ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ፋርማሲስቶች የታመሙ ሰዎችን ስለምታገለግሉ አመሰግናለሁ አሉ።

በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዝያ 08/2012 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የታመሙ ሰዎችን በማገልገል ላይ የሚገኙትን የምድኅኒት ቤት ሰራተኞች (ፋርማሲስቶች) ጸሎት ያደርጉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ስብከት ላይ ፋርማሲስቶችን አመስግነዋል። ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ቅዱስ ወንጌልን በታላቅ ብርታት እንድንመሰክር የሚያስችለንን ታላቅ ጥንካሬ ያገኘነው ከሙታን በተነሳው ጌታ ደስታ ተሞልተን ነው ያሉ ሲሆን ይህ ደስታ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በመስዋዕተ ቅዳሴው መግቢያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትኩረታቸውን ያደረጉት በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በተነሳው ወረርሽኝ ምክንያት የታመሙ ሰዎችን በመርዳት ላይ የሚገኙትን የመድኅኒት ቤት ሰራተኞችን ወይም ፋርማሲስቶችን በጸሎት በማሳትወስ ሲሆን የገዛ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ለሌሎች አግልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትን ፋርማሲስቶች አመስግነዋል፣ እንዲህም ብለዋል . . .

በእነዚህ ቀናት ውስጥ በእኔ ላይ አንድ ነቀፋ ደርሶብኝ ነበር፣ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን አንድ ቡድን ዘንግቼ ነበረና ... ዶክተሮችን ፣ ነርሶችን ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎችን አመስግኜ ነበር ... "ነገር ግን ፋርማሲስቶችን ረስቼ ነበር" - እነሱ የታመሙ ሰዎችን ከበሽታው እንዲፈወሱ ለመርዳት በጣም ብዙ በመሥራት ላይ የገኛሉ። ለእነሱም እንፀልያለን ፡፡

በወቅቱ ከሉቃስ ወንጌል 24፡35-48 ላይ ተወስዶ በተነበበው “ከሙታን የተነሳው ጌታ ለሐዋርያቱ በተገለጸበት ወቅት እነሱ ደንግጠው በፍርሀት ተዋጡ፤ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው። ከደስታቸው ብዛት ያዩትን ማመን አቃታቸው” በሚለው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስተንትኖ ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በከፍተኛ ደስታ መሞላት የመጽናናት ተሞክሮ ነው ብለዋል።

የጌታ መምጣት ሙላት ነው፣ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ  ጸጋ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በላቲን ቋንቋ  “Evangelii nutiandi” (ወንጌልን ማወጅ)ከተሰኘው ጳውሎስ 6ኛ ከጻፉት ደስተኛ የቅዱስ ወንጌል ሰባኪዎችን የሚያመለክት ቃለ ምዕዳን በመጥቀስ ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ እና የሕይወት ምስክርነት በመስጠት ወደፊት ለመጓዝ የሚያስችለንን ጥንካሬ የሚሰጠን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ የሆነው በጌታ የምናገኘው ደስታ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

16 April 2020, 08:45
ሁሉንም ያንብቡ >