ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ተስፋ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ህያው የሆነ መሳሪያ ነው!!”
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ተስፋ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ህያው የሆነ መሳሪያ ነው!!”
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ምዕመናን፣ ደናግላን እና ቀሳውስት በተገኙበት በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 13/2011 ዓ.ም ጥዋት ላይ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 12፡35-38 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መስረቱን ባደረገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ግለጹት “ተስፋ ተጨባጭ የሆነ ነገር ነው፣ ተስፋ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ተጨባጭ የሆነ መሳሪያ ነው” ማለታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “በዕየለቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በምናደርጋቸው ግንኙነቶች መደሰት ይኖርብናል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ
አንድ ነፍሰ ጡር የሆነች ሴት ልትወልድ በተቃረበች ወቅት አዲስ ከሚወለደው ልጇ ጋር በደስታ ለመገናኘት በማሰብ በእየቀኑ ሆዱዋን በመነካካት አዲስ የሚወለደውን ልጅ በደስታ እንደ ምትጠባበቅ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩም እኛም በተስፋ እየሱስን ለመገናኘት የምናደርገው ጥረት በደስታ የተሞላ ሕይወት እንድንኖር ይረዳናል፣ ቁምነገር ሊሆን የሚገባው ነገር በእየቀኑ ከኢየሱስ ጋር በተለያየ መልክ የምናደርጋቸው ትናንሽ በሚባሉ ግንኙነቶች ለመደሰት መሞከር በራሱ ታላቅ ጥበብ ነው ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
በዕለቱ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በጻፈው መልእክቱ በምዕራፍ 2፡12-22 ላይ በተጠቀሰው “የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ” በሚለው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተንተርሰው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር ለእያንዳንዳችን የዜግነት መብት በነጻ እንደ ሰጠን ጠቅሰው ይህ እግዚኣብሔር በውርስ መልክ የሰጠን መብት ነው ብለዋል።
“እግዚኣብሔር በልጁ በኢየሱስ አማካይነት ሕግጋትን በመሻር የጠላትነት መንፈስን አስወግዶ እርቅ እንዲፈጠር ማድረጉን” በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም ሁኔታ እኛ አንዳችን ለአንዳችን በእግዚኣብሔር መንፈስ አማካይነት አንድ መሆናችንን በማሳየት፣ አንድነታችንንም በመግለጽ፣ በኢየሱስ አማካይነት የቅዱሳን ኅብረት ተካፋዮች መሆናችንን መግለጽ ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው “የእኛ መለያ ባሕርይ መሆን የሚገባው በጌታ በኢየሱ ክርስቶስ መዳናችንን የሚገልጽ ስብዕናን መላበስ እንደ ሆነ ገልጸው መንፈስ ቅዱስ በመካከሉ የሚገኝ አንድ ማኅበርሰብ መገንባት ይኖርብናል ብለዋል።
ስለዚህ እግዚኣብሔር የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንድንችል ወደ ፊት እንድንራመድ እንደ ሚረዳን በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህ በመተማመን እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር እንደ ሆነ በማመን ጭምር በዚህ ተስፋ መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል። በቀጣይነት ወደ ፊት በምናደርገው ጉዞ ውስጥ ውርሳችንን መፈለግ እንደ ሚገባ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ውርሳችንን የምናገኘው ደግሞ በመጨረሻው ጊዜያችን እንደ ሆነ ጨምረው ገለጸዋል። ውርሳችንን በእየለቱ መፈለግ እና ማንነታችንን ጠብቀን በእርጠግጠኛነት ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚረዳን ተስፋ እንደ ሆነ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህንንም የምናደርገው በጣም ትንሽ የሆነ በጎነት ወይም አስቸጋሪ የሆኑ ተግባራትን በእየለቱ በመወጣት ሊሆን እንደ ሚችል ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።
ተስፋ ካልህ በፍጹም አትቆጭም
እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር የእግዚኣቤር ስጦታዎች ናቸው። ፍቅር እና እመነትን መረዳት የሚከብድ ነገር አይደለም። ነገር ግን “ተስፋ ምን ማለት ነው?” በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ተስፋ ማድረግ ማለት በሰማያዊ ነገር ተስፋ ማድረግ፣ ከቅዱስን ጋር እንደ ምንገናኝ ተስፋ ማድረግ፣ ዘላለማዊ የሆነ ደስታ እንደ ምናገኝ መተማመን ማለት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው “ ነገር ግን ለእናንተ መንግስተ ሰማይ ማለት ምን ማለት ነው?” የሚለውን ጥያቄ አንስተው ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .
አዎን! በተስፋ መኖር ማለት አንድን ሽልማት ለማግኘት ወደ ፊት መራመድ ማለት ነው፣ እኛ አሁን የሌለን ዓይነት ደስታ ነገር ግን ለወደፊቱ ከፍተኛ የሆነ ደስታ የምናገኝበት ሥፍራ ነው፣ ለመረዳት የሚያዳግት ምግባር ነው። ይህ ምግባር በፍጹም የሚያስፍረን አይደለም፣ አንተ/አንቺ ተስፋ የምታደርግ ከሆነ በፍጹም አታፍርም። በፍጹም! በፍጹም! ተጨባጭ የሆነ ምግባር ነው። “ነገር ግን መንግሥተ ሰማይን ወይም የሚጠብቀኝን ነገር የማላውቅ ከሆነ እንዴት ነው እሱ ይህ ነገር ተጨባጭ የሆነ ነገር ሊሆን የሚችለው?”። ተስፋ፣ ለእኛ በውርስነት የሚሰጠንን ነገር እንድናገኝ የሚረዳን ነገር ነው እንጂ ተስፋ አንድ በሐሳብ ውስጥ ያለ ውብ የሆነ አንድ ሥፍራ አይደለም። ይህንን ተስፋ በተመለከተ ኢየሱስ ብዙን ጊዜ አስምሮ ሲናገር እርሱን ለመገናኘት መጠባበቅ የሚለውን ትርጉም በአጽኖት ሲሰጥ እናያለን።
አዲስ ከሚወልድ ልጇ ጋር ለመገናኘት በጉጉት በመጠባበቅ የምትኖረው ነፍሰ ጡር ሴት
ዛሬ በስርዓተ አምልኮ ወቅት በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ሉቃ. 12፡35-38) ውስጥ “እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ” በማለት ኢየሱስ መናገሩን በመገለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ማለት ከጌታ ጋር መገናኘታችን ተጨባጭ የሆነ እውነታ እንደ ሆነ እንደ ሚያሳይ ገልጸው ይህንን ሐሳባቸውን በተሻለ መልኩ ለማስረዳት በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .
እኔ ሁል ጊዜ ስለ ተስፋ ሳስብ አንድ ነገር ወደ አእምሮዬ ይመጣል፣ ይህም አንድ ነፍሰ ጥሩ የሆነች ልጇን ለመገላገል በመጠባበቅ ላይ የምትገኝ ሴት ምስል ወደ አእምሮዬ ይመጣል። ወደ አንድ ሐኪም በመሄድ በአልትራሳውንድ እንዲመለከተው በማድረግ ልጇ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን ታረጋግጣለች አይደል! በዚህም ትደሰታለች! ለልጇ ያላትን ፍቅር ለመግለጽ በእየቀኑ ሆዱዋን ትዳብሳለች፣ በዚህም ሁኔታ ሕጻኑን ትጠባበቃለች፣ ይህንን ሕጻን በመጠባበቅ ትኖራለች። ይህ ምስል ተስፋ ምን ማለት እንደ ሆነ እንድንረዳ ያደርገናል፡ አንድን ነገር ለመገናኘት መጠባበቅ ማለት ነው። ያቺ ነፍሰ ጡር የሆነች ልጇ ምን ዓይነት ዓይን እንደ ሚኖረው፣ ፈገግታው ምን እንደ ሚመስል፣ ጠይም ወይም ጥቁር ይምሰል አይምሰል
ከኢየሱስ ጋር የምናደርጋቸው ትናንሽ የሆኑ ግንኙነቶች እንዴት አስደሳች እንደ ሆኑ ማወቅ ይኖርብናል
ቀደም ሲል ስለ አንዲት ነፍሰ ጡር ስለሆነች ሴት የተጠቀሰው ምሳሌ ተስፋ ምን ማለት እንደ ሆነ በደንብ እንድንረዳ ያግዘናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ተስፋ ተጨባጭ የሆነ ነገር ነው ምክንያቱም ሁል ቀን አንድ ነገር ለማግኘት መጠባበቅ ማለት በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ጠቅሰው በእየቀኑ በቅዱስ ቁርባን፣ በጸሎት፣ በቅዱስ ወንጌል፣ በድኾች፣ በማኅበራዊ ሕይወት በእየለቱ አንድ እርማጃ ይህንን እውነታ ለማግኘት በምንራምድባቸው ወቅቶች ሁሉ በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉ ነገሮች አማካይነት ኢየሱስን መገናኘት እንደ ምንችል የገለጹት ቅዱስነታቸው በሕይወታችን በጥቃቅን ነገሮች አማካይነት ኢየሱስን መገናኘት የሚሰጠውን ደስታ በጥበብ በመመልከት ከኢየሱስ ጋር መገናኘታቸን እርገጠኛ እንደ ሆነ ማወቅ ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።