ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በትህታና እና በየዋሕነት ማገልገል የሰዎች ልብ እንዲከፈት ያደርጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በዛሬው እለት ማለትም በጥር 30/2011 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ትሁት እና የዋህ በሆነ ልብ የሚሰጥ አገልግሎት የሌሎች ሰዎችን ልብ ለመክፈት ይረዳል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 6፡7-13 ላይ ተወስዶ በተነበበው የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሌሎች ሰዎችን ልብ ለመክፈት እና መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጡ ለማድረግ እና ለማስቻል የዋሕነት፣ ትህትና እና የድህነት መንፈስ፣ በተጨማሪም የኢየሱስን ፈለግ መከተል ያስፈልጋል እንጂ ከሌሎች የተሻልን አድርገን ራሳችንን መቁጠር ወይም ደግሞ የግል ሰብዓዊ ፍላጎቶቻችንን ብቻ ለሟሟላት አስበን መንቀሳቀስ ግን የለብንም ብለዋል።

ኢየሱስ ወደ እዚህ ምድር የመጣው ለመፈወስ እንደ ሆነ ሁሉ ዛሬም ቢሆን በእኛው ውስጥ ስር መሰርቱን የዘረጋውን “የመጀመሪያውን ኃጢኣት” እንዲፈውሱ ደቀ-መዛሙርቱን ይልካቸዋል፣ “የኃጢኣት ስርዬት” ማለት ደግሞ አዲስ ሰው ማድረግ ማለት ነው፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ እኛን ከእነ ሥር መሰረታችን ፈጠረን፣ ከዚያም በእርሱ ትምህርት ላይ ተመርኩዘን ወደ ፊት እንድንጓዝ አደረገ፣ የእርሱን አዳኝ የሆነ አስተምህሮ ተቀብለን ወደ ፊት እንድንጓዝ አዘዝን ብለዋል። ኢየሱስ ደቀ-መዛሙርቱን በላካቸው ጊዜ የሰጣቸው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ሰዎች መንፈሳዊ ለውጥ ያመጡ ዘንድ እንዲረዱዋቸው ነበር የላካቸው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .

በመጀመሪያ መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያመጡ ማደርግ ማለት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ልባቸው እንዲገባ ለማድረግ ልባቸውን በመክፈት እንዲድኑ ማድረግ ማለት ነው።  ይህም ልብን ይከፍታል፣ በዚያ ውስጥ ያሉ  ሌሎች ነገሮች እንዲታዩም ያደርጋል። ልብ ከተዘጋ ግን ሊፈወስ አይችልም። አንድ ሰው በጽኑ ከታመመ ወደ ሐኪም መሄድ የማይፈልግ ከሆነ አይፈውስም። ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ በቅድሚያ ያላቸው ነገር ቢኖር “መንፈሳዊ ለውጥ አምጡ፣ ልባችሁንም ክፈቱ” በማለት ነበር የተናገራቸው። ምንም እንኳን እኛ ክርስቲያኖች  ብዙ ጥሩ ነገሮችን ብንፈጽምም ነገር ግን ልባችን ዝግ ከሆነ ግን ለይስሙላ ላይ ላዩን ቀለም እንደ ተቀባ እቃ እንሆናለን ማለት ነው።

እረኛ የበጎቹን ወተት መፈለግ የለበትም

ይሁን እንጂ ሰዎች መለወጥ እንዳለባቸው ማስተማር አስፈላጊ ነው። ኢየሱስን ለመገናኛት ደግሞ የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለን “ለመንገዳችሁ ከበትር በቀር እንጀራም ቢሆን፣ ከረጢትም ቢሆን፣ መሐለቅም በመቀነታቸው ቢሆን እንዳትይዙ” በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ማለት ደግሞ ተልዕኮዎቻችንን በድህንት መንፈስ ማከናውን ማለት ነው ብለው “ደቀ-መዝሙር ወይም እረኛ መሆን ማለት የበጎቹን ወተት አለመፈለግ ማለት ነው” ብለዋል።

በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የክብር ቦታዎችን መፈለግ ፈውስን አያመጣም

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለን አንድ እረኛ ወይም ደቀ-መዝሙር “የድህነት መንፈስ፣ ትህትናና የየዋሕነት መንፈስ” ያስፈልገዋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በምትሄዱበት ቦታ ሁሉ ሰዎች የማይቀበሉዋችሁ ከሆነ ከዚያ ወጣታችሁ ወደ ሌላ አገር ሂዱ ብሎዋቸው እንደ ነበረ አስታውሰው የአንድ ትክክለኛ ወይም እውነተኛ ደቀ-መዝሙር ባሕርይ ግን የድህነትን መንፈስ መላበስ፣ ትሁት እና የዋህ መሆን ግን ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

07 February 2019, 14:23
ሁሉንም ያንብቡ >