ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በመልካም እና በክፉ መካከል ባለው ውስጣዊ ትግል ውስጥ ድነትን እንመርጣለን” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ ዛሬ በጥቅምት 14/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመና በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ከምዕራፍ 7፡18-25 ተወስዶ በተነበበው የጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት “በመልካም እና በክፉ መካከል ባለው ውስጣዊ ትግል ውስጥ ድነትን እንመርጣለን” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ በመልካም ነገር እና በኃጢያት መካከል ትግል እየተደረገ እንደ ሚገኝ ገልጸው እኛ የምናደርጋቸው ማነኛውም ዓይነት ውሳኔዎች የሚመነጩት ከእግዚአብሔር ነው ወይስ ከሰያጣን? ብለን በቀኑ ማብቂያ ላይ በልባችን ለራሳችን ጥያቄ ማቅረብ ይገባናል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን  

በውስጣችን እየተከሰተ የሚገኘውን ነገር "በደንብ" እንድናውቅ እንዲረዳን ጌታ "ብርሀኑን" እንዲሰጠን እንጠይቅ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “መልካምን ለማድረግ ባለው ፍላጎት” እና ይህንን ገቢራዊ ለማድረግ አለመቻሉ በቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ሕይወት ውስጥ የተንጸባረቀ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ውስጣዊ ተጋድሎ በማደረግ እውነተኛ የሆነ ጦርነት በውስጥ እንዲከሰት አድርጎ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የሁላችንም ትግል

“አንድ ሰው” አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት “አንድ ሰው ሳይፈልግ  ክፉ ነገር መጽም ሊሆን ይችላል” ያሉት ቅዱስነታቸው ሁልጊዜም ቢሆን በውስጣችን በክፉ እና በመልካም ነገሮች ማከከል ከፍተኛ የሆነ ትግል እንደ ሚፈጸም ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ መግለጹን አስታውሰው የእዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ትግል በቅዱስና ሕይወት ውስጥ ተከስቶ ያለፈ ሁላችንንም የሚነካ ጉዳይ ነው በውስጣችን እየተካሄደ የሚገኝ “ዕለታዊ ጦርነት” ነው ብለዋል። ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

በመልካም እና በክፉ መካከል የሚደረግ ትግል ነው፣ ነገር ግን መልካም እና ረቂቅ በሆኑ ክፉ ነገሮች መካከል ውስጣዊ ትግሎች ይከሰታሉ፣ መልካም ነገር እንድንፈጽም የሚረዳን እና የሚያነሳሳን መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ክፉ ነገር እንድንሰራ የሚያነሳሳን ደግሞ ክፉ የሆነ መንፈስ ነው። በእነዚህ መካከል ከፍተኛ የሆነ ትግል አለ። ይህም በሁላችንም ውስጠ የሚከሰት ተግል ነው። “እኔ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች አይነካኩኝም፣ እኔ ደስተኛ የሆንኩ ሰው ነኝ፣ እኔ ብጹዕ ነኝ፣ እኔ ሰላም የሆንኩ ሰው ነኝ የሚል ሰው ካለ፣ እርሱ በውስጡ የሚመላለሱ ነገሮችን የማይረዳ የደነዘዘ ሰው ነው።

በዚህ ዕለታዊ ትግል ውስጥ ዛሬ እኛ አንዱን እናሸንፋለን፣ ነገ ደግሞ “ሌላ” ይከሰታል በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ሌላ። እንዲህ እያለ “እስከ መጨረሻው” በሕይወታችን ውስጥ የሚከሰት ተግል ይሆናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “ሰማዕታት እምነታቸውን ለመጠበቅ እስከ መጨረሻው መዋጋት እንደ ነበረባቸው” ገልጸው ለምሳሌ የሕጻኑ ኢየሱስ ማኅበር መስራች የሆኑት ቅድስት ትሬዛ “በጣም ከባድ የሆነው ውጊያ በመጨረሻ ሰዓት ላይ ገጥሞዋቸው እንደ ነበረ” አስታውሰው በመጨረሻው የሕይወት ዘመናቸው ላይ በአልጋ ላይ በነበሩበት ወቅት “ክፉ መንፈስ” ከጌታ ሊለያቸው እንደ ፈለገ በመረዳታቸው የተነሳ ከፍተኛ ፍልሚያ አድርገው እንደ ነበረ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 12፡54-59 ላይ ተወስዶ በተነበበውና ኢየሱስ ለሕዝቡ “ደመና በምዕራብ በኩል ሲወጣ ስታዩ ወዲያው፣ ዝናብ ሊመጣ ነው ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል፤ የደቡብ ነፋስም ከደቡብ በኩል ሲነፍስ፣ ቀኑ ሞቃት ይሆናል ትላላችሁ፤ እንደዚያም ይሆናል። እናንት ግብዞች፤ የምድሩንና የሰማዩን መልክ መመርመር ታውቁበታላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መመርመር እንዴት ተሳናችሁ?” በማለት በተናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

እኛ ክርስቲያኖች መልካምም ቢሆኑ እንኳን በብዙ ነገሮች ላይ ለዘብተኛ አቋም እንይዛለን፣ ነገር ግን በውስጣችን ምን እይተከሰተ ነው? ይህ እንዲከስት ያደርገው መንፈሳዊ ዝንባሌ ምንድነው? የእዚህ ዓይነት ስሜት እንዲሰማን ያነሳሳው ምንድነው?  ሕይወታችን ብዙውን ጊዜ በመንገድ ላይ እንዳለ ሕይወት ነው: - በሕይወት ጎዳና ላይ እንሄዳለን ... በጎዳና ላይ ስንሄድ ትኩረታችንን የሚስቡትን ነገሮችን ብቻ ነው የምንመለከተው፣ ትኩረታችንን የማይስቡ ሌሎች ነገሮችን አንመለከታቸውም።

ፀጋ እና ኃጢአት

“ትግሉ የሚካሄደው በጸጋ እና በኃጢአት፣ እኛን ሊያድነን በሚፈልግው በጌታ እና በመጥፎ ጎዳና ላይ እንድንራመድ በሚፈልገው በክፉ መንፈስ መካከል ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለሆነም እያንዳንዳችን በሕይወት ጎዳና ላይ በምንራመድበት ወቅት የእዚህ ዓይነቱን ጥያቄ መጠየቅ እንደ ሚገባን ገልጸው ሕይወታችን በመልካም ወይም በክፉ መንፈስ እየተመራ መሆን አለመሆኑን ለመለየት ራሳችንን በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት እንደ ሚኖርብን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “መልካም የሆኑ ውሳኔዎቻችን በሙሉ የሚመነጩት ከጌታ ነው፣ የራስ ወዳድ መንፈስ ደግሞ የሚመነጨው ከሰይጣን ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

በውስጣችን ምን እየተከሰተ እንደ ሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ውስጣችንን እያዳመጥን መኖር በጣም አስፈላጊ ነው፣ ነፍሳችን በመልካም ጎድና ላይ እየተመላለሰች መሆኗን ማረጋገጥ መልካም ነው። አባት ሆይ ፥ ይህ እንዴት ሆነ? በማለት ቀናችን ከመጠናቀቁ በፊት ሁለት ወይም ሶስት ደቂቃዎችን ወስደን ዛሬ በሕይወቴ ውስጥ የተከሰተው ነገር ምንድነው፣ ጥሩ ወይስ መጥፎ በማለት መጠየቅ ይኖርብናል። የእዚህ ዓይነት ጥያቄ ማቅረባችን ደግሞ የፈጸምናችውን መልካም እና ክፉ ነገሮችን ለይተን እንድናውቅ ይረዳናል።

 

25 October 2019, 15:55
ሁሉንም ያንብቡ >