ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “እምነት በዓለም ላይ ያለውን የክፍፍል መንፈስ ያሸንፋል”።

አንድ ሰው በሌላው ላይ ምቀኝነትን የማያስብ ከሆነ፣ ሊያጠቃውም የማይነሳ ከሆነ በእርግጥ ያ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ የቀረበ መሆኑን እገነዘባለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው፣ ወንድሙን የሚወድ፣ በሚወደውና ዕለት ዕለት በሚያገኘው ወንድሙ በኩል እግዚአብሔርንም ይወዳል ብለዋል። የዚህ ዓለም መንፈስ የሚሸነፈው ከእምነት በምናገኘው ሃይል እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ጥር 2 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ቅድስት ማርታ ጸሎት ቤታቸው ውስጥ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ፣ መስዋዕተ ቅዳሴውን ለተካፈሉት ካህናት ደናግልና ምዕመናን፣ በዕለቱን በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባት መሠረት በማድረግ ስብከታቸውን አቅርበዋል። በዚህ ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደገለጹት እግዚአብሔርን ለመወደድ ወንድሞቻችንን መውድድ፣ መልካም ቢሆንም ባይሆኑ፣ ለጠላትም ቢሆን በመጸለይ ለምቀኝነትና ለቅናት መንፈስ እድልን መስጠት እንደማያስፈልግ አሳስበዋል። ይህን ካደረግን እምነት በዓለም ላይ ያለውን የክፍፍል መንፈስ ያሸንፋል ብለዋል።   

ከመጀመሪያው ዮሐንስ መልዕክት በምዕ. 4. 19 እና በምዕ. 5. 4 በተነበበው የመጀመሪያ ንባብ ላይ በማስተንተን ስብከታቸውን ያቀረቡት ቅዱስነታቸው፣ ሐዋርያው ዮሐንስ በዚህ መልዕክቱ ስለ ዓለማዊ ነገሮች እንደሚናገር ገልጸው፣ ሐዋርያው በመልዕክቱ በምዕ. 5. ቁጥር 4 ላይ “ከእግዚአብሔር የተወለደ ዓለምን ያሸንፋል። የሚያሸንፈውም በእምነት ነው” ሲለን በየዕለቱ ከሚያጋጥመን ከዚህ ሐሰተኛ ዓለማዊ መንፈስ ጋር የምናደርገውን ውጊያ በማስመልከት እንደሆነ ተናግረው፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ግን እውነተኛ እንደሆነ አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም የዚህ ዓለም መንፈስ ከንቱ፣ ሃይል የሌለው፣ ጠንካራ መሠርትም ስለሌለው በቀላሉ የሚወድቅ መንፈስ መሆኑን አስረድተዋል።

ዓለማዊ መንፈስ ሁል ጊዜ ቤተሰብንና ማሕበረሰብን የሚከፋፍል መንፈስ ነው፣

ሐዋርያው ዮሐንስ በመልዕክቱ የእግዚአብሔርን መንፈስ በግልጽ ለማወቅ የሚያግዘንን መንገድ ሲያመላክተን፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ካለ መልካም የሆኑ ነገሮችን ማከናወን እንችላለን። ይህንን ማወቅ የምንችለው በየእለታዊ ኑሮአችን መካከል እንደሆነ እንመለከታለን። ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና፣ 1ኛ የዮሐንስ መልዕክት በምዕ. 4. ቁጥር 20። በዚህ የዮሐንስ መልዕክት ላይ ሲያስተነትኑ፣ የምናየውን መውደድ፣ በእጆቻችንም መዳሰስ መቻል ስንል በተጨባጭ ስለማነየው ነገር መናገራችን አይደለም ብለዋል።

በተጨባጭ በምናየው ነገር በኩል እግዚ አብሔርን መውደድ ካልቻልን በእርግጥ እግዚአብሔርን እንወደዋለን ማለት አንችልም። የዚህ ዓለም መንፈስ ግን ገና የምናያቸውን፣ አብረውን የሚኖሩ ቤተሰቦቻችንን፣ ማሕበረሰባችንን እንኳን እንዳንወድ በማድረግ በመካከላችን ክፍፍልን ይፈጥራል ብለዋል። ይህ መከፋፈልም ጥላቻንና ጦርነትን የወልዳል ብለዋል። ሐዋርያው ዮሐንስም አንድ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን የሚጠላ ከሆነ ሐሰተኛ ነው፣ ይህም ሰውም በዚህ ዓለም መንፈስ የተዋጠ ሐሰተኛና ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ የዮሐንስ መልዕክት ላይ ባደረጉት አስተንትኖአቸው ወንድማችንን የማንወድባቸው ሦስት ምልክቶች በሚገባ ለማወቅ የሚከተሉን ጥያቄዎች ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል ብለዋል። እነርሱም፣ ጠላቶቻችንንም ጨምሮ ለሰዎች በሙሉ እጸልያለሁ? ለእነዚህ ሰዎች በሙሉ የማልጸልይላቸው ከሆነ እነርሱን አለመውደዴን መርዳት ይኖርብኛል። በውስጤ ወይም በልቤ ውስጥ የምቀኝነትና የቅናት መንፈስ ካለብኝ፣ ሰዎችን አለመውድውዴን ማወቅ ይኖርብኛል። ይህ መንፈስ በውስጤ ማደጉን ከተረዳን አውልቀን መጣል ይኖርብናል። በውስጣችን እንዲያድግ ዕድል መስጠት የለብንም። በብዛት የተለመደውና በየዕለቱ የሚያጋጥመን ደግሞ እግዚ አብሔርን እወዳለሁ እያልን ወንድሞቻችንን የምናጠቃ ከሆነ፣ ምቀኞች የምንሆን ከሆነ፣ ይህን ወንድማችንን እንወደዋለን ማለት አንችልም በማለት አስረድተዋል።

የዚህን ዓለም መንፈስ ለመዋጋት እምነት ያስፈልጋል፣

አንድ ሰው በሕይወቱ ሌላውን ለማጥቃት የማያስብ ከሆነ በእርግጥ ያ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ የቀረበ መሆኑን እገነዘባለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው፣ ወንድሙን የሚወድ፣ በሚወደውና ዕለት ዕለት በሚያገኘው ወንድሙ በኩል እግዚአብሔርንም ይወዳል ብለዋል። የዚህ ዓለም መንፈስ የሚሸነፈው ከእምነት በምናገኘው ሃይል እንደሆነ አስገንዝበዋል።

10 January 2019, 16:23
ሁሉንም ያንብቡ >