ፈልግ

2018.09.21 Messa Santa Marta 2018.09.21 Messa Santa Marta  (Vatican Media)

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ “ከየት ቦታ እንደተመረጥን እናስታዉስ”።

ኣብዛኛውን ጊዜ ራሳችንን ከመመልከት ፋንታ ሌሎችን እናያለን ስለ ኃጢአታቸውም እናወራለን ይህ የሚያም ነገር ነው። ራሳችንን መክሰስ እና ክርስቶስ ከየት ቦታ እንደመረጠን ወደየት ቦታም እንዳመጣን ማስታውሱ የተሻለ ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ዛሬ ማለትም መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. እንደተለመደው በቅድስት ማርታ መሥዋተ ቅዳሴ ሲያሳርጉ የዛሬው መሥዋዕተ ቅዳሴ የቀራጩ ማቴዎስን ጥሪ ኣስታውሰዋል። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ማቴዎስን ከቀራጭነት ወደ ሓዋርያነት እንደጠራው ገልጸው 3 ነገሮች ላይ ማለትም የምሕረት ዕቅድ ምርጫና በምርጫ ላይ የሚደረግ ግንባታን ላይ ትንታኔ ማድረጋቸውን የቫቲካን ከተማ የሬዲዮ ኣገልግሎት ባልደረባ አድሪኣና ሞሳቲን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሲናገሩ ቀራጩ ማቴዎስ በእርግጥም በሙስና በመዘፈቅ ሃገሩናን ሕዝቡን ያታልል ነበር ምናልባት ኣንዳንዶች ብዙ የተሻሉ መልካም ሰዎች እያሉ እንዴት ቀራጩን እንዲሁም የተለያዩ በኅብረተሰቡ ዘንድ ቦታና ክብር የማይሰጣቸውን ለደቀመዝሙርነት ይመርጣል ይሉ ይሆናል። ነገር ግን የቤተክርስቲያንን ሕይወት ስንመለከት ኣብዛኞቹ ቅዱሳኖች በሰዎች ከተናቁና ታች ካሉ ቦታዎች የተጠሩ ናቸው። እኛ ክርስቲያኖች ከየት ቦታ እንደተነሳን ከየት ቦታ ከምን ላይ እንደተመረጥን በመጀመሪያ የት ቦታ እንደነበርን ማስታወስ ይገባናል። መጀመሪያ በነበርንበት ቦታ ሆነን ስለ ኃጢያታችን ብጫ ማሰብ ነበረብንን? ኣግዚእብሄር ግን በምሕረቱ ኃጢኣታችንን ደመሰሰልን ክርስቲያን ኣደረገን በመጨረሻም የእርሱ ተከታይ እንድሆንም መረጠን።

ማቴዎስ ከየት ቦታ እንደተነሳ ኣልረሳም

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ማቴዎስ ከተጠራበት ዓላማ ጋር የነበረውን ግንኙነት ሲያስረዱ እሱ እጅግ የከበረ ልብስ ኣለበሰም እኔ ከሓዋርያቶች ሁሉ እበልጣለሁ የሁሉ ጌታ ነኝ የሁሉ ኃላፊ ነኝ ኣላለም እርሱ ሕይወቱን በሙሉ ለወንጌል መስፋፋት ኣውሏል።

ኣንድ ሐዋሪያ የእራሱን መነሻ ሲረሳው እና የራሱን ሥራ ብቻ መስራት ሲጀምር ከጌታ ይርቃል እንደ ሓዋርያ ሳይሆን ኣንደ ማንኛዉም ሰው የኣንድ ጥሩ የሥራ ኃላፊ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስን ሊያስተላልፍ የእርሱን ወንጌል ማስተማር ግን አይችልም ምክንያቱም መነሻውን ረስቷልና ኣንድ ጥሩ ጉዳይ ኣስፈጸሚ እንጂ እንድ ሓዋርያ ለመሆን እይችልም ብለዋል።

ኣብዛኛውን ጊዜ ራሳችንን ከመመልከት ፋንታ ሌሎችን እናያለን ስለ ኃጢአታቸውም እናወራለን ይህ የሚያም ነገር ነው። ራሳችንን መክሰስ እና ክርስቶስ ከየት ቦታ እንደመረጠን ወደየት ቦታም እንዳመጣን ማስታውሱ የተሻለ ነው። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በማከልም እግዚኣብሔር ሲመርጥ የሚመርጠው ለአንድ ትልቅ ዓላማ ነው ብለዋል። ክርስቲያን መሆን ታላቅ እና የሚያምር ነገር ነው እኛ ሁላችንም ራሳችንን ከእርሱ እናርቃለን በግማሽ መንገድም ላይ እንቆማለን ስለዚህ ለጋስነት ይቀረናል ማለት ነው ከፈጣሪ ጋር መነጋገር መቻል ኣለብን እርሱ ደግሞ ሁሌም ይጠብቅናል።

የሕጉ ዶክተሮች እንቅፋትነት

በጥሪው ላይ ማቴዎስ ኢየሱስን ለመከተል ፍቅርን ገንዘብን ክዷል እናም ይላሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጓደኞቹን ጌታን ለማክበር ከእርሱ ጋር ምሳ ጋበዛቸው ስለዚህ በዚያ ቦታ የኃጥአን ስብስብ ነበር ጌታችን ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ይበላ ነበር።

የሕግ ዶክተሮቹ ይህንን ነገር በተመለከቱ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ጠርትው ይህ ጌታ የምትሉት እንዴት ይህንን ነገር ያደርጋል? ከኃጥአን ጋር ይበላል ስለዚህ እርሱ ራሱ ኃጢያተኛ ሆኗል አሉ ኢየሱስም ይህንን ሰምቶ እንዲህ ኣለ "ሂዱና ምን እንደምፈልግ ተማሩ እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መስዋዕትን አይደለም። የእግዚአብሔር ምህረት ሁሉንም ሰው ያካትታል ሁሉንም ይቅር ይላል ከሁላችን የሚጠበቀው ጌታ ሆይ እርዳኝ ማለት ብቻ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የምህረት ምሥጢር የእግዚአብሔር ልብ ነው

ኢየሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ሐኪም የሚያስፈልገው ለበሽተኞች እንጂ ለጤናማ ሰዎች አይደለም ብሎ መልሶላቸዋል ምሕረትን እሻለሁ እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም ብሎ ተናግሯቸዋል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የጌታን ምህረት መረዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረው የእግዚአብሔር ልብ ኣንድ ምስጢር ነው በጣም ትልቅ እና እጅግ ጥልቅ ምስጢር ነው ካሉ በኃላ ወደ እግዚአብሔር ልብ ውስጥ ለመግባት የሚፈልግ የምህረትን መንገድ መያዝና በምህረት መንገድ ውስጥም መመላለስ እንድሚያስፈልግ ኣብራርተው የዕለቱን ቃለ እግዚኣብሔ ደምድመዋል።

21 September 2018, 17:20
ሁሉንም ያንብቡ >