ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  04/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 04/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “መንፈስ ቅድስ የስብከተ ወንጌል ዋነኛው አጋዥ ነው”

በማንኛውም ስብከተ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ “ተዋናይ” ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “መንፈስ ቅድስ የስብከተ ወንጌል ዋነኛው አጋዥ ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ለሚሰበሰቡ ቀሳውስት፣ ደናግልና እና ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ኢያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በሰኔ 04/2010 ዓ.ም በአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር የላቲን የስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ መሰረት የቅዱስ ባርናባስ አመታዊ በዓል በተከበረበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት በማንኛውም ስብከተ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ “ተዋናይ”  መሆኑን ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

ቅድሱ ወንጌልን የማብሰር ሂደት ከሌሎች የመገናኛ ዓይነቶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጉዳይ አለምሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ወንጌልን የማስበር ሂደት በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ የሚከናወን በመሆኑ የተነስ ልብን የመቀየር ኃይል አለው ብለዋል። አንድ አንድ ጊዜ በጥም ምርጥ የሚባሉ ሐዋሪያዊ ተግባራትን የማከናወኛ እቅዶች ቢኖሩም እናኳን እነዚህ ምርጥ የተባሉ ሐዋሪያዊ እቅዶች በራሳቸው ልብን የመለወጥ ኃይል ወይም ብቃት እንደ ሌላቸው በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ እቅዶች በራሳቸው ወድ ግብ እንድናመራ የሚያደጉን ናቸው እንጂ በራሳቸው ወደ ግብ መስመር መውሰጃ መሳሪያዎች ግን አይደሉም ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን አስባቸውን ለማተናከር በማሰብ የሚከተለውን ብለዋል . . .

ኢየሱስ እኛን ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ብቻችንን አይደለም የሚልከን፣ በፍጹም እንዲ አይደለም! ነገር ግን የሚልከን ከመነፈስ ቅዱስ ጋር ነው እንጂ። ይህም የብርታታችን ምንጭ ነው። ከብርቱ ወንጌላዊ በስተጀርባ ያለው የሰው ልጅ ድፍረት አይደለም። በፍጹም እንዲ አይደለም ብርታን የሚሰጥን እና ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አገልግሎት ሁለተኛ ቅዱስ ወንጌል የማብሰር ሂደት ገጽታ አድርገው የሚመለከቱ ሲሆን እንዲያውም ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ "በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎትን ወይም ስኬትን መፈለግ ማለት አንድ ሰው ወንጌልን ምንም እንደማያውቅ የሚያሳይ ምልክት ነው የሚያዝ ሰው በራሱ የሚያገለግል ሰው ሊሆን የገባዋል የሚል ከፍተኛ አቋም እንዳልቸው ይታወቃል።

ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“መልካም የሆኑ ነገሮችን መናገር እንችል ይሆናል፣ አገልግሎት ካልታከለበት ግን ስብከተ ወንጌል ነው ልንል በፍጹም አንችልም። ስብከተ ወንጌልን ሊመስል ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን አይደለም፣ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የጌታን እውነታዎች እና የጌታን ሕይወት ለማወጅ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት የሚመራን፣ ነገር ግን በተጨማሪም ትናንሽ በሚባሉ አገልግሎቶች ሳይቀር ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን እንድናገለግል ያደርገናል። ለማገልገል የተላኩ ወንጌላዊያን የሚባሉ ሰዎች በሌሎች ሰዎች ሲገለገሉ ማየት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። የስብከተ ወንጌል ንጉሥ ይሆናሉ. . . ይህም በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው።”

ወንጌል በነፃ የሚሰጥ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በነጻ የሚሰጥ አገልግሎት መሆኑ ደግሞ የወንጌላዊነት ሦስተኛው የመገለጫ ገጽታ እንደ ሆነ የጠቀሱ ሲሆን ምክንያቱም ማንም ቢሆን በራሱ ብርታ ታግዞ የዳነ ሰው ባለመኖሩ የተነሳ ነው በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ ገለጸው  ቅዱስ ወንጌል “ በነጻ የተቀበላችሁትንም በነጻ ስጡ” በማለት እንደ ሚናገር ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ይህንን በተመለክተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል

ሁላችንም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በነጻ ነው የዳነው። ስለዚህ እኛም በነጻ መስጠት ይገባናል። ሐዋሪያዊ ተግባሮችን የሚያከናውኑ ወንጌላዊያን ይህንን የግድ ሊማሩ ይገባል። ሕይወታቸውን በነጻ፣ በአገልግሎት፣ በማብሰር እና በመነፍስ ቅዱስ ዳግም በመወለድ ሊያከናውኑ ይገባል። ግላዊ የሆነ ድኽነታቸው ራሳቸውን ለመንፈስ ቅዱስ እንዲከፍቱ ያስገድዳቸዋል ብለዋል።

11 June 2018, 11:24
ሁሉንም ያንብቡ >