ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት፣  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የግድ የለሽነት ባሕል የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደሚቃረን ገለጹ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱንና ሕዝቡን ስለ ፍቅርና ስለ ርሕራሄ እንዲሁም ስለ ሌሎች በርካታ መልካም ነገሮች እንዳስተማረ ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ደቀ መዛሙርቱ ከሕዝቡ ይልቅ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደፈለጉት፣ ይህም የሆነበት ሌሎችን ጠልተው ሳይሆን፣ ወይም በሌሎች ላይ ክፋትን በማሰብ ሳይሆን በኢየሱስና በሕዝቡ መካከል ልዩነት በመፍጠራቸውና የፍቅርን ትርጉም ባለማወቃቸው ነው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ታሕሳስ 30 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ቅድስት ማርታ የጸሎት ቤታቸው ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴው ለተካፈሉት ካህናት ደናግልና ምዕመናን በዕለቱ የተነበበውን የወንጌል ንባባት መሠረት በማድረግ ስብከታቸውን አቅርበዋል።

ከማር. ምዕ. 6, 34-44 ተውስዶ በተነበበውና፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሳ እንደመገባቸው የሚተርክ የወንጌል ክፍል ላይ በማስተንተን ባሰሙት ስብከታቸው እግዚአብሔር እንደሚያፈቅረን፣ ፍቅሩም በርህራሄና በምህረት የተሞላ እንደሆነ ገልጸው፣ ነገር ግን እኛ መልካሞች ብንሆንም፣ የእኛን ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች የግድ የለሽነት ስሜት ያድርብናል ብለዋል። ምናልባትም ይህ የሚሆንበት ምክንያት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ውስጥ ስላልገባ ይሆናል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት  ቤታቸው ባቀረቡት የወንጌል አስተንትኖአቸው ወቅት፣ ለዘለዓለማዊ ዕረፍት የተጠሩትን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጆርጆ ዙርን አስታውሰው፣ ሊቀ ጳጳስ ጆርጆ ዙር ከዚህ በፊት በኦስትሪያ የቅድስት መንበር እንደራሴ ሆነው ማገልገላቸውን አስታውሰዋል።

እግዚአብሔር ከሁሉ አስቀድሞ ወድዶናል፣

ፍቅር ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሆነ እርስ በእርሳችን መዋደድ ያስፈልጋል ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ውስጥ እንዴት እንደሚገለጥ የጻፈውን በመጥቀስ፣ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከው የእርሱን የፍቅር ሕይወት መጋራት እንድንችል ስለፈለገ ነው ብለው፣ እግዚአብሔር ከሁሉ አስቀድሞን የወደደን የፍቅር ምስጥርም ይህ ነው በማለት እግዚአብሔር ለእኛ የገለጠልንን ቀዳሚ ፍቅር ግልጽ አድርገዋል። እግዚአብሔር ይህን ያደረገበትም በመካከላችን ፍቅር እንደሚጎል ስለተገነዘበ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ተገንዝበን የእርሱ ምስክሮች እንድንሆን ስለፈለገ ነው ብለው፣ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ አማካይነት የገለጠልን የመጀመሪያ ፍቅር፣ ድነትን እንድናገኝ፣ ሕይወታችን ታድሶ ትርጉም እንዲኖረው ለማድረግ ነው በማለት አስረድተዋል።

በጢሮስ ሐይቅ ላይ ኢየሱስ ለሕዝቡ ራርቶአል፣

በማር. ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት እንጀራና በሁለት ዓሳ እንደመገባቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ ኢየሱስም ይህን ያደረገበት ምክንያት ከጀልባቸው ወርደው፣ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ሆነው፣ በጢሮስ ወንዝ ዳርቻ ብቻቸውን ተቀምጠው ለነበሩት ሰዎች ስለ ራራላቸው ነው ብለዋል።

የእግዚአብሔር የፍቅር ልብ በመከራ የወደቁትን ሰዎች እየተመለከተ በዝምታ ማለፍ አይቻለውም። ፍቅር እረፍት የለውም፣ ፍቅር ግድየለሽ አይደለም፣ ፍቅር ርኅሩህ በመሆኑ ልብን በመቀስቀስ ምሕረትንም ያደርጋል፣ ለሌሎችም ይጨነቃል።

ደቀ መዛሙርትም ለሌሎች ምግብን ለመፈለግ ተሰማርተዋል፣

ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱንና ሕዝቡን ስለ ፍቅርና ስለ ርሕራሄ እንዲሁም ስለ ሌሎች በርካታ መልካም ነገሮች እንዳስተማረ ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ደቀ መዛሙርቱ  ከሕዝቡ ይልቅ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደፈለጉት፣ ይህም የሆነበት ሌሎችን ጠልተው ሳይሆን፣ ወይም በሌሎች ላይ ክፋትን በማሰብ ሳይሆን በኢየሱስና በሕዝቡ መካከል ልዩነት በመፍጠራቸውና የፍቅርን ትርጉም ባለማወቃቸው  እንደሆነ ነው ብለዋል። በመሆኑም ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ልብ እውቆ በሽፍራው ለተሰበቡት በርካታ ሰዎች የሚበላ ምግብን በማከፋፈል የፍቅርና የርሕራሄ ልብ እንዲኖራቸው ማድረጉን አስረድተዋል።

የፍቅር ተቃራኒ ጥላቻ ሳይሆን ወገናዊነት ነው፣

የእግዚአብሔር ፍቅር ለሰዎች ቅድሚያ አለው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህን የገለጠውም ርህራሄንና ምሕረትን በግልጽ በማሳየቱ ነው ብለው የፍቅር ተቃራኒ ጥላቻ ቢሆንም በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ ጥላቻ ሳይሆን በሰዎች መካከል ልዩነትን ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል። ብዙን ጊዜ ከሰዎች በኩል በእግዚአብሔር ርህራሄና ምሕረት ላይ የሚሰነዘር ቅራኔ በሰዎች መካከል ልዩነትን በመፍጠር የሚደረግ ማበላለጥ እንደሆነ አስረድተዋል። ለራስ ወይም ለምናውቃቸው ወይም ለምንወዳቸው ብቻ መልካም ማድረግን ካወቅንበት የማናውቃቸውንና በተለያዩ ማሕበራዊ ችግሮች ወድቀው የሚገኙትንም ማስታወስ ይስፈልጋል ብለው እግዚአብሔር ግን ሰዎችን አንዱን ከሌላው ሳያበላልጥ ለሁሉም ምሕረቱንና ርህራሄውን በገሃድ እንዳሳየ ገልጸዋል።

08 January 2019, 16:07
ሁሉንም ያንብቡ >