ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  29/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 29/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ ሰላም የትህትና፣ የገርነት እና የደግነት መንገድ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 16/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት “ማድረግ” እና “ማጠናከር” የሚሉትን ሁለት ግሶች በመጠቀም ሰላምን በተመለከተ ባደርጉት ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ዓለማቀፍ ተቋማት ሰላምን በተመለከተ መግባባት ላይ አለምድረሳቸውን የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ሰላም የትህትና፣ የገርነት እና የደግነት መንገድ ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራት ኃ/ጊዮርጊስ

“በዓለም ውስጥ ሰላምን በእውነትኛ መንገድ ለማስፈን ከተፈለገ የሰው ልጆች ሁሉ በትህትና፣ በገርነት እና በበጎነት መንገድ” ማለፍ ይኖርባቸዋል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም መተግበር የሚገባን በማኅበርሰባችን እና እንዲሁም በቤተሰባችን ውስጥ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በላቲን የስረዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በቀዳሚነት ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች በጻፈው (4፡1-6) ተወስዶ በተነበበው መልእክት ላይ መሰረቱን ባደረገው ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ በእስር በብቸኝነት በቆየባቸው ጊዜያት ሁሉ ክርስቲያኖች እውነተኛ እና "አንድ የሚያደርጋቸውን የውዳሴ መዝሙር"  "ለጥሪያቸው ክብር በመስጠት” ሊዘምሩ እንደ ሚገባ አሳስቦ እንደ ነበረ ቅድስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ሰላምን በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም

ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ በሮም ከተማ በሚገኘው ትሬ ፎንታኔ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ ሕይወቱን እስካጣበት ዕለት ድረስ ክርስትያኖች ስለነበራቸው ውስጣዊ እክል ይጨነቅ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩም ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት የመጨረሻ ራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በሚቋደስበት ወቅት እግዚኣብሔር ሁላችንም አንድ የምንሆንበት ጸጋ እንዲሰጠን ጠይቆት እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በአሁኑ ወቅት እኛ ሁላችን ያለ መታደል ሆኖ  “የግጭት አየር መተንፈስ ተለማምደናል”፣ በዕየለቱ በቴለቪዢን እና በጋዜጦች ላይ ሳይቀር አናት በአናቱ የጦርነት እና የግጭት ዜናዎችን በዕየለቱ በማዳመጥ ላይ እንገኛለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ጊዜ የምተገኘው ዓለማችን “ያለ ሰላም እና ያለ አንድነት” እየኖረች ተገኛለች ማለታቸው ተገልጹዋል። በዓለም ደረጃ “ ማንኛውም ዓይነት ግጭቶችን  ለማስቆም "ስምምነቶች ይደረጋሉ" ነገር ግን እነዚህ ስምምነቶች ችላ ይባላሉ’ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በዚህ የተነሳ የጦር መሳሪያዎች ለመታጠቅ የሚደረግ ሩጫ፣ ለጦርነት እና ለጥፋት የሚደረጉ ሩጫዎች ተፋፍመው ለመቀጠል ችለዋል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

በሰው ልጆች መካከል በተሻለ መልኩ ሰብዐዊ የሆነ ኅበረት፣ ሰላም እና አንድነት ለመፍጠር እንዲቻል በማሰብ የተቋቋሙት ዓለማቀፍ ተቋማት እንኳን ሳይቀሩ ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ የሚያስችል አንድ ስምምነት የማስገኘት አቋም ላይ አልደረሱም፣ ይህንን የሚከለክል አንድ ነገር አለ፣ ይህ እውን እንዳይሆን የሚያደርግ ፍላጎት አለ . . .በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ አንድ የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ይቸገራሉ። ከጥቂት ጊዜዎች በኋላ ሕጻናት የሚባላ ነገር አይኖራቸውም፣ ወደ ትምሕርት ቤት አይሄዱም፣ ተገቢውን ትምሕርት አያገኙም፣ በጦርነት ምክንያት በጣም ብዙ የሆኑ ተቋማት በመፈራረሳቸው የተነሳ የሕክምና ተቋምት ሊኖሩ አይችሉም። የማውደም፣ የጦርነት እና የመከፋፈል ዝንባሌዎች አሉን። ከልባችን ውስጥ ሰብአዊነትን የሚያጠፋ፣ የጠላትነት ዘር የሚዘራ  አንድ ጠላት አለ ይህም ሰይጣን ነው። ጳውሎስ በዚህ ምንባብ ውስጥ ወደ አንድነት የሚያመራን መንገድ ያስተምረናል። አንድነት በመጋረጃ ተሸፍኑዋል ለማለት እንችላለን። ሰላም ወደ አንድነት ይመራል።

ልባችንን መክፈት

“ስለዚህ የተቀበለውን ጥሪ ተገቢ በሆነ ሁኔታ በትህትና፣ በደግነት እና በበጎነት በመኖር ትክክለኛውን ጥሪያችንን ማስቀጠል ይኖርብናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ሰላም ለመፍጠር በቅድሚያ በመካከላችን አንድነት መፍጠር ይገባናል፣ እኛ እርስ በእርሳችን መሰዳደብ እና መጯጯህ የለመድን፣ ይህንን ትተን ጣፋጭ በሆነ መልኩ እና በጋለ ስሜት አንድነትን በመካከላችን መፍጠር ይኖርብናል። ሁሉንም ነገር ተው፣ ልብህን ክፈት። ነገር ግን በእነዚ ሦስት ትናንሽ ነገሮች አማካይነት በዓለማችን ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ይቻላል ወይ? አዎን በሚገባ! ይህ ሂደት ነው። አንድነትን መፍጠር ይቻላል ወይ? አዎን በሂደት “በትህትና፣ በገርነት እና በደግነት መንገድ” በመጓዝ መድረስ ይቻላል። ሐዋርያው ጳውሎስ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮችን ያስቀምጥልናል፣ “እርስ በእርሳችሁ በፍቅር ተደጋገፉ” ይለናል። አንዳችን ለአንዳችን ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል። ይህ ነገር በጣም ቀላል የሚባል ነገር አይደለም፣ ሁሉ ጊዜ በሰዎች ላይ መፍረድ፣ ማውገዝ ይቀለናል፣ ይህም ተግባር ከሰዎች ጋር እንድንለያይ ከፍተት ይሰጣል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ከጅምሩ መረዳት

በአንድ ቤተሰብ መካከል ክፍተ ሊፈጠር እንደ ሚችል በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ክፍተ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በሚክሰትበት ወቅት “ሰይጣን በጣም ይደሰታል” ይህም የጦርነት መጀመርያ ይሆናል ብለዋል። ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ሊሆን የሚችለው እኛ አንዳችን ለአንዳችን “መቀባበል” ይኖርብናል ምክንያቱም እኛ ሁላችን አንዱ ለአንዱ ምቾት እንነሳለን፣ ትዕግስት እናጣለን በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ደግሞ እኛ ሁላችን ኃጢያተኞች በመሆናችን የተነሳ እንደ ሆነ ገለጸው በዚህም የተነሳ እኛ ሁላችን ደክመት ስላለብን ነው ብለዋል። ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ “የሰላም ማሰሪያ መሆን የመንፈስን አንድነት ጠብቆ ለማቆየት " እንደ ሚያስችል ምክሩን እንደ ለገሰ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእርግጠኛነት ኢየሱስ የመጨረሻ ራቱን ይመገብ በነበረበት ወቅት “ሁሉም አንድ አካል እና አንድ መንፈስ ይሆኑ ዘንድ” የተማጸነው አንድነት የሰላም ምንጭ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

“ከእግዚኣብሔር ጋር በመሆን ወደ ፊት መጓዝ የሰላምን አድማስ እንድንመለክት እንደ ሚረዳ” በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ በጸሎቱ ‘አባት ሆይ እኛ አንድ እንደ ሆንን እነርሱም አንድ ይሆኑ ዘንድ’ በማለት የሰላምን አድማስ በጸሎት እንዳሳየን ሁሉ ኅበረት የሰላም ምንጭ ነው ብለዋል። በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 12፡54-59 ላይ ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ ተንተርሰው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኢየስሱ በቃሉ በመንገድ ላይ ከባለ አንጥህ ጋር በምትጓዝበት ወቅት ሰላምን ፍጠር በማለት ምክር ለግሶ እንደ ነበረ አስታውሰው ይህም በጣም መልካም የሚባል ምክር እንደ ሆነ ገለጸው “ጠቦች ተጠናክረው ከመቀጠላቸው በፊት ሰላም መፍጠር በጣም ጠቃሚ የሆነ አንገር በመሆኑ የተነሳ ነው” ማለታቸንው ለመረዳት ተችሉዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

ከመጀመርያው አንስቶ ስምምነት እንድንፈጥር እና ሰላም እንድናወርድ ኢየሱስ ይመክረናል፡ ይህ ደግሞ ትህትናን ያመለክታል፣ ይህ ጣፋጭ መሆናችንን ያሳያል፣ ይህ በጉነት ነው። በዓለማችን ውስጥ በእነዚህ ሦስት ትናንሽ በሚመስሉ ተጋባራት አማካይነት ሰላምን ማስፈን ይቻላል፣ ምክንያቱ እነዚህ ትህትና፣ የዋህነት እና ሁሉንም ይቅር ማለት የኢየሱስ ባሕርያት በመሆንቸው የተነሳ ነው። ዓለማችን በአሁኑ ወቅት ሰላም ያስፈልጋታል፣ እኛ በአሁኑ ወቅት ሰላም ያስፈልገናል፣ ቤተሰባችን በሁኑ ወቅት ሰላም ያስፈልገዋል፣ ማኅበርሰባችን በአሁኑ ወቅት ሰላም ያስፈልገዋል። እነዚህን በጎነት፣መልካምነት እና አንድነት የተሰኙ ሦስት ነገሮች በቅድምያ ከቤታችን በመጀመር መትግበር ይኖርብናል። በዚህም መንገድ ወደ ፊት እንጓዝ፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ኅብረት እና አንድነትን በመመስረት እንጓዝ። በዚህ መንገድ በአግባቡ መጓዝ እንችል ዘንድ ጌታ ይርዳን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
26 October 2018, 16:03
ሁሉንም ያንብቡ >