ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ ስለ እያንዳንዳችን ይጸልያል” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 15/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እየተከሰቱ የሚገኙትን ችግሮች እና አጋጣሚዎች በመጠቀም ከሁኔታው ትርፍ ለማጋበስ ለሚጥሩ ሰዎች ከእዚህ ነውር ከሆነ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ጸሎት ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ምዕመናን ለእኛ በመጸልይ ላይ በሚገኘው ኢየሱስ ማመን እንዲቀጥሉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ሐሳባቸውን በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መከራ ለደረሰባቸው ብዙ ሰዎች ላይ አድርገው ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “በብዙ ቦታዎች ይህ ወረርሽኝ ከሚያስከትላቸው መዘዞች አንዱ ብዙ ቤተሰቦች ራሳቸውን ችለው መኖር እንዲያቅታቸው እና ለራብ እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል” በማለት በመስዋዕተ ቅዳሴው መግቢያ ላይ የተናገሩት ቅዱስነታቸው አለመታደል ሆኖ በእዚህ አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ሁኔታውን ተጠቅመው ትርፍ ለማጋበስ የሚጥሩ ብዙ ሰዎች  እንደ ሚገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

“ይህ ተግባር ሌላ ወረርሽኝ ፣ ሌላ ቫይረስ ነው - ይህ ማህበራዊ ወረርሽኝ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት ሥራ የሌላቸው እና በቤቶቻቸው ውስጥ በሚገኘው ጠረጴዛዎች ላይ ለልጆቻቸው የሚሆን የሚያስቀምጡት ምግብ የሌላቸውን ብዙ ቤተሰቦች አጋጣሚውን ተጠቅመው ለመዘረፍ ለሚጥሩ ሰዎች ከእዚህ ነውር ከሆነ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ ልንጸልይላቸው ይገባል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለእነዚህ ቤተሰቦች እና ለክብራቸው እንጸልይ ፣ እናም አጋጣሚውን ተጠቅመው ለመዝረፍ የተዘጋጁ ሰዎችን ልብ እግዚአብሔር እንዲነካ እና እንዲቀይር እንጸልይ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያደረጉት ስብከት በወቅቱ (ሐዋ. 5 27-33) ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በሚገኘው “ሐዋርያትንም አምጥተው በሸንጎው ፊት አቆሟቸው፤ ሊቀ ካህናቱም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ ደግሞም እኛን ለዚህ ሰው ደም ተጠያቂዎች ልታደርጉን ቈርጣችሁ ተነሣችሁ።” ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያትም መልሰው እንዲህ አሉ፤ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል! እናንተ በዕንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን፣ የአባቶቻችን አምላክ ከሙታን አስነሣው፤ እርሱም ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአትን ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ እግዚአብሔር የሁሉ ራስና አዳኝ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው። እኛም ለእነዚህ ነገሮች ምስክር ነን፤ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው።” ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ክፉኛ ተቈጡ፤ ሊገድሏቸውም ፈለጉ” በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ተገልጹዏል።

የጴጥሮስ ድፍረት

የመጀመሪው ንባብ እንደሚናገረው ሐዋርያቱ በሸንጎ ፊት እንዲቆሙ በወታደሮች ሲወሰዱ እና ሊቀ ካህናቱ “በኢየሱስ ስም ማስተማራችሁን እንድታቆሙ ጥብቅ የሆነ መመሪያ ሰጥተናችሁ አልነበረምን?” በማለት ሐዋርያቱን ያፋጠጧችወ ሲሆን ሆኖም “እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ እዲሆን እያድረጋችሁ ትገኛላችሁ” በማለት እንደ ከሰሷቸው ቅዱስነታቸው አክለው ገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ሐዋሪያት በተለይም ጴጥሮስ “ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይሻላል” የሚለውን በውስጡ ያለውን እምነት በድፍረትና በብርታት መግለጹን ያወሱት ቅዱስነታቸው እኛ እግዚአብሔርን እንታዘዛለን እናተ ግን ጥፋተኞች ናችሁ ብሎ እንደ መለሰ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጴጥሮስ ከእዚህ ቀደም “በፍርሃት ተሞልቶ ኢየሱስን የካደው ሰው ነበር” በማላት የተናገሩ ሲሆን አሁን ግን ደፋት እንዲሆን ያደረገው እና "እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደረስ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህንን ሐሳባቸውን ሲያብራሩ ጴጥሮስ በሰላማዊ መንገድ ከሰዎች ጋር ለመኖር ያስችለው ዘንድ አቋሙን ማስተካከል ይችል እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ነገር ግን ድፍረትን እና ብርታትን ያሳየበትን ጉዞ ለመጀመር መርጠዋል፣ “በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ፣ የቤተክርስቲያኗ ምዕመን የእግዚአብሔርን ህዝብ ለመታደግ ይህንን የመሰለ ተግባር አከናውነው ማለፋቸውን” ጨምረው የገለጹ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የቤተክርስቲያን  መሪዎች “ቅድስት ቤተክርስቲያንን” ሳይሆን ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ቃል ኪዳናቸውን አፍርሰዏል ብሏል።

እምነቱን ለማጉደል ፈቃደኛ ያልሆነውን የጴጥሮስ ምሳሌ በማውሳት ደፋር ለመሆን መምረጡን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ያወሱ ሲሆን “በጥልቀት ኢየሱስን ይወድ ነበር፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ሰዓት ትንሽዬ ፍርሃት ነበረበት ብለዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ “የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለመግለጥ ለእግዚአብሔር ልቡን የከፈተ ሰው ነበር ፣ ከዚያ በኋላ ኢየሱስን በመካድ ወደ ፈተና ውስጥ የገባል” በማለት ስለጴጥሮስ ታሪክ ያስታወሱ ሲሆን ነገር ግን ከፈተና ወደ ጸጋ የተደረገ ጉዞ ነበር ብለዋል።

የጴጥሮስ 'ሚስጥር'

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ “የጴጥሮስ ጥንካሬ ምስጢር ከየት መጣ?” በማለት ጥያቄ ማንሳታቸው የተገለጸ ሲሆን እኛ ይህንን እንድንረዳ የሚያግዘን አንድ ጥቅስ አለ  ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ያለውን ስሜት ሲገልጽ ‘ “ስምዖን፣ ስምዖን ሆይ፤ እነሆ፣ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ” (ሉቃስ 22፡31) ብሎ መናገሩን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለዕለቱ ያዘጋጁትን ስብከት ከማጠናቀቃቸው በፊት ኢየሱስ ለጴጥሮስ እንደሚፀልይ ተናግረዋል፣ ለሁላችንም ይጸልያል ያሉ ሲሆን ምዕመኑ ጸሎት በሚያደርግበት ወቅት በጸጋ ላይ ጸጋ እንዲሰጣቸው ብቻ መጸለይ እንደ ማይገባ ገልጸው ለእኛ ሲል መከራን በተቀበለው በኢየሱስ ሕማማት ላይ በማሰላሰል መጸለይ እንደ ሚገባ ጨምረው ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው የእለቱን ስብከት አጠናቀዋል።

23 April 2020, 17:39
ሁሉንም ያንብቡ >