ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 11/2010 ዓ.ም  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 11/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© VATICANMEDIA S.S. Francesco - Messa Domus Sanctae Marthae 11-01-2018)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ አንባገነንነት የሚጀምረው የሰው ስም በማጥፋት ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳው “አንባገነንነት የሚጀምረው የሰው ስምን በማጥፋት ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “አንባገነንነት የሚጀምረው የሰው ስም በማጥፋት ነው”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳው “አንባገነንነት የሚጀምረው የሰው ስምን በማጥፋት ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ማለትም በሰኔ 11/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባስሙት ስብከት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን መጥፎ የሆኑ ወሬዎች እና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም አፍራሽ የሆነ የስም የማጥፋት ዘመቻ ማድረግ ተግቢ እንዳልሆነ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ባለፉት ምዕተ አመታት በአይሁዳዊያን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ የሆነ ስደተ ማስታወስ እንደ ሚገባ ገልጸው ዛሬው ሚሆን በተለያዩ መንገዶች ተመሳሳይ የሆኑ ስህተቶች እየተፈጸሙ እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው ጨመው ገለጸዋል።

የአንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ስም ለማጥፋት ሲፈልጉ በቅድሚያ የእዛን ግለሰብ ወይም ተቋም ስም ማበለሸት ይጀምራሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህን የስማ ማጥፋት ቅሌቶች የሚፈጽሙት አባባይ በሆነ መልኩ በሚቀርቡ የመጋናኛ ዘዴዎች አማካይነት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በዕለቱ ያደርጉት ስብከት መሰረቱን ያደርገው በእለቱ ከ1ኛ መጻፈ ነግሥት ከምዕራፍ 21፡1-16 ላይ ተወስዶ በተነበበው በናቦት ታሪክ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም በኢየሱስ ላይ፣ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ፣ በሁሉም ቅዱሳን እና ሰማዕታት ላይ ሳይቀር በሐሰት የጥፋት ወሬዎች ምክንያት የተፈጸሙ እንግልቶች እና ስቃዮችን ያስታውሰናል ብለዋል። ይህ አፍራሽ የሆነ ስም የማጥፊያ የሐሰት ወሬ በተመሳሳይ መልኩም በተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና አስተዳደሮች ላይ በመፈጸም ላይ የሚገኝ ተግባር እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በአንድ ውሸት በሆነ ወሬ ይጀመርና ቀስ በቀስ ደግሞ በእዚህ የሐሰት ወሬ የተነሳ ውሳኔን በማስተላላፈ ተፈጻሚ እንዲሆን በማድረግ የአንድን ግለሰብ ወይም አንድን ተቋም ወደ ማፈራረስ ደረጃ ይደርሳሉ ብለዋል። ዛሬውም ቢሆን በተለያዩ ሀገራት የመናገር መብትን በጋሻነት በመጠቀም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አፍራሽ የሆኑ የሐሰት ዜናዎችን በማሰራጨት ላይ የሚገኙ በርካታ ገልሰቦች እና ተቋማት እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ዕለታዊ በሆነ ኑሮዋችን ውስጥ ሳይቀር ይህ ተመሳሳይ ችግር እንዳለ በመጥቀስ ስበከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው የአንድ ግለሰብን ስም ለማጣፍት ከተፈለገ የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ሰለ ግለሰቡ መጥፎ ነገር በመናገር፣ ሀሰት የሆኑ ነገሮችን አግዝፎ በማዉጣት አሳፋሪ የሆኑ ተግባራት እየተፈጸሙ እንደ ሚገኙ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል

“መጥፎ የሆኑ ወሬዎች በሙሉ በጣም ማራኪ የሆኑ ወሬዎች በመሆን የሰዎችን ቀልብ ሲስቡ እናያለን። መጥፎ ወሬዎች የሰው ቀልብ ይስባሉ። ጥሩ የሚባሉ ወሬዎች ግን የሰውን ቀልብ ብዙም አይስቡም፣ ጥሩ ነገር ነው? ታዲያ እኛ ምን ኣናድርግ? ርሱስ ምን እያደርገ ነው? ብሎ በመጠየቅ ብዙም ሳይገረሙ ዝም ይላሉ። መልካም የተባለ ወሬ ወሬ ሆኖም ብዙ አይቀጥልም፣ በእዚያው ያልፋል። ነገር ግን አንድ መጥፎ የሆነ ዜና የሆነ ከሆነ ግን “ይህንን አይተሃል፣ ያንን አይተሃል! ያ ሰው የሰራውን ነገር አይተሃል? በእዚህ ዓይነት ሁኔታ ወደ ፊት መጓዝ አይቻልም . . .አይሆንም አይሆንም በእዚህ ሁኔታ ወደ ፊት መጓዝ አይቻልም። በእዚህ መልኩ ወሬው እየተስፋፋ ይሄዳል፣ በእዚህም መልኩ ይህ ጥሩ ያልሆነ ወሬ የተወራበት ሰውም፣ ተቋም ወይም ሀገር በእዚያው ከስሞ ይቀራል ያወድማል። በመጨረሻም በሰዎች ላይ አይፈርዱባቸውም። በሰዎች ወይም በተቋማት ውድቀት ላይ ነው የሚወስኑት ምክንያቱም እነዚህ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ራሳቸውን የመከላከል አቋም ስለሌላቸው ነው።”

በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት የሚተላለፉ መጥፎ ወሬዎች አፍራሽ የሆኑ ተግባሮች እንደ ሆኑ በመገለጽ ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው ይህም በመጽሐፍ ነገሥት መጽሐፍ ወጥ ተጠቅሶ ከሚገኘው “ዘር ማነዘሮቹ ያወረሱት ሀብት አልሸጥም በማለት ለዘርማነዘሮቹ ሃብት ታማኝ በነበረው በናቦት ላይ ከደርሰው ጥፋት ጋር ተመሳሳይ እንደ ሆነ ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ በይበልጥ ለመረዳት በመጥፎ ወሬ የተነሳ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደርሰውን ታሪክ መመልከት በቂ እንደ ሆነ ገለጸው እወነቱን ከመጋፈጥ ወይም ከመስማት ይልቅ እስጢፋኖስን በድንጋይ ወገረው መገድል መርጠው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አውስተው በእዚህ ዓይነቱ የክፋት ወሬ የተነሳ በጣም የብዙ ሰዎች ሕይወት መበላሸቱን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

18 June 2018, 15:44
ሁሉንም ያንብቡ >