ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቤተ ክርስቲያን ብዙ ትእይንቶችን ሳታሳይ በዝምታ እያደገች ትገኛለች!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በዛሬው እለት ማለትም በሕዳር 06/2011 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከሉቃስ ወንጌል (17፡20-25) ላይ ተወስዶ በተነበበው የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ባደርገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ቤተ ክርስቲያን “በቅዱስ ቁርባን እና በመልካም ተግባሯ አማካይነት በዓይን ሊገቡ የሚችሉ ብዙ ትእይንቶችን ሳታሳይ በዝምታ እያደገች ትገኛለች” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቤተ ክርስቲያን “በትህትና፣ በዝምታ፣ በምስጋና፣ በመስዋዕተ ቅዱስ ቁርባን፣ በወንድማማችነት መንፈስ፣ ሁሉም የሚዋደዱበት እና የማይነጣጠሉበት ሕብረት በመመስረት በማደግ ላይ እንደ ሆነች” የጠቀሱት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር መንግሥት ለታይታ የሚደረግ ትእይንት አይደለም ብለዋል።

መልካም ተግባሮች ለዘገባ አይመቹም

ምንም እንኳን በዜና መልክ የሚገለጽ ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን “በቅዱስ ቁራባን እና በመልካም ስራዎቿ” እንደ ምትገለጽ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የክርስቶስ ሙሽራ የሆነቺው ቤተ ክርስቲያን እንደ አይሁዳዊያን ጥሩምባ ሳትነፋ በዝምታ መልካም ፍሬዎችን እያፈራች እንደ ምትገኝ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለመግለጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ጌታ የዘሪውን ምሳሌ በመጠቀም ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደ ምታድግ አስረድቶናል። ዘሪው ዘሩን ይዘራል፣ ዘሩም በቀን ይሁን በማታ እያደገ ሄደ -የምያበቅለው እግዚኣብሔር ነው - ከዚያም እኛ ሁላችን ፍሬውን እናያለን። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ ነው፣ በቅድሚያ ቤተ ክርስቲያን በዝምታ በድብቅ ታድጋለች፣ ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አካሄድ ነው። ይህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት ይገለጻል? የሚገለጸው በመልካም ተግባራት ነው - ምክንያቱም ሰዎች ይህንን በጎ የሆነ ተግባሩዋን በማየት ለሰማያዊ አባታችን ምስጋናን ያቀርባሉ - ኢየሱስ እንዳለው - ይህም የሚገለጸው በሚደርገው የምስጋና መስዋዕት ነው - ይህም የቅዱስ ቁርባን መስዋዕት ነው።  ቤተ ክርስቲያን በዚያ ውስጥ ትገለጻለች፣ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ቁርባን እና በመልካም ሥራ ትገለጻለች።

 

ቤተ ክርስቲያን የምያማልል ፈተናዎች ይገጥሟታል

“ቤተ ክርስቲያን በምስክርነት፣ በጸሎት፣ በውስጧ ለሚገኘው መንፈስ ቅዱስ ትኩረት በመስጠት” እያደገች እንደ ምትሄድ በአጽኖት የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንንም ማድረግ የሚገባት እንዲሁ ለይስሙላ እና ለታይታ መሆን እንደ ማይገባው ገልጸው ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳን አጋዥ የሆኑ ሰዎች ብያስፈልጓትም ነገር ግን “የቤተ ክርስቲያን እድገት የሚመነጨው በዝምታ፣ በድብቅ፣ በመልካም ሥራ በተደገፈ መልኩ እና የፋሲካ ምስጢር በሆነው ለእግዚኣብሔር የሚቀርብ የምስጋና መስዋዕት በሆነው በቅዱስ ቁርባን አማካይነት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

በምያማልሉ ነገሮች ተፈትነን እንዳንወሰድ ጌታ ይረዳናል። እኛ ቤተ ክርስቲያን በደንብ እንድትታይ እንፈልጋለን፡ ቤተ ክርስቲያን ጎልታ እንድትታይ ምን ማድረግ ይኖርብናል? አንዳንድ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በዝምታ፣ በበጎ ተግባር እና በድብቅ እንድታድግ ሳይሆን ነገር ግን በዓላትን በማዘጋጀት እንድታድግ የሚል ፈተና ውስጥ እንገባለን።

የዓለም መንፈስ ሰማዕትነትን አይታገስም

“ያለመታደል ሆኖ አሁን ባለንበት ዓለማችን ታላላቅ ትእይንቶችን፣ ዓለማዊነትን፣ በሰዎች ለመታየት በመፈለግ ወደ ፈተና ውስጥ እንገባለን” በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስም በተመሳሳይ መልኩ መፈተኑን ማስታወስ እንደ ሚገባ ገልጸው ኢየሱስ ግን ሁሉንም ነገር ወደ ኋላው አሽቀንጥሮ በመጣል “የወንጌል ስብከት፣ የጸሎት እና የመልካም ሥራ መንገድ ተከትሎ ማለፉን እና በስተመጨረሻም የመስቀል እና የስቃይ መንገድ ላይ እንደ ተጓዘ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

መስቀል እና ስቃይ። በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን የምታድገው ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገው ባቀረቡ በሰማዕታት ደም ነው። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰማዕታት አሉ። የምያጓጓ ዜናዎች ግን ሆነው ቀርበው አያውቁም። ዓለማችን ይህህንን መስዋዕትነት ደብቃ ይዛለች። የዓለም መንፈስ ሰማዕት የሆኑ ሰዎች እንዲታወቁ አይፈልግም፣ ነገር ግን ዓለማችን የሰማዕታትን ዜና ደብቃ ታቆያለች ብለዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
15 November 2018, 15:54
ሁሉንም ያንብቡ >