ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቅዱስ ዮሴፍ በዝምታ ተግባሩን ያከናወነስ ሰው ነበር”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 09/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መሳዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል 1፡18-24 ላይ በተጠቀሰው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ በተወሰደው “ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ የሆነ ሰው ስለነበረ እርሷን ልያጋልጣት አለፈለገም ነገር ግን በስውር ሊተዋት ፈልገ፣ እርሱ ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ። የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ” በሚለው የጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ቅዱስ ዮሴፍ በዝምታ ማርያምን የረዳት ሰው እንደ ነበረ” አስታውሰዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
“ቅዱስ ዮሴፍ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅና በጸጥታ ውስጥ ሆኖ ማርያምን ያገዘ የሕልም ሰው ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ዮሴፍን በሚገባ ሊገልጹት የሚችሉ ሁለት ባሕሪያትን ቅዱስነታቸው ጠቁመዋል።
የጥሩ ወላጆች ጥበብ
በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ቅዱስ ዮሴፍ “ጻድቅ፣ ሕግን አክባሪ፣ ትጉ ሠራተኛ፣ ትሁት እና ማርያምን የሚወድ እጮኛ’ እንደ ነበረ እንረዳለን በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማርያም ማርገዟን ባወቀበት ወቅት መጀመሪያ ላይ ሁኔታውን በጥልቀት ለመረዳት ስያዳግተውና ሲቸገር እንመለከታለን፣ በዚህም ምክንያት የተነሳ ማርያምን “በስውር ሊተዋት መፈለጉን” እናያለን፣ ነገር ግን በተቃራኒው ይህንን ሁሉ ውዝግብ መፍታት የሚችል የእግዚኣብሔር ተልዕኮ ሲገለጥለት እንመለከታለን ብለዋል። እናም ዮሴፍ ተልዕኮውን ይቀበላል፣ የእርሱን ሚና በመጫወት የእግዚአብሔርን ልጅ ያሳድጋል፣ ነገር ግን እርሱ ይህንን ሁሉ ነገር የምያደርገው “በዝምታ፣ ሳይፈርድ፣ ምንም ነገር ሳይናገር እና ሳይነጫነጭ ነበር” ብለዋል።
ብዙን ጊዜ ብዙ የቤተሰብ አባላት በዝምታ የመጠበቅ ብቃት እንደ ሚጎላቸው በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሕጻናት ስህተት በሚፈጽሙበት ወቅት ሳይቀር በዝምታ እና በትዕግስ ማሳደጋችንን ልንቀጥል ይገባል እንጂ መጮኽ ተገቢ አይደለም ብለው ከመናገራችን በፊት ምን መናገር እንዳለብን ጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል፣ ይህም ጥበበኞች እንድንሆን ይረዳናል ብለዋል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ውስጥ እንደ ተጠቀሰው እግዚኣብሔር ለእኛ በሕላማችን እንደ ሚናገር በመግለጽ ስብከታችውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ የቅዱስ ዮሴፍን ታሪክ ማውሳት እንደ ሚቻል ገልጸው ቅዱስ ዮሴፍ ሕልመኛ የሆነ ሰው ሳይሆን ሕልም የምያልም ሰው መሆኑን ገልጸው እርሱ ተጨባጭ እና እውነተኝ የሆነ ሕልም እንደ ነበረው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
 

18 December 2018, 16:05
ሁሉንም ያንብቡ >