ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (ANSA)

ሕይወታችንን ዐለት በሆነው በክርስቶስ ላይ መገንባት ይኖርብናል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደንግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በኅዳር 25/2012 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ሕይወታችን በውጫዊ ገጽታ ላይ ሳይሆን ነገር ግን በጌታ ላይ መሰረቷን ማደረግ ይኖርባታል” ማለታቸው የተገልጸ ሲሆን ሕይወታችንን አላፊ በሆኑ ነገሮች ላይ ሳይሆን ከእዚያ ባሻገር በመሄድ ጠንክራ መሰረት ባለው “ዐለት” ላይ መገንባት ለሕይወታችን ደስታ እንደ ሚሰጣት ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉት ስብከት በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል 7፡21-27 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ስለ ብልኁና ሞኙ ቤት ሠሪ በሚገልጸው ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ከስፍራው ለቫቲካን ሬዲዮ ክደረሰው ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን  “ሁል ጊዜ በጌታ ተማመኑ፣ ምክንያቱም ጌታ ዐለታችን ነው፣ የሕይወታችን ዘላለማዊ ዐለት ነው” ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ጠንካራ የሆነ ውዳሴ” የተሰኘው ሐሳብ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደረጉት ስብከት ማዕከላዊ ይዘት እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት በእለቱ በተነበው ቅዳስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ  ጥበበኛ እና ሞኝ የነበሩትን ሁለት ሰዎች በንጽጽር በማስቀመጥ አንደኛው ሰው ሕይወቱን በጌታ ላይ የመሰረተ፣ የሕይወቱ ስር መሰረት በጌታ ላይ እንደ ሆነ፣ በሕይወቱ ውስጥ የራሱን ቤት በዐለት ላይ እንደ ገነባ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ሌላኛው ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል የማይሰማ፣ እንዲሁም የታይታ ሕይወት ይኖር የነበረ ሰው በመሆኑ የተነሳ የእዚህ ዓይነቱ ሰው ደግሞ ቤቱን ደካማ በሆነ በአሸዋ ላይ የገነባ ሰው ይመስላል ብለዋል።

ጌታ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጠንካራ ዐለት ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ጥበበኛ እና ሞኝ” በሚሉት ሁለት ቃላት ላይ ትኩረቱን ባደረገ መልእኩ ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት “ተስፋችን፣ ደህንነታችን እና ሕይወታችን በምን ዓይነት ዐለት ላይ እንደ ተገነባ ለይተን ማወቅ እንችል ዘንድ ፀጋውን እንዲሰጠን ጌታን ልንጠይቀው የገባል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ሕይወታችን፣ ተስፋችን እና ሕልውናችን እውነተኛ የሆነ ዓለት ላይ ነው ወይስ አሸዋ ላይ ነው የተገነባው የሚለውን ለይተን ለማወቅ እንችል ዘንድ እግዚኣብሔር እንዲረዳን ልንጠይቀው የገባል” ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተልውን ብለዋል. . .

ዐለታችን ጌታ ራሱ ነው።  እራሳቸውን ለጌታ በአደራ የሚሰጡ ሁሉ መሠረታቸው ዓለት ላይ ስለሆነ ፣ ሁልጊዜ ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል። በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ የተናገረው ይህንኑ ነው። እሱ ከበድ ያሉ ጉዳዮች በሕይወቱ ቢገጥሙትም እንኳን በጌታ በመተማመን ቤቱን በዐለት ላይ የገነባ ሰው እርሱ ጥበበኛ ሰው ነው።  እናም ይህ እምነት በጣም ጥሩ የሆነ መሰረት ነው፣ ምክንያቱም የዚህ ዓይነቱ ሕይወት ግንባታ መሠረት አስተማማኝ ነው ፣ ጠንካራም ነው።

በአሸዋ ላይ መሰረቱን ያደረገ የክርስትያን ሕይወት ፈራሽ ነው!

ስለዚህ ቤቱን በዓለት ላይ የሚገነባ ሰው እርሱ ጥበበኛ ሰው ነው፣ በተቃራኒው “ሞኙ” አሉ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ሞኙ ሰው ቤቱን ለመግንባት የፈለገው እውነተኛ መሰረት በሌለው “በሚንቀሳቀስ አሸዋ” ላይ ለመገንባት መምረጡን” ገልጸው በእዚህ ሁኔታ የተገነባ ቤት ደግሞ በንፋስ እና በዝናብ የሚደረመስ ቤት ነው ብለዋል። ይህ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ፣ እንዲሁም መልካም እና ጠንክራ ባልሆነ መሠረት ላይ የተገነቡ ሕንጻዎች ላይ የሚከሰት እውነት ነው፣ እንደእነዚህ ያሉ ሕንጻዎች ይወድቃሉ፣ እኛም ሕይወታችን በአሸዋ ላይ የተመሰረተ ከሆነ እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ እንወድቃለን ብለዋል።

መሠረታችን ጠንካራ ካልሆነ ሕይወታችንም እንደዚህ ሊሆን ይችላል። አውሎ ነፋሱ ይመጣል - እኛ ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ አውሎ ነፋሶች ይከሰታሉ፣ ሁሉም ሰው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አንስቶ እስከ መጨረሻው ባሉ ሰዎች ሕይወት ውስጥ በሁላችንም ሕይወት ውስጥ የሚክሰተውን አውሎ ነፋስ ብቻችንን መቋቋም አንችልም። ብዙዎች ደግሞ “አይሆንም ህይወቴን እለውጣለሁ” ይላሉ እናም የአንድን ሰው ሕይወት ለመለወጥ ውጫዊ ገጽታን ብቻ ማስተካከል በቂ ነው ብለው ያስባሉ። ህይወትን መለወጥ ማለት ሕይወታችን የተመሰረተበትን መሰረት መለወጥ ማለት፣ እርሱም ዓለታችን በሆነው በኢየሱስ ላይ መሰረታችንን ማደረግ ማለት ነው። "ይህንን ቤት ወይም ቤተመንግስት ለማደስ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ሕንጻው   እጅግ በጣም አስቀያሚ ስለሆነ አፍርሼው መሰረቱን በጥሩ ዐለት ላይ አድርጌ መልሼ መገንባት እፈልጋለሁ። ነገር ግን መልኩን ብቻ አሳምሬ መሰረቱን በማይረባ አለት ላይ በማድረግ ቤቱን ከገነባው ሕንጻው ብዙም አይቆይም፣ ይፈርሳል፣ በታይታ ላይ የተመሰረተ የክርስትና ሕይወትም እንዲሁ ነው፣ በእዚህ መልኩ ይወድቃል።

“አሰትማማኝ መሰረታችን ኢየሱስ ብቻ ነው፣ ውጫዊ ገጽታ በራሱ ምንም ዋጋ የለውም፣ እናም ይህ ነገር እና የእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ንስሐ በምንገባበት ወቅት ጭምር በግልጽ ይታያል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለምሳሌም ራሳቸውን እንደ ኃጢያተኛ ፣ ደካማ ፣ መዳን እንዳለባቸው የሚገነዘቡ ሰዎች ብቻ ሕይወታቸው በጌታ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ሆነ አድርገው እንደ ሚያስቡ የገለጹት ቅዱስነታቸው ለእዚህ ዓይነቱ ሰዎች ኢየስሱ ቅርብ እንደ ሆነ ገልጸዋል። በእዚህም ምክንያት የተነሳ በማያልፈው እና በማይፈርሰው ዐልት በሆነው በኢየሱስ ላይ ሕይወታችንን መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

መልካም በሚመስሉ ነገሮች ላይ፣ ሁሉን ነገር ጥሩ እንደሆነ በሚያስመስሉ ነገሮች ላይ ሕይወታችንን መገንባት የለብንም። ደህንነት ወደ ሚሰጠን ዓለት እንሂድ። እናም ሁላችንም እዚያ ደስተኞች እንሆናለን።

ስለሆነም በእዚህ አሁን በምንገኝበት በስብከተ ገና ወቅት (የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በኅዳር 21/2012 ዓ.ም የተጀመረውን የስብከተ ገና ወቅት ማለታቸው ነው) “እያንዳንዳችን ሕይወታችንን ልንገነባበት የምንፈልገው መሠረት ምንድነው?” ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በእዚህ የስብከተ ገና ወቅት የምናደርገውን ጸሎት እንዴት መጸለይ እንደ ሚገባን እንዲረዳን ጸጋው መጠየቅ ይገባል፣ ሕይወታችን የተገነባው በጠንካራ ዐለት ላይ ነው? ወይስ በአሸዋ ላይ ነው? ለሚለው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንችል ዘንድ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ እንችል ዘንድ እንዲረዳን ልንማጸነው የገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
05 December 2019, 15:13
ሁሉንም ያንብቡ >