ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  05/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 05/10/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© Servizio Fotografico L'Osservatore Romano)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ክርስቲያንዊ ምስክርነት መስጠት የምድር ጨው እና ብርሃን መሆን ማለት ነው”

ክርስቲያኖች ክርስቶስን በመመስከር ሂደት ውስጥ ለራቸው ጥቅም እና ዝና ብለው ሳይሆን ነገር ግን እንደ ጨው እና እንደ ብርሃን በመሆን ማከናወን ይገባቸዋል

ር.ቃ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ “ክርስቲያንዊ ምስክርነት መስጠት ማለት የምድር ጨው እና ብርሃን መሆን ማለት ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን ቀደም ሲል ያሰማናችሁን ቃል የተናግሩት በሰኔ 05/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ክርስቲያኖች ክርስቶስን በመመስከር ሂደት ውስጥ ለራቸው ጥቅም እና ዝና ብለው ሳይሆን ነገር ግን እንደ ጨው እና እንደ ብርሃን በመሆን ማከናወን ይገባቸዋል ካሉ በኃላ ክርስቲያንዊ ምስክርነት መስጠት ማለት ሌሎች ሰዎችን ማነጽ ማለት ነው እንጂ ራሳችንን የምናስተዋውቅበት መደርክ ግን ሊሆን አይገባውም ብለዋል።

ክርስቲያኖች የተጠሩት “ቀለል ባለ መልኩ እና ሊለመድ በሚችል መልኩ” እለት በእለት ቅድስናን የሚገልጹ ባሕሪያትን ለማንጸባረቅ እንደ ሆነ በመግለጽ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ክርስቲያናዊ የሆነ ምስክርነት መስጠት ማለት ኢየሱስ ያሳየን አብነት በመከተል ነብሳችንን በመስዋዕትነት መስጠት ማለት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቶስን የሚያመላክቱ ተግባራትን በእለት ተእለት ተግባራችን ከእንቅልፋችን ስንነቃ፣ ሥራ ሥንሰራ ወደ አልጋችን ስንሄድ ሳይቀር በምናከናውናቸው ጥቃቅን ተግባራት ኢየሱስን መመስከር እንደ ሚችላ የገለጹት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን እነዚህ ተግባራት “ትናንሽ የሆኑ ተግባራት የሚመስሉ ቢሆንም ቅሉ” ነገር ግን ተዐምራት የሚከናወኑት በእየለቱ በምናከናውናቸው ጥቃቅን ነገሮች ጋር በተያያዘ መልኩ ነው ብለዋል።

የአንድ ክርስቲያን ምስክርነት መሰርቱን በትህትና ላይ ሊያደርግ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ማለት ልክ እንደ ጨው እና እንደ ብርሃን በቀላሉ መገኘት ማለት ነው ካሉ በኃላ ይህን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

““ለሌሎች ጨው፣ ለሌሎች ብርሃን መሆን፡ ምክንያቱም ጨው ለራሱ ጣዕም አይሰጥም፣ ነገር ግን የሚያገለግለው ሌሎች ሰዎችን ነው። ብርሃን ለራሱ አያበራም፣ ነገር ግን ለሌሎች ብርሃን ይሰጣል። የገበያ ማዕከላት ጨውን የሚሸጡት በብዛት በቶን በሚቆጠር መልኩ አይደለም። ጨው ራሱን አያስተዋውቅም ምክንያቱ ራሱን አያገለግልምና። ሌሎችን ለማገልገል መኖር፣ ለሌሎች ጣዕም ለመስጠት ይኖራል። ይህም በጣም ቀላል የሆነ ምስሌ ነው።”

ክርስቲያንዊ ምስክርነትን መስጠት ማለት ለሌሎች ብርሃን መሆን ማለት ነው፣ ሰዎች በጨለማ ውስጥ በሚሆኑባቸው ጊዜያት ሁሉ የእነርሱ ብርሃን መሆን ማለት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

“ጌታ እናንተ ጨው ናችሁ እናንተ ብርሃን ናችሁ ይለናል። ይሁን እንጂ ሌሎች ሰዎች አምላክን እንዲያዩና እንዲያከብሩ ይህን አድርጉ ። ምንም ዓይነት ስጦታ ላታገኝ ትችል ይሆናል። ምግብ በምንመገብበት ወቅት በውስጡ ያለውን ጨው አናመሰግንም። ነገር ግን በአንጻሩ ይህ ፓስታ ወይም ይህ ስጋ እንደት ጥሩ ነው፣ ነው የምንለው። በምሽት ወደ አልጋችን በምንሄድበት ወቅት ያ ብርሃን በጣም ጥሩ የሆነ ብርሃን ነው አንልም። ብዙን ጊዜ እኛ ብርሃንን ችላ እንላለን ነገር ግን እኛ የምንደምቀው በብርሃን ነው። ይህም ክርስቲያኖችን ማንነታቸው ያልታወቀ ምስክሮች እንዲሆኑ ያነሳሳቸዋል”።”

12 June 2018, 11:31
ሁሉንም ያንብቡ >