ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (ANSA)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በእምንት በመበርታት ለገና በዓል መዘጋጀት ይኖርብናል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በታኅሳስ 01/2011 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “በዚህ አሁን በመጀመርነው የሁለተኛው የስብከተ ገና ሳማንት የገናን በዓል በሚገባ ማክበር የምያስችለንን ዝግጅት ማደርግ እንድችል ጸጋውን እንዲሰጠን እግዚኣብሔርን ልንለምነው እንደ ሚገባ” ገልጸው እምነትን መጠበቅና እምነትን መንከባከብ ግን ቀላል የሆነ ነገር አይደለም ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“የገናን በዓል እውነተኛ በሆነ መልኩ ማክበር ይገባል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 5፡17-26 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ኢየሱስ አንድ ሽባ የሆነ ሰው መፈወሱን በሚተርከው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከታቸው እንደ ግለጹት በወቅቱ አንድ ሽባ የሆነ ሰው ይዘው ወደ ኢየሱስ የመጡ ሰዎች ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ኢየሱስ ያስተምር ወደ ነበረበት ቤት ሽባውን ሰው ለማስገባት ስላቃታቸው የቤቱን ጣርያ ሸንቁረው አካል ጉዳተኛ የነበረውን ሰው ወደ ኢየሱስ እንዳቀረቡት እና ኢየሱስም የሰዎቹን እምነት ተመልክቶ አካል ጉዳተኛ የነበረውን ሰው እንደ ፈወሰው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “እምነት ድፍረትን ያመጣል ይህ አካሄድ ደግሞ የኢየሱስን ልብ መንካት የምንችልበት መንገድ ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

ምስጢራዊ በሆነ መልኩ በልጁ አማካይነት ሰው በሆነው እግዚኣብሔር ላይ እምነት እንዲኖረን ይጋብዘናል። በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ምንመለከተው ዛሬውም ቢሆን እምነት የኢየሱስን ልብ የመንካት አቅም አለው። ጌታ ብዙን ጊዜ በአስተምህሮው እመነት እንዲኖረን በመጋበዝ በጽኖት አስተምሮናል። “እመነታቸውን ተመልክቶ. . . ” ይላል ቅዱስ ወንጌል። ኢየሱስ የሚመለከተው እምነታችንን ነው- ምክንያቱም ብርታት እንዲኖረን ይፈልጋል፣ ጣራውን ቀደው የታመመውን ሰው በኢየሱስ ፊት ለማድረስ የሚያስችል ጥንካራ እና በብርታት የተሞላ እምነት ይፈልጋል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱ እነዚያ ሰዎች እምነት ነበራቸው። እነርሱ ይህ የታመመ ሰው በኢየሱስ ብፊ ቢቀርብ እንደ ሚድን ጠንቅቀው ያውቁ ነበር።

የገናን በዓል ዓለማዊ በሆነ መንፈስ ማክበር ተገቢ አይደለም

“ኢየሱስ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱትን እና ጠንካራ እመንት ያላቸውን ለምሳሌም የመቶ አለቃ የነበረው ሰው አገልጋዩን እንዲፈውስ በታላቅ እምነት ኢየሱስን እንደ ለመነው፣ ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት በትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት የነበረች አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፍታ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ የለመነችውን ሴት እመንት ወይም ደግሞ የቀሚሱን ጫፍ እንኳን ብነካ እፈወሳለሁ በማለት በታላቅ እምነት የኢየሱን ልብስ ነክታ ለብዙ አመታት ደም ሲፈሳት ስያደርጋት ከነበረ በሽታ የተፈወሰችውን ሴት እምነት ኢየሱስ ማድነቁን” በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተቃራኒው ደግም በጣም ትንሽ የሚባል እምነት የነበራቸውን ለምሳሌም ጴጥሮስን ይወቅስ እንደ ነበረ ገልጸው በእመነት ሁሉንም ነገር ማከናወን እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው በአጽኖት ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

አሁን ባለንበት በሁለተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ላይ ዛሬ ይህንን ጸጋ እንዲሰጠን በመጠየቅ መጪውን የገና በዓል በታላቅ እምነት ለማክበር የሚያስችለንን እምነት እንዲሰጠን እንጠይቅ። እርግጥ ነው ሁላችንም እንደ ምናውቀው ብዙን ጊዜ የገና በዓልን በታላቅ እምነት በማክበር ላይ እንደ ማንገኝ እሙን ነው፣ ብዙን ጊዜ የገናን በዓል የምናከብረው ዓለማዊ ወይም አረማዊ በሆነ መንፈስ ነው፡ ነገር ግን ጌታ የገናን በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት በእመንት ተሞልተን እንድናከብር ነው የሚጠይቀን፣ በዚህ በያዝነው ሁለተኛው የስብከተ ገና ሳምንት የገናን በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት እናከብር ዘንድ እንዲረዳን ጸጋውን እንዲሰጠን ልንጠይቅ ይገባል። እምነትን መጠበቅ ቀላል የሆነ ነገር አይደለም፣ እምነታችንን ከጥቃት መከላከል ቀላል የሆነ ነገር አይደለም፣ በፍጹም ቀላል አይደለም።

 

እምነት ከልባችን ሊመነጭ ይገባል

በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ ዘጠኝ ውስጥ የተጠቀሰው እና ዓይነ ስውር የነበረው ሰው ታላቅ የሆነ እምነት ስለነበረው እና ኢየሱስ መስህ መሆኑን በሕዝቡ ፊት በመመሰከሩ የተነሳ መፈወሱን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱሰንታቸው እምነታችንን በአደራ ለእግዚኣብሔር በመስጠት በእመነታችን ላይ የሚጋረጡትን ማነኛውም ዓይነት ዓለማዊ ከሆኑ ፈተናዎች እምነታችንን መከላከል እንደ ሚኖርብን ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

በእዚህ በሁለተኛ የስብከተ ገና ሳምንት ውስጥ ባሉ ቀናት በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 9 ላይ የተጠቀሰውን እና ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ኢየሱስ እንደ ፈወሰው የሚገልጸውን ታሪክ በጣም ውብ የሆነ ታሪክ በሆኑ የተነሳ ደጋግመን ልናነበው የገባል። “ጌታ ሆይ በአንተ አምናለሁ” የሚለውን ቃል በልባችን እንዲሰርጽ ይረዳል። ትንሽ የሆነችውን እምነቴ እንዳሳድግ እርዳኝ። እምነቴን ከዓለማዊነት፣ ከአጉል እምነቶች፣ የእመንት ካልሆኑ ነገሮች እንድከላከል እርዳኝ። በአንተ እምነት እንዲኖረኝ እርዳኝ።

 

10 December 2018, 16:35
ሁሉንም ያንብቡ >