ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በችግር እና በፈተና ወቅት ካህናት ለሕዝባቸው ቅርብ ሊሆኑ ይገባል አሉ!

ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 04/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም እና እንዲሁም በጣሊያን በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በእዚህ በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች ጸሎት ማድረጋቸውን እንደ ሚቀጥሉ የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም በእዚህ በሽታ የተያዙትን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ብቻቸውን እንዳይተዋቸው የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በእዚህ በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማደረግ ይጎበኙዋቸው እና ያጽኗኗቸው ዘንድ ለቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና እረኞች ጸሎት ማደረግ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የቤተክርስቲያን እረኞች የእግዚአብሔርን ህዝብ ብቻቸውን እንዳይተዋቸው ተገቢውን ጥንቃቄ በማደረግ ምዕመኑን እንዲጎበኙ፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተንተርሰው እንዲያጽኗኗዋቸው እና ቅዱስና የቤተክርስቲያን ምስጢራትን ተደራሽ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም በፀሎት መንፍስ አብረዋቸው ይጓዙ ዘንድ ለቤተክርስቲያን እረኞች ልንጸልይ ይገባል ብለዋል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባስረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እርሳቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበትን ሰባተኛ አመት በማስታወስ ጸሎት ያደርጉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያ ለበሽታ ለተዳረጉ ሰዎች ጸሎት ያደረጉ ሲሆን ምዕመናኑም በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት በመሰቃየት ላይ ለሚገኙ ሰዎች ጸሎት ያደርጉ ዘንድ ቅዱስነታቸው ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የሚከተለውን ብለዋል . . .

በእነዚህ ቀናት በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለሚሠቃዩ ሕመምተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በጸሎት ከእነርሱ ጋር ሕብረት ልንፈጥር ይገባል። በተጨማሪም በዚህ ችግር ውስጥ ከሚገኙ የእግዚአብሔርን ህዝብ ጋር አብረው ይጓዙ ዘንድ፣ በተቻላቸው መጠን ጥንቃቄ በማድረግ በእዚህ በሽታ ተጠቂ ለሆኑ ምዕመናን ቅዱሳና የቤተክርስቲያን ምስጢራትን ተደራሽ ያደርጉ ዘንድ  እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን እረኞችን ይረዳቸው ዘንድ በጸሎታችን ልናግዛቸው ይገባል። በእዚህ ወቅት የቤተክርስቲያን እረኞች የሚሰጡት አገልግሎት አደጋ ላይ የሚጥላቸው በመሆኑ የተነሳ ልንጸልይላቸው ይገባል። እረኞች በእዚህ ወቅት የማስተዋል ችሎታ እንዲኖራቸው  እና ለቅዱሱ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሰጡትን መንፍሳዊ አገልግሎት በጥንቃቄ ያከናውኑ ዘንድ እንዲረዳቸው መንፍስ ቅዱስ እንዲያበረታቸው ልንጸልይ የጋብል።  የእግዚአብሔር ህዝብ የቤተክርስቲያን እረኞች ከእነርሱ ጋር እንደ ሆኑ ሆኖ እንዲሰማቸው መጽናኛ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል ማዳረስ ይችሉ ዘንድ እንዲረዳቸው ልንጸልይ ይገባል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአሁኑ ወቅት የጣልያን መንግሥት ይህንን ወቅታዊው የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ይቻል ዘንድ መንግሥት በመውሰድ ላይ  የሚገኘውን የመካከል እርምጃ አንዱ አካል የሆነውን “በርካታ ሕዝብ በአንድ ቦታ መስብሰብ የለበትም፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ሊደረጉ አይገባም” በማለት ይህ የኮሮና ቫይረስ እያደርሰ የሚገኘውን አደጋ ለማስቀረት በመንግስት በኩል የሚወስደውን እርምጃ የማይቃወም ሲሆን  ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት አስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ በምንገኝበት ወቅት በመንፈሳዊነት አብሮ መጓዝ የሚያስፈልጋቸውን የታመሙ ሰዎች ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤተክርስቲያን እረኞች የተቻላቸውን ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ እንክብካቤ ለምዕመኑ ማደረግ ይኖርባቸው የሚለውን መንፈሳዊ ጥሪ ይመለክታል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ ከሰጡት አስተያየት በመቀጠል በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል (21፡ 33-43) ተወስዶ በተነበበውና . . .

“አንድ የወይን ዕርሻ ባለቤት ነበረ፤ በዕርሻው ዙሪያ አጥር አጠረ፤ ለወይኑ መጭመቂያ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ለጥበቃ የሚሆን ማማ ሠራ፤ ከዚያም ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። የመከር ወራት ሲደርስ፣ ፍሬውን ለመቀበል አገልጋዮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላካቸው። “ገበሬዎቹም አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። እርሱም ከፊተኞቹ የሚበልጡ ሌሎች አገልጋዮቹን ላከ፤ ገበሬዎቹም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። በመጨረሻም፣ ‘ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከ። “ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት። “ታዲያ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት ሲመጣ እነዚያን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?” . . .

. . . በሚለው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ያጠነጠነ ስብከት እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በእለቱ ከኦሪት ዘፍጥረት 37፡3 ጀምሮ በተነበበው እና ዮሰፍ በወንድሞች መሸጡን በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፣ በሁለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል ግንኙነት እንዳለ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ሁለቱም ምንባባት የክርስቶስን ስቃይ፣ ሞት እና ከሙታን መነሳት እንደ ሚያመለክቱ ጨምረው ገልጸዋል።

በእለቱ በተነበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው “የወይን ዕርሻ ገበሬዎች ምሳሌ” ውስጥ የተጠቀሱት ገበሬዎች የእግዚአብሔር ሕዝብን እንደ ሚወክሉ ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው የሚመከተለውን ብለዋል . . .

እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ መረጠ፣ እናንተ ሕዝቦቼ ናችሁ በማለት ለአብርሃም የገባለት ቃል ነው፣ በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያመለክታል፣ ህዝቡ ሁል ጊዜ የተመረጠ ህዝብ መሆኑ በመገንዘብ፣ የሚጠብቀውን ተስፋ በየቀኑ በታማኝነት ለመኖር የሚደረገውን ጥረት ሁል ጊዜ ማስታወስ አለበት። ነገር ግን በዚህ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሱ የወይኑ ፍሬ የሚሰበሰብበት ጊዜ ሲመጣ እነዚህ ገበሬ የነበሩ ሰዎች የእርሻው ባለቤት አለመሆናቸው ረስተው ባለቤት ለመሆን ፈልገው ነበር።  “ገበሬዎቹ አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ገደሉት ሌላውም በድንጋይ ወገሩት። ከዚያም ጌታው ከእዚያ የሚበልጡ ብዙ ሌሎች አገልጋዮቹን ላከ ፤ እነሱ ግን በተመሳሳይ መንገድ ሁሉንም ነገር ፈጸሙባቸው። በእርግጠኝነት ኢየሱስ እዚህ ጋር ልያሳየን የፈለገው ነገር ቢኖር የሕግ መምህራን የነበሩ ሰዎች ነቢያትን እንዴት እንዳሰቃዩዋቸው ለመግለጽ አስቦ ነው የተናገረው።  ለልጁ አክብሮት ይኖራቸዋል ብሎ በማሰብ የገዛ ልጁን ወደ እነሱ ላከ። ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በእርሳቸው 'ወራሹ እርሱ ነው። ኑ እንግደለው። ​​ርስቱንም እንውረስ! ተባባሉ’።  ርስቱን ሰረቁ፣ ይህ ርስት ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ያስታውሳል። መመረጥ፣ ቃልኪዳን መግባት እና ከእግዚአብሔር ጋር ሕበረት መፍጠር እነዚህ ነገሮች ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጡን ጸጋዎች ናቸው።  የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ማጉደል ተገቢ አይደለም። ይህ ታላቅ ኃጢአት ነው ፡፡ እግዚአብሔር እራሱን ለእኛ ስጦታ አድርጎ የሰጠውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሕይወታችን አጥብቀን ልንይዘው የገባል። እግዚአብሔር እንደ ስጦታ አድርጎ የሰጠንን ነገር መርሳት የለብንም። እግዚአብሔር እራሱን እንደ ስጦታ አድርጎ እንደገለጠ እናስታውስ።  እራሱ ለእኛ ስጦታ አድርጎ እንዳቀረበ እና እንደሰጠ እኛም ራሳችንን ለሌሎች መስጠት ይኖርብናል። በአዕምሯችን  እና በአስተሳሰባችን ዛሬ ስጦታውን እንደ ስጦታ ለመቀበል እና ስጦታን እንደ ግል ንብረት ሳይሆን እንደ ሃይማኖታዊ መንገድ ፣ ጠንካራ የማይበጠስ የቃል ኪዳን ገመድ አድርገን መቀበል እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንማጸነው ይገባል።

13 March 2020, 13:25
ሁሉንም ያንብቡ >