ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 13/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 13/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© Servizio Fotografico L'Osservatore Romano)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ““ቤተክርስቲያን እናት በመሆኗ የተነሳ እንስት ናት”

“ቤተክርስቲያን እናት በመሆኗ የተነሳ እንስት ናት”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮ “ቤተክርስቲያን እናት በመሆኗ የተነሳ እንስት ናት” ማለታቸው ተገለጸ።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አነሳሽነት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማሪያም ያለን ሐይማኖታዊ የሆነ ክብር እና ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ በማሰብ፣ በቤተክርስቲያን እረኞች አማካይነት በቤተክርስቲያን፣ በቅዱሳን ማኅበራት እና በምዕመናን ውስጥ የእናትነት መንፈስ እያደገ እንዲመጣ፣ በአጠቃላይ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ያለን እውነተኛ የሆነ ክብር እና እናትነቷን የሚገልጽ ሐይማኖታዊ ፍቅር ተጥናክሮ በሰዎች ልብ ውስጥ በማደግ፣ አማላጅነቷን ዘወትር መማጸን ያስችለን ዘንድ በማሰብ ይህ ጉዳይ በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረው እና የስነ-አምልኮ እና የቅዱሳን ምስጢራት ጉዳይ በሚንከባከበው እና በሚቆጣጠረው መንፍሳዊ ጉባሄ ጉዳዩ በጥልቀት ከተጠና በኃላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ማሪያም የቤተክርስቲያን እናት ናት” በማለት ባለፈው የካቲት 28/2010 ዓ.ም ማወጃቸው ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን ሐዋሪያት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ሆነው በመጸለይ ላይ በነበሩበት ወቅት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉበት የጴራቅሊጦስ በዓል በኃላ ባለው ቀን እንዲከበር ተወስኖ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ ውስጥ እንዲካተት የተደርገ ሲሆን “ማሪያም የቤተክርስቲያን እናት ናት”  የተሰኘው ዓመታዊ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 13/2010 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ በታላቅ መንፈሳዊነት በመላው ዓለም በሚገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ውስጥ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ በዓል በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 13/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ተከብሮ ማለፉ የታወቀ ሲሆን በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ቤተክርስቲያን እንደ ማሪያም እንስት እና እናት ናት” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህም አግባብ የአንድ እናት ስነ-ምግባር መለያ ባሕሪይ  ሊሆን የሚገባው ርኅራኄን መላባስ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

“ቤተክርስቲያን እንስት ናት”፣ በእዚህም ምክንያት ቤተክርስቲያን “እናት ናት” በእዚህ ረገድ ቤተክርስቲያን ይህንን የእናትነት መለያ ባሕሪይዋን ካጣች ደግሞ እንደ አንድ “የበጎ አድራጎት ማህበር ወይም የእግር ኳስ ቡድን” ትሆናለች በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያን ተባዕት በምትሆንበ ጊዜ ደግሞ በሚያሳዝን ሁኔታ ማፍቀር እና ፍሬያማ መሆን የማይቻል ወንድላጤ ሆና ትቀራለች ብለዋል።

ይህ ቀደም ሲል ያስነበብናችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 13/2010 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረውን እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስርዓተ አምልኮ የቀን መቁጠሪያ ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ የጰራቅሊጦስ በዓለ ከተከበረ በኃላ ባለው ቀጣይ ቀን እንዲከበር በተደርገው “ማሪያም የቤተክርስቲያን እናት” በመባል በሚጠራው አመታዊ በዓል ላይ ቅዱስነታቸው ያሰሙትን ስብከት ሲሆን  የእዚህ መነፈሳዊ በዓል ዋንኛው ዓለማ “በቤተክርስቲያን እረኞች፣ በመንፈሳዊ ማኅበራት እና በምዕመኑ ውስጥ ቤተክርስቲያን እናት ናት የሚለውን ስሜት ለማሳደግ ታስቦ የተሰየመ ዓመትዊ በዓል ሲሆን በእዚህም መልኩ እውነተኛ ወይም ሐቀኛ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ፍቅር በሰዎች ልብ ውስጥ እያደገ እንዲሄድ ለማድረግ ታስቦ የተሰየመ በዓል እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ማሪያም “እንደ አንድ ወይዘሮ” ሳይሆን የተጠቀሰችው ነገር ግን ሁል ጊዜም ቢሆን “የክርስቶስ እናት” እንደ ሆነች ተደርጋ በበርካታ ቦታዎች መጠቀሱዋን በመግለጽ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእርሷ የእናትነት ባሕሪይ መልኣኩ ገብርኤ ካበሰራት ጊዜ አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ተጠቅሶ እንደ ሚገኝ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው በእዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ በጥንት ጊዜ የነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ማሪያምን እንደ እናታቸው አድርገው በመቁጠር እና በእርሷ አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ የጀመሩት በእዚሁ ምክንያት እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

እናም ከዚህ ቤተክርስቲያን እናት ናት ከሚለው ከማሪያም ከመነጨ አመለካከት በመነሳት ይሄን አመለካከት እኛ የዚህን አንስታዊ ገጽታ መረዳት እንችል ዘንድ በመርዳት፣ ነገር ግን ይህ የእናትነት ባሕሪይ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሌለ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ማንነቷን ታጣለች፣ ወደ አንድ የበጎ አድራጎት ማህበር ወይም የእግር ኳስ ቡድን ወይም ወደ ማኛውም ነገር ትለወጣለች፣ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ልንላት ግን አንችልም።

አንድ እንስት የሆነች ቤተክርስቲያን ብቻ ናት ፍሬያማ ልትሆን የምትችለው፣ የእግዚኣብሔር ልጅ ከሴት ለመወለድ የፈለገው እኛን ይህንን መንገድ ልያስተምረን ፈልጎ እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“ዋናው አስፈላጊው ቁም ነገር ቤተክርስቲያን እንስት፣ የሙሽሪት እና የእናትነት ባሕርይ የተጎናጸፈች መሆኑዋን ማወቅ ነው። ይህንን በምንረሳበት ወቅት ቤተክርስቲያን ተባዕት ይሆናል፣ በእዚህም አካሄድ ቤተክርስቲያን በሚያሳዝን ሁኔታ ብቻውን ተገልሎ እንደ ሚኖር፣ ማፍቀር የማይችል፣ ፍሬያማ እንዳልሆነ እንደ አንድ ወንድ ላጤ ትሆናለች ማለት ነው። ያለ እንስት ቤተክርስቲያን ወደ ፊት መራመድ በፍጹም አትችልም፣ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ራሷ እንስት በመሆኑዋ የተነሳ ነው። ቤተክርስቲያን ይህንን የእንስትነት ባሕሪይ ያገኘችሁ ከማሪያም ነው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ የፈለገው እንዲሁ እንዲሆን ነው።”

እንክብካቤ ማድረግ እና ርኅራኄን ማሳየት የአንድ ሴት መለያ ባሕሪይ መሆኑን በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ማሪያም “የበኩር ልጅዋን በወለደች ጊዜ፣ በጨርቅ ጠቅልላው በግርግም ውስጥ እንዳስተኛችሁ” በእዚያም በጥንቃቄ፣ በትህትና እና በየዋሕነት እንዳገለገለችሁ ሁሉ ይህም የእናቶች ጠንካራ እና ልዩ የመለያ ባሕሪያቸው እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል...

“አንድ እናት የሆነች ቤተክርስቲያን በፍቅር መንገድ ላይ ትጓዛለች። በታላቅ ጥበብ ተሞልታ የፍቅር፣ የዝምታ፣ የርኅራኄ ቋንቋዎችን በመጠቀም እንዴት ዝም ማለት እንደ ሚገባት በሚገባ ታውቃለች። እናም አንድ ነብስ ወይም አንድ የእዚህች ቤተክርስቲያን አባል የሆነ አንድ ግለሰብ ቤተ ክርስቲያን እናት መሆኑዋን በመረዳት ትሁት፣ ርኅሩ፣ በፈገግታ እና በፍቅር የተሞላ መሆን ይኖርበታል።”

 

21 May 2018, 09:43
ሁሉንም ያንብቡ >