሁ ተናገሩ” ሲሉ ላኩባቸው። ጳውሎስም ተነሥቶ በእጁ በመጥቀስ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ደግሞም እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ አድምጡ። የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ፣ አባቶቻችንን መረጣቸው፤ በግብፅ ምድር እያሉም ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ በኀያል ክንዱም ከዚያ አወጣቸው። አርባ ዓመት ያህልም በበረሓ ታገሣቸው፤ በከነዓን ምድር የነበሩትንም ሰባት መንግሥታት አጥፍቶ፣ ምድራቸውን ለገዛ ሕዝቡ ርስት አድርጎ አወረሳቸው። ዳዊትን አነገሠላቸው፤ ስለ እርሱም፣ ‘እንደ ልቤ የሆነና እኔ የምሻውን ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ሲል መሰከረለት። እግዚአብሔርም በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ። ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ንስሓ ገብተው እንዲጠመቁ ሰብኮላቸው ነበር። ዮሐንስ ተልእኮውን በማጠናቀቅ ላይ ሳለ፣ ‘እኔ ማን መሰልኋችሁ? እኔ እኮ እርሱ አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግሩን ጫማ እንኳ መፍታት የማይገባ ከእኔ በኋላ ይመጣል’ ይል ነበር። “እናንት ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ ወንድሞች፤ ደግሞም በመካከላችሁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፤ ይህ የድነት መልእክት የተላከው ለሁላችንም ነው” (ሐዋ. 13፡13-25)።

ቅዱስነታቸው በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ባደረገው ስብከት አንደ ገለጹት ሐዋርያው  ጳውሎስ በምኩራብ ውስጥ የእስራኤልን ሕዝብ ታሪክ ሲያስረዳ ኢየሱስ የተጠበቀው አዳኝ መሆኑን በማወጅ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል .. .

ሐዋርያው ጳውሎስ አዲሱን አስተምህሮ ሲያብራራ ስለ ደህንነት ታሪክ ተናግሯል። ከኢየሱስ ጀርባ የፀጋ፣የመመረጥ፣ የተስፋ ታሪክ አለ -እግዚአብሔር አብርሃምን መርጦ ከህዝቡ ጋር አብሮ ይጓዝ ነበር። ከህዝቡ ጋር የእግዚአብሔር ታሪክ አለ። ሐዋርያው ጳውሎስ አስተምህሮውን የጀመረው ከኢየሱስ አይደለም፣ ነገር ግን ከታሪክ ይጀምራል። ክርስትና የእምነት አስተምህሮ ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን ወደዚህ የእመነት ትምህርት የሚመራ ታሪክን ያካትታል። ክርስትና ሥነ-ምግባር ብቻ አይደለም ፣ የሥነ-ምግባር መርሆዎችም አሉት ፣ እኛ  ክርስቲያኖች ግን የምንመለከተው ሥነ-ምግባራዊ እይታዎችን ብቻ አይደለንም፤ ከእዚያም ባሻገር እንሄዳለን። ክርስቲያኖች ለእውነት ለመመስከር የተመረጡ ምሑራን አይደሉም፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይህ የቅንጦት አስተሳሰብ ይንጸባረቃል፣ ክርስቲያን መሆን ማለት በነጻ የተመረጠ እግዚአብሔር ሕዝብ አባል መሆን ማለት ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባል የመሆን ፍላጎት የሌለን ከሆነ ትንሽዬ የእመንት አስተምህሮ እና ትንሽዬ ሥነ ምግባር ያነገብን ርዕዮተ-ዓለማዊ በሆነ መልኩ ክርስቲያኖች እንሆናለን፣ ሌሎች ተጥለው ወደ ገሃነም እንደሚሄዱ የሚያምኑ ክርስትያኖች እንሆናለን። እውነተኛ ክርስቲያኖች አንሆንም። ብዙ ጊዜ በእነዚህ ክፍፍሎች ውስጥ እንወድቃለን-የቅንጦት ልኬቱ በጣም የሚጎዳ እና የቅዱሱ ታማኝ የእግዚአብሔር ህዝብ የመሆንን ስሜት እናጣለን። ታማኝ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባል መሆን አለብን። የመዳን ታሪካችንን እና ማህደረ ትውስታችንን ለሰዎች ማሰራጨት አለብን። በጣም አደገኛ የሆነው የክርስትና እምነት የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ አባል መሆናችንን መዘንጋት ነው። እኛ በጠቅላላው እምነት ያለን የቅዱሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ አባል መሆናችንን መዘንጋት የለብንም”።

07 May 2020, 09:25
ሁሉንም ያንብቡ >