ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በጥር 08/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በጥር 08/2012 ዓ.ም  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በሕይወታችን መሠረታዊ የሆነ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በጥር 08/2012 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 2፡1-12 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ኢየሱስ ሽባ ሆኖ የተወለደውን ሰው መፈወሱን በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ ስብከት እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የሕይወታችን መሠረታዊ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው” ማለታቸው ለመረዳት ተችሉዋል። “አካላዊ የሆነ ፈውስ ማግኘት መልካም ነገር ነው፣ ነገር ግን እኛ ስነልቦናዊ ሰለሆነ ፈውስ አስበን እናውቃለን ወይ?” በማለት ጥያቄ በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስነልቦናዊ የሆነ ፈውስ ሊሰጠን ወደ ሚችለው ሐኪም መሄድ እንዘነጋለን ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቀደም ሲል እንደ ገለጽነው በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል ላይ ተወስዶ በተነበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ሽባ ሆኖ የተወለደውን ሰው መፈወሱን የሚገልጽ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ሲሆን ኢየሱስ በቅፍርናሆም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነ በማሰተማር ላይ በነበረበት ወቅት እጅግ በጣም ብዙ ሰው በዙሪያው ተስብስቦ ነበር፣ አራት ሰዎች አንድ ሽባ የሆነ ሰው እንዲፈውስላቸው በማሰብ በአልጋ ላይ በሽተኛውን አስተኝተው ወደ ስፍራው መጡ፣ ከህዝቡ ብዛት የተነሳ ኢየሱስ የነበረበት ስፍራ መድረስ ስላልቻሉ ኢየሱስ የነበረበትን ቤት ጣር ሸንቁረው በሽተኛውን በሸነቆሩት ቀዳዳ ወደ ውስጥ አስገብተው በኢየሱስ ፊት አቀረቡት፣ እነርሱ ኢየሱስ ሽባውን ሰው ይፈውሰዋል የሚል ተስፋ የነበራቸው ሲሆን ኢየሱስ ግን “አንተ ልጅ፣ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል!” በማለት ሁሉንም ሰው ያስገረመ ንግግር ካደረገ በኋላ በመቀጠል “ተነስተህ አልጋህን ይዘህ ወደ ቤትህ ሂድ” ይለዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ በእዚሁ ጭብጥ ዙሪያ ባደርጉት ስብከት ኢየሱስ በቃሉ በሕይወታችን ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ እንድናመጣ ወደ ሚያደርገን እግዚኣብሄር መቅረብ እንዳለብን ጥሪ ያቀርብልናል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን “እርሱ የእግዚአብሔር ሰው ነው” በማለት ሕዝቡ በሁኔታው እንደ ተገርመው እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን በእዚህም የተነሳ ሕዝቡ እግዚኣብሔርን እንዳመሰገነም ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጽናት አስበው ሽባውን ተመለከተና “ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው፣ አካላዊ ፈውስ ማግኘት በራሱ አንድ ስጦታ ነው፣ አካላዊ ጤንነት ከፍ አድርገን ልንመለከተው የሚገባ ጸጋ ነው። ነገር ግን የልባችንን ጤንነት፣ መንፈሳዊ ጤናንነታችን መጠበቅ እንዳለበት ጌታ ያስተምረናል” ብለዋል።

ከጌታ ጋር ለመገናኘት እርሱ ወደሚኖርበት ቦታ የመሄድ ፍርሃት

በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው እያለቀሰች ወደ እርሱ የመጣችሁን አንዲት ኃጢአተኛ ሴት አታልቅሺ “ኃጢአትሽ ተስርዮልሻል” ብሎ ኢየሱስ መናገሩን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ንግግሩ ኢየሱስ በሕይወት ውስጥ መሰረታዊ ወደ ሆነ ሁኔታ ውስጥ እንድንገባ ያሳስበናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በማለቱ ሌሎች ሰዎች መደናገጣቸውን የገለጹ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በሕይወታችን ውስጥ መሰረታዊ ወደ ሚባሉ ነገሮች በምንቀርብበት ወቅት በእዚያ ስፍራ ትንቢታዊ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል በመኖሩ የተነሳ ነው በለዋል። በተመሳሳይ መልኩም በሴሎሄም የመታጠቢያ ስፍራ የነበረውን ሰው ኢየሱስ ባየው ጊዜ “ ተነስና ሂድ፣ ነገር ግን ዳግመኛ ኃጢአት አትሥራ” ብሎ ተናግሮ እንደ ነበረ ጨምረው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በሕይወታችን ውስጥ መሰረታዊ የሚባለው ነገር ከእግዚኣብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው ብለዋል።

“እኛ ብዙን ጊዜ ይህንን እውነታ እንዘነጋለን፣ በሕይወታችን ውስጥ መሰረታዊ ወደ ሆነው ወደ እግዚኣብሔር መቅረብ እንፈራለን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አካላዊ የሆነ ፈውስ ለማግኘት በማሰብ ሕክሞቻችንን እናማክራለን፣ መድኃኒት እንወስዳለን፣ ነገር ግን የነፍሳችን አዳኝ የሆነውን እግዚኣብሔር ለመገናኘት መሂደ ግን እንፈራለን ብለዋል። በመሆኑ በሕይወታችን ውስጥ “አስፈላጊው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ የነፍሳችን አዳኝ ወደ ሆነው እግዚኣብሔር መቅረብ መፍራት አይኖርብንም ብለዋል።

ይቅርባይነት ለልብ ጤና መድሃኒት ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ለነፍሳችን እና ለልባችን ፍቱህ የሆነው መድኃኒት የኃጢአት ስርዬት ነው ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን የነፍሳችን በሽታዎች ሁሉ ሊፈወሱ የሚልቹት በእዚሁ መልኩ ብቻ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
17 January 2020, 14:23
ሁሉንም ያንብቡ >