ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ ወደ መንግሥቱ ይጋብዘናል፣ እንቢ እንዳንለው መጠንቀቅ ያስፈልጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ምያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት ማለትም በጥቅምት 27/2011 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 14፡15-24 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና አንድ ሰው “ታላቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን መጋብዙን፣ ነገር ግን የተጋበዙ ሰዎች በተለያዩ ምክንያት የተነሳ ግብዣውን መታደም አለመቻላቸውን በመግለጽ ግብዣው ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን” በሚያመልክተው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ኢየሱስ በመንግሥቱ የተዘጋጀውን ግብዣ እንድንታደም ሁላችንንም ይጋብዘናል፣ እኛም የቀረበልንን ግብዣ እንቢ እንዳንል መጠንቀቅ ይገባናል” ብለዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“ብዙን ጊዜ የእግዚኣብሔር መንግሥት እንደ አንድ ግብዣ ተደርጎ እንደ ሚመሰል” በመግለጽ ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በዚህ ግብዣ ላይ እንድንሳተፍ ሁላችንንም እንደ ሚጋብዝ የገለጹት ቅዱስነታቸው ነገር ግን እኛ አንድ አንድ ጊዜ የራሳችንን ምክንያቶች በመፍጠር ግብዣውን ችላ እንደ ምንል ገልጸው “ኢየሱስ መልካም ነው፣ ነገር ግን ፍታዊ የሆነ አምላክ መሆኑም ሳይቀር ማስታወስ ይገባል ብለዋል።

በተላንትናው ዕለት ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 14 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና “አንድ ፈሪሳዊ ሰው ኢየሱስን በቤቱ ምሳ በጋበዘው ወቅት፣ ተጋባዥ እንግዶች የክብር ሥፍራ ለመያዝ የሚያደርጉት እሽቅድድም ኢየሱስ በተመለከተ ጊዜ ግብዣውን ላዘጋጀው ፈሪሳዊ ሰው ‘አንተ ግን ምሳ ስታዘጋጅ ብድርህን መክፍል የማይችሉትን ድኾች መጋበዝ ይኖርብሃል` ብሎ የተናግረውን ቃል በመንደርደሪያነት በመጠቀም ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት (በጥቅምት 27/2011 ዓ.ም ) በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ደግሞ በዚያው ግብዣ ላይ ከነበሩ ሰዎች አንዱ ይህንን የኢየሱስን ቃል ሰምቶ ‘በእግዚአብሔር መንግሥት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው’ ብሎ ምላሽ እንደ ሰቶ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ሁለት ዓይነት እንቢታዎች እንደ ሚታዩ በመገልጸ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  “አንድ ሰው ታላቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን እንደ ጠራ፤ ነገር ግን ተጋባዥ እንግዶች “አንቢየው አልችልም አልመጣም” ከማለት ይልቅ ሁሉም ተጋባዣ እንግዶች በአንድነት  በሰለጠነ መልኩ ማመካኘት መጀመራቸውን” በመግለጽ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  የግብዣው አዘጋጅ መልእክተኛውን “ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች ፈጥነህ ውጣ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ ወደ ግብዣው ስፍራ አስገባቸው” ብሎ መናገሩን የዕለቱ ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚገልጽ ያስታወሱት ቅዱስናታቸው ይህም የመጀምርያው ዓይነት እንቢታ ነው ብለዋል።

“የዛሬው ቅዱስ ወንጌል የሚጠናቀቀው ከኢየሱስ አፍ በወጣው እና ሁለተኛው ዓይነት እንቢታ በማመላከት ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ ለሚያቀርብልን ጥሪ እንቢ የሚል ምላሽ ስንሰጥ፣ ኢየሱስ ሌላ እንድል የሰጠናል፣ አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ፣ ሦስት ጊዜ . . .ዐራት፣ አምስት ጊዜ . . .ነገር ግን ከዚያን በኋላ ኢየሱስን ራሱ እንቢ ማለት እንጀምራለን”  ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

እኛን በጣም ሊያሳስበን የሚገባው የዚህ ዓይነቱ እንቢታ ነው፣ አንዳንድ ጊዜ እኛን የሚጠራን ኢየሱስ ራሱ ነው፡ ከእርሱ ጋር እንድንደሰት ይጠራናል፣ ከእርሱ አጠገብ እንድንሆን ይጠራናል፣ ሕይወታችንን እንድንቀይር ይጠራናል። እርሱ በጣም ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹን እንደ ሚፈልግ ነገር ግን የእርሱ ቅርብ የተባሉ ጓደኞች እንቢየው እንዳሉ አድርጋችሁ አስቡት! ከዚያም እርሱ የታመሙትን . . .ወዘተ ጠራ እነርሱም መጡ፡ ምን አልባት አንዳንድ ሰው እንቢ ሊል ይችል ይሆናል። ወደ እርሱ እንድንመለስ፣ የልግስና ተግባራትን እንድንፈጽም፣ እንድንጸልይ እርሱን እንድንገናኝ ኢየሱስ እኛን ስንት ጊዜ ነው የሚጠራ! “ነገር ግን ጌታ ሆይ ሥራ አለኝ፣ ጊዜ የለኝም፣ አዎ፣ ዛሬ አልችልም፣ ነገ ልሞክር. . .” ነገር ግን ኢየሱስ ሁሌም በዚያ ይገኛል።

ብዙን ጊዜ ለኢየሱስ ሰበባችንን እናቀርባለን

“ኢየሱስ እኛ ለመገናኘት፣ ከእኛ ጋር ለማውራት፣ ከእኛ ጋር ለመወያየት እኛን በምጠራን ወቅት ሰበብ አስባብ በመፍጠር እንቢ ያልነው ስንት ጊዜ ነው?” በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛም ብዙን ጊዜ የኢየሱስን ጥሪ ሳንቀበል ቀርተናል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

እስቲ እያንዳንዳችን እናስብ! በሕይወታችን ዘመን የፍቅር ሥራዎችን እንድንሠራ፣ የፍቅር ሥራዎች ውጤት የሆነውን ኢየሱስን እንድንገናኝ፣ ጸሎት እንድናደርግ፣ ሕይወታችንን እንድንቀይር መንፈስ ቅዱስ ላቀረብልን ጥሪ ስንት ጊዜ ነው ምላሽ የሰጠነው? ሁል ጊዜም ቢሆን ይህንን ጥሪ ላለመቀበል ምክንያት እንፈጥራለን። ይህ ደግሞ ጥሩ የሆነ ነገር አይደለም።

ኢየሱስ በጣም መልካም ነው ፣ ነገር ግን ፍታዊ ነው

“ኢየሱስ በጣም መልካም ነው፣ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ ፍታዊ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም በመጨረሻ ቀን ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ ሰው የኢየሱስን ጥሪ ችላ ያላለ ወይም ደግሞ በኢየሱስ ችላ ያልተባለ ሰው መሆኑን ገልጸው ኢየሱስ በጣም ጥሩ እንደሆነ እና በመጨረሻው ሰዓት ሁሉንም ሰዎች ይቅር እንደ ሚል በማሰብ ትርጓሜ ለሚሰጡ ሰዎች ሁሉ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

‘አዎን እርሱ መሐሪ እና መልካም ነው’ በምሕረት የተሞላ ነው፣ ነገር ግን ፍታሃዊ ነው። አንተ የልብህን በር ከውስጥ ክርችም አድረግህ የምትዘጋ ከሆነ እርሱ በፍጹም ሊከፍተው አይችልም፣ ምክንያቱ ለእኛ ልብ ከፍተኛ የሆነ ክብር ስላለው ነው። ኢየሱስን እንቢ ማለት ልባችንን ከውስጥ በኩል ክርችም አድርጎ መቆለፍ ማለት ነው፣ እርሱም ወደ ውስጥ ሊገባ አይችልም። ከእኛ መካከል ማነኛችንም ብንሆን ኢየሱስን እንቢ ማለት “እኛ በኢየሱስ ላይ ልባችንን ከውስጥ በኩል ክርችም አድርገን ቆልፈናል” ማለት እንደ ሆነ አድርገን በፍጹም አስበን አናውቅም።

ኢየሱስ በሞቱ ለድግሱ ከፍሎልናል

ታዲያ ለግብዣው መክፈል የሚገባው ማነው? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለግብዣው የሚከፍለው ኢየሱስ ነው፣ ዛሬ በተነበበልን የመጀመርያው ምንባብ ላይ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ፊሊጲሲዮስ ሰዎች 2፡5-11 ላይ በጻፈው መልእክቱ ላይ “ነገር ግን እርሱ የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፣ በምስሉም እንደ ሰው ሆኖ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ያውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፍሊጲ 2፡5-11) በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ምስጢር በሚገብ በመረዳት የልብ ድንዳኔ፣ የጋለ ስሜት፣ እንቢ ማለት እና በጸሎት የሚገኝ ጸጋ ምን ማለት እንደ ሆኑ መረዳት እንችል ዘንድ ኢየሱስ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንማጸነው ይገባል ካሉ በኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
06 November 2018, 14:34
ሁሉንም ያንብቡ >