ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በእግዚኣብሔር ፊት ሆነን በድፍረት እና በብርታት መጸለይ ይገባናል” አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 26/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት በብርታት መጸለያችንን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት ከጌታ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን መጸለይ እንደ ሚገባን፣ በተለይም ደግሞ ሕይወታችንን በሙሉ ለእርሱ ማቅረብ እንደ ሚገባ” የገለጹ ሲሆን በተለይም ደግሞ በዚህ በዐብይ ጾም ወቅት በብርታት ጸሎት ማድረጋችንን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል። ይህንን ስናደርግ ደግሞ ሦስት መንፈሳዊ እና መሰረታዊ ነገሮችን ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን የዐብይ ጾም ወቅት በጸሎት፣ ለጋስ በመሆን እና በመጾም ማክበር ይኖርብናል ብለዋል።

በድፍረት ጸልዩ

ለመጸለይ ብዙ ብርታት ያስፈልገናል። ብዙን ጊዜ ደግሞ እኛ ግድ የለሽ እና ለብ ያልን ሰዎች እንሆናለን። እውነተኛ ጸሎት ደግሞ ይህ ነው. . . ከጌታ ጋር አብሮ መሆን ነው። ስንጸልይ ከፍተኛ የሆነ ብርታት ያስፈልገናል። ጸሎታችንን ሥረዓት ባለው እና መንገዱን በጠበቀ መልኩ ማድረግ ይኖርብናል። ‘እሺ ነገር ግን በዚህ መልኩ ብጸልይ፣ እግዚኣብሔር እኔን እንደ ሚሰማኝ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?’ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል። ማረጋገጫችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ብቻ ነው። እርሱ ታላቅ የሆነ አማላጃችን ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት በድፍረት ወይም በነፃነት የመናገር መብታችንን ተጠቅመን ጌታን በድፍረት መለመን ይጠበቅብናል ብለው ይህንን በተመለከተ በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ የተጠቀሱትን በብቃት የማማለድ ተግባራቸውን የተወጡትን ሙሴን፣ አብርሃምን፣ ሐና እና ከኔናዊት የነበረችውን ሴት ምሳሌ በዋቢነት አንስተዋል።

እነዚህ ቀደም ሲል በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ፍላጎቶቻቸውን ለማስፈጸም በብርታት እና በድፈረት ከጌታ ጋር ተነጋግረው እንደ ነበረ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች አንድ ነገርን ለማግኘት ከጌታ ጋር እንዴት እንደሚታገሉ ስንመለከት ከእግዚአብሔር ጋር ውጊያ የሚያደርጉ የሚመስል ሲሆን ነገር ግን ያሰቡት ነገር ሁሉ ይፈጸምላቸው ነበር” ብለው በድፍረት እና በኃይል ይጸልዩ ነበር ምክንያቱም ጌታ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟላ እንደሚችል እምነት ስለነበራቸው ነው ብለዋል።

ኢየሱስ ለእኛ ያማልዳል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ኢየሱስ በዚህ ምድር የነበረውን መከራ ከቀበሉ በፊት ለጴጥሮስ በገባለት ቃል መሰረት ኢየሱስ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ወቅት በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ እንደ ሚያማልድ ቃል ገብቶለት እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

04 April 2019, 13:46
ሁሉንም ያንብቡ >