ፈልግ

 2018.10.18 Messa Santa Marta 2018.10.18 Messa Santa Marta  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ከሃብት የተላቀቀ፣ ስቃይንና ብቸኝነትን የሚታገስ ልብ ያስፈልጋል”።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከአለማዊ ሃብት የተላቀቀ፣ ለስቃይና ለብቸኝነት የሚታገስ ልብ እንዲኖር ያስፈልጋል ብለዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ዛሬ ጠዋት ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው በቅድስት ማርታ ጸሎት ቤታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ፣ መስዋዕተ ቅዳሴውን ለተካፈሉት ካህናት ደናግልና ምዕመናን ባሰሙት ስብከታቸው፣ ከአለማዊ ሃብት የተላቀቀ፣ ለስቃይና ለብቸኝነት የሚታገስ ልብ እንዲኖር ያስፈልጋል ብለው ክርስቲያናዊ ድህነትንና ለወንጌል ምስክርነት ሲሉ የስቃይና የመከራ ሕይወት የሚኖሩ መኖራቸውን አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ጠዋት በቅድስት ማርታ ጸሎት ቤት ባቀረቡት አስተንትኖ እንደገለጹት፣ አንድ ደቀ መዝሙር ሦስት ዓይነት ሕይወት ለመኖር ተጠርቷል ብለው ከእነዚህም የመጀመሪያው ልቡን ከዓለማዊ ሃብት ሙሉ በሙሉ ነጻ ማድረግ፣ ሁለተኛ ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ በወንጌል ምስክርነት ምክንያት በሕይወት ላይ ሊደርስ የሚችለውን መከራና ስቃይ በትዕግስት መቀበል፣ ሦስተኛ በሕይወት መካከል ሊያጋጥም የሚችለውን የብቸኝነት ስሜትን በትዕግስት መቀበል እንደሆነ አስረድተዋል። ከሉቃስ ወንጌል በምዕ. 10. 1-9 የተነበበውን የዛሬውን የወንጌል ክፍል መሠረት በማድረግ ባሰሙት ስብከታቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን እንዲያስተምሩ ለላካቸው ሰባ ሁለት ደቀ መቀሙርት፣ ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፣ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን፣ ከረጢትም ቢሆን፣ ጫማም ቢሆን አትያዙ በማለት የተናገረውን አስታውሰው፣ ይህን የተባሉበት ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዝሙር ሕይወት የድሕነት ሕይወት እንዲሆን ስለፈለገ ነው ብለዋል።

የደቀ መዝሙር ልብ ከሃብት የተላቀቀ መሆን አለበት፣

የዕለቱን ስብከተ ወንጌል በድሕነት ሕይወት ላይ በማትኮር ያስተነተኑት ቅዱስነታቸው፣ ሐዋሪያዊ አገልግሎቶችን በማበርከት ላይ የሚገኙት ተቋማት ሃብታም ሆነው ከተገኙ ይህን ሃብት ለደሆች ጥቅም እንዲውል በተገቢ መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበውል።

18 October 2018, 17:32
ሁሉንም ያንብቡ >