ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የጾም ወቅት ከመኮነንና ከመፍረድ በመቆጠብ ይቅርታ የምናደርግበት ወቅት ነው!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 09/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቄሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “የሰማይ አባታችን መሐሪ እንደ ሆነ ሁሉ እኛም በዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት ጾማችን እውነተኛ እና እግዚኣብሔርን የሚያስደስት ይሆን ዘንድ ለበደሉን ሰዎች መሕረት ማደረግ ይኖርብናል” ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል ላይ ተወስዶ በተነበበውና “የሰማይ አባታችሁ ርኅሩኅ እንደ ሆነ ርኅሩኆች ሁኑ፣ አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ” (ሉቃስ 6፡36) በሚለው የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ ተንተርሰው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱሰነታቸው በዚህ አሁን በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት እነዚህን ክርስቲያናዊ በሕሪያትን መላበስ ይኖርብናል ብለው፣ ሁላችንም ብንሆን በሕይወት ሂደት ውስጥ ስህተቶችን እንዳንፈጽም ይረዳን ዘንድ እግዚኣብሔርን ለመምሰል መትጋት ይኖርብናል፣ በእግዚኣብሔር ፊት መመላለስ ይኖርብናል ብለዋል። በተለይም ደግሞ የሰማይ አባታችን መሐሪ እንደ ሆነ እኛም ይህንን በሐሪይ ተላብሰን መሕረት አድራጊዎች መሆን ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ሁኔታ ውስጥ የምንሆን ከሆንን ደግሞ መጥፎ የሚባሉ እና በእኛ ላይ የደረሱ በደሎችን ሁሉ ይቅር ለማለት እንችላለን ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጽናት በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል. . .

የእግዚአብሔር ምሕረት በጣም ትልቅ የሆነ ነገር ነው። ይህንን በፍጹም መርሳት አይኖርብንም። ምን ያህል ሰዎች (እንዲህ ይላሉ)፦ "እንደዚህ ያሉትን መጥፎ ነገሮች አድርጌያለሁ። እኔ በሲኦሌ ውስጥ ለእኔ የሚሆን መሬት ገዝቼለው፣ ወደ ኋላ መመለስ አልችልም"። ነገር ግን እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ስለእግዚኣብሔር ምሕረት አስበው ያውቃሉ ወይ? ከድልድይ ላይ ወደ ታች በመዝለል በወንዝ ውስጥ ገብቶ ራሱን አጥፍቶ የነበረ ሰው መበለት የነበረችው የአንዲት ድሃ ሴት ታሪክ እንመልከት፣ እርሷ ንስሐ ለመግባት ወደ አንድ ቤተ መቅደስ ትሄዳለች። እያለቀሰችም እንዲህ ትላለች “እኔ አጢያተኛ የሆንኩኝ ሚስኪን ሰው ነኝ! ምስኪን ባለቤቴም በሞት ተለይቶኛል! በገሃነብ ውስጥ ይገኛል! ራሱን በራሱ ነው ያጠፋው፣ የራሱን ነፍስ ማጥፋት ደግሞ በጣም ትልቅ የሆነ የዘለዓለም ሞት የሚያስከትል ኃጢአት ነው። በዚህም የተነሳ እርሱ በገሃነም ውስጥ ይኖራል! ንስሐ ያስገቡዋት ካህንም እንዲህ በማለት ይመልሳሉ “አንቺ ሴት እባክሽን አታልቅሽ! ምክንያቱም በድልድዩ እና በወንዙ መካከል የእግዚኣብሔር መሕረት አለና! እስከ መጨረሻ ጊዜ ድረስ የእግዚኣብሔር ምሕረት አለ።

ለዐብይ ጾም ወቅት የሚሆኑ መልካም ልምዶች

በዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት ልንከተላቸው የሚገባን ሦስት ተጨባጭ መልካም ልምዶችን ኢየሱስ ይጠቁመናል፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅድሚያ በጣም መጥፎ የሆነውን “የመኮነን ባሕሪይ” በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት ራሳችንን ማራቅ ይኖርብናል ብለው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ይህ የመኮነን ባሕሪይ እኛ ሳናውቀው በህይወታችን ውስጥ ጣልቃ የሚገባ ልማድ ነው። ሁሌም የሚጀምረው በዚሁ መልኩ ነው! እንዲሁም ቀለል ባለ መልኩ ውይይት በምናደርግበት ወቅት "ምን እንዳደረገ ተመልክተኸዋል?" በማለት ቀለል አድርገን እንጀምራለን። በዚህም ተግባራችን ሌላውን እንኮንናለን። በቀን ለስንት ጊዜ ያህል ሰዎችን እንደ ምንኮንን እናስብ! ግን እኮ እባካችሁን! እኛ ሁላችንም መጥፎ የሆንን ፈራጆች ነን አይድለ! አዎን ሁላችንም እንዲሁ ነን! ይህ ደግሞ ቀለል ባለ ውይይት ይጀምራል፣ ከዚያም ቀስ በቀስ ሌላውን በመኮነን ይጠቃለላል፣ በዚህም መልኩ ቀስ በቀስ የሌሎች ሰዎች መልክና ቁመና ላይ በምላሳችን አማካይነት ቀዶ ጥገና ማድረግ እንጀምራለን! ይህ ደግሞ ከሁሉም በላይ አስቀያሚ የሆነ ነገር ነው!

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በሰዎች ላይ መፍረድ የለብንም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመጨረሻ ደግሞ ምንም እንኳን በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ምሕረት ማድረግ ተገቢ እንደ ሆነ ገልጸው ምክንያቱም እኛ እርስ በእርሳችን በምናሳየው መልካም ተግባር ልክ ነው ጌታ ለእኛ ለእያንዳንዳችን የሚያደርግልን ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

18 March 2019, 15:47
ሁሉንም ያንብቡ >