ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የጌታ ቸርነት ምድረ በዳው እንኳን ሳይቀር እንዲለመልም ያደረጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት “የጌታ ቸርነት ምድረ በዳው እንኳን ሳይቀር እንዲለመልም ያደረጋል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉት ስብከት መሰረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በቀዳሚነት ከመጸሐፈ መሳፍንት 13፡ 2-7,24-27 ላይ ተወስዶ በተነበበውና የሳምሶ መወለደ በሚገልጸው ታሪክ ላይ እና እንዲሁም በተጨማሪም በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 1፡5-25 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ በሚገልጸው ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በእነዚህ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የተገለጹት የሳምሶን እናት እና እንዲሁም የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የነበረችው ኤልሳቤጥ ሁለቱም መሐን የነበሩ ሴቶች የነበሩ ሲሆን እግዚኣብሔር በምሕረቱ ማሕጸኖቻቸው እንዲለመልም አድርጉዋል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢሳያስን ትንቢት በመጥቀስ ፣ አምላክ ሁሉንም ነገር በቸርነቱ መለወጥ እንደ ሚችል፣ በረሃውን ሳይቀር ማለምለም እንደ ሚችል በመግለጽ እና ለክርስቲያኖች በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚአብሔር በነጻ ያድናል፣ ነገር ግን እራሳችንን ለማዳን በፈለግን ጊዜ ኃጢአት እንሠራለን ብለዋል።

በእግዚአብሔር ዘንድ የማይቻል ነገር የለም

ከሳምንት በኋላ በሚከበረው የገና በዓል (የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ምዕመናን ዘንድ ከሳምንት በኋላ የሚከበረውን የገና በዓል ይመለከታል) ከመድረሱ በፊት የተነበቡት የእግዚኣብሔር ቃላት “በሁለት በረሃዎች ፊት ያስቀመጣናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ ሁለት በረሃዎች ሁለቱን መካን የነበሩ ሴቶችን ማለትም የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የነበረችው ኤልሳቤጥ እና በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሰችው የሳምሶን እናት እንደ ሚወክሉ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኤልሳቤጥ ሲናገሩ የአብርሃምን እና የሣራ ታሪክ ያስታውሰናል። መካንነት ከምድረበዳነት ጋር እንደ ሚመሳሰል በስብከታቸው ያብራሩት ቅዱንሰታቸው ኤልሳቤጥ እና ሳራ ሁለቱም ሴቶች በጌታ ላይ እምነት ነበራቸው፣ በእዚህም ምክንያት መካን የነበሩ ሁለቱ ሴቶች ሁለቱም ጸንሰው ልጅ ለመውለደ መቻላቸውን ጨምረው ገልጸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጨምረው እንደ ገለጹት ሁለቱም ሴቶች መፀነሳቸው እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የተፈጥሮን ሕግ እንኳን ሳይቀር ለመቀየር ብቃት እንዳለው የሚያሳይ ተግባር እንደ ሆነ አመልክተው ለቃሉ መንገድን የመክፈት ችሎታ እንዳለው ጭምረው ገልጸዋል።

የእግዚአብሔር ቸርነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “የእግዚአብሔር ስጦታዎች በነጻ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፣ የሁለቱ ሴቶች ሕይወት የእግዚአብሔር ችሮታ መገለጫ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱነታቸው እንደ እርሳቸው ገለጻ ገለጻ መጥምቁ ዮሐንስ እና ሳምሶን “የእግዚአብሔር የቸርነት ስጦታ መገለጫዎች ናቸው”  ይልቁንም “የመዳን አምሳያችን” ምልክቶች ናቸው ፣ ምክንያቱም “ራሱን ሊያድን የሚችል ማንም ሰው የለም” ብለዋል። ከስህተቶቻችን እና ከጭካኔዎቻችን ሊያድነን የሚችለው ማን ነው? እናም አንድ ሰው ጌታ ያድነው ዘንድ ራሱን የማይሰጥ ከሆነ አይድንም ፣ ስለዚህ አንድ ሰው እምነት ሊኖረው ይገባል እርሱም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ብለዋል።

ሁላችንም መካኖች ነን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት የጸጋ ስጦታን በተመለከተ አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት የቅዱስ አጎስጢኖስን መልካም ሐሳብ እና ጥሪ በመከተል ልባችንን ለእግዚኣብሔር መክፈት ተገቢ እንደ ሆነ ቅዱነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። አንድ ሰው ካቶሊክ ነኝ ቢል እና ዘወትር እሁድ መስዋዕተ ቅዳሴ ለማስቀደስ ወደ ቤተክርስቲያን ቢሄድ፣ የአንድ ማህበር አባል እና የመሳሰሉት የቤተክርስቲያን ተቋማት አባል ቢሆን “በእግዚአብሔር ስጦታዎች ላይ የማይታመን” ካልሆነ በስተቀር ምንም ሊያድነው አይችልም ያሉ ሲሆን ሁሉም ነገር የጸጋ ስጦታ ስለሆነ ፣ ሁሉም እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ እና እርሱን እንዲያመሰግኑ ተጠርተዋል ብለዋል።

ኃጢአት ራሳችንን የመበዤት ፍላጎት ውጤት ነው

በዛሬው ምንባባት ውስጥ የተጠቀሱት ከሁለት መካን ሴቶች መካከል የተወለዱት ታዋቂ ሰዎች መካከል አንዱ በሆነውና ሕዝቡን ከፍልስጥኤማውያን የሚያድን ጠንካራ እና ተዋጊ የነበረው ሳምሶን ላይ ትኩረታቸውን በማደረግ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ምናልባት ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ስጦታ በግድዬለሽነት የተቀበለ ሰው መሆኑን ገልጸው ስህተት ሠርቶ ለፍልስጥኤማውያን በሸጠችው ሴት እጅ ውስጥ ወደቀ ብለዋል። ሆኖም እርሱ ከስህተቱ ተመለሰ፣ ሳምሶን ሁላችንም ኃጢአተኞች መሆናችንን እና ኃጢያተኛነት ይህንን የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያጨናግፍ አለመሆኑን ክርስቲያኖችን እንዲያስታውሱ የሚረዳቸው መሆኑ ጭምረው ገለጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስብከታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት እኛም እንደ ሳምሶን ተንሸራተን እራሳችንን በራሳችን እንደምናድን ወደ ማመን እንሄዳለን፣ ይህ ራሳችንን በራሳችን ለማዳን የመፈለግ ምኞት በራሱ ኃጢአት ነው ብለዋል።

በእዚህ አሁን ከገና በዓል በፊት ባለንበት ቀናት ውስጥ እግዝኣብሔር ስለሚሰጠን የድህንንተ ስጦታ አመስጋኞች መሆን ይኖርብናል ያሉት ቅዱነታቸው እርሱ ማለትም እግዝኣብሔር በነጻ ስለሚሰጠን ነገሮች ሁሉ እርሱን ማመስገን ይኖርብናል ካሉ በኋላ ቅዱነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

20 December 2019, 12:44
ሁሉንም ያንብቡ >