ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  20/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 20/09/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (© Servizio Fotografico L'Osservatore Romano)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ክርስቲያኖች “የግል ፍላጎቶቻቸው ባሪያዎች” መሆን አይገባም

“የክርስቲያን ደስታ የሚመነጨው ትንሽ እና ጣፋች ከሆነ ሕይወት ሳይሆን ከሰላም ነው”

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የክርስቲያን ደስታ የሚመነጨው ትንሽ እና ጣፋች ከሆነ ሕይወት ሳይሆን ከሰላም ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 20/2010 ዓ.ም በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች “የግል ፍላጎቶቻቸው ባሪያዎች” መሆን የለባቸውም፣ ነገር ግን በተቃራኒው በደስታ እና በመጽናናት መንፈስ የተሞሉ ሰዎች ሊሆኑ ይገባል ማለታቸው ተገልጸ።

የዚህ ዜና አቀናባሪ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ ቫቲካን

 “ደስታ የአንድ ክርስቲያን እስትንፋስ ሊሆን የገባል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእውነተኛ ሰላም ላይ የተመሰረተ ደስታ እንጂ፣ ክርስቲያኖች በአሁኑ ወቅት ዓለማችን እያቀረበልን በሚገኘው ባህል የተነሳ ደስታ የሚገኘው በተቻለን መጠን ቁሳቁሶችን በማጋበስ እንደ ሆነ አድርጎ ዓለም በሚያቀርብልን አሳሳች አስተሳስብ ሊሆን እንደ ማይገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው የክርስቲያኖች ደስታ ለሕይወታችን ጣዕም በሚሰጡ ጥቃቅን ነገሮች ላይ ሊወሰን እንደ ማይገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የላቲን ስርዓተ አምልኮ ተከታይ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ በእለቱ ከመጀመሪያው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መልእክት 1፡3-9 ላይ በተጠቀሰው እና አሁንም በእለቱ ከማርቆስ ወንጌል 10፡17-27 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ንብረቱን ትቶ እየሱስን መከተል ያልፈለገው ወጣት ሐብታም የነበረው ሰው ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ እውነተኛ የሆነ ክርስቲያን በፍጹም ሐዘንተኛ ሊሆን አይገባም ብለዋል።  “አንድ በደስታ የተሞላ ሰው መሆን ማለት የሰላም ሰው መሆን ማለት ነው፣ በመጽናናት የተሞላ ሰው መሆን ማለት ነው” ብለዋል።

ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል . . .

“የክርስቲያን ደስታ የአንድ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው፣ በልቡ ደስታ የሌለው አንድ ክርስቲያን ጥሩ ክርስቲያን ነው ሊባል አይችልም። ከክርስቲያን እስትንፋስ የሚወጣው ነገር ደስታ ብቻ ነው። ይህም ደስታ እርሱ የሚገዛው ወይም ደግሞ በእራሱ ጥረት የሚያገኘው ነገር ሳይሆን በልብ ውስጥ የደስታ ፍሬ እንዲኖር የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፣ በልባችን ውስጥ ደስታ እንዲኖር የሚያደርገው መንፍስ ቅዱስ ነው።”

በቀዳሚነት ክርስቲያናዊ ደስታ የተመሰረተበት ጠንካራ ዓለት “ማህደረ ትውስታ” ነው፣ ይህም ማለት “በእርግጥ ጌታ ለእኛ ያደርገልንን ነገር መርሳት በጣም ከባድ ነገር ነው፣ እንደገና ወደ አዲስ ሕይወት እንድንመለስ ስለሚረዳን ጌታ የዋለልንን ውለታ መርሳት በጣም ከባድ የሆነ ነገር ነው፣  እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ ከጌታ ጋር ለመገናኘት ያለን ተስፋ የክርስቲያን የደስታ ምንጭ ነው” ብለዋል። ማሕደረ ትውስታ እና ተስፋ እነዚህ ሁለት ክርስቲያኖች በደስታ እንዲኖሩ የሚረዱዋቸው ሁለት ዋና ዋና መሰረታዊ ነገሮች እንደ ሆኑ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ደስታ እንዲያው ጊዜያዊ የሆነ ወይም ባዶ የሆነ ደስታ ሳይሆን ነገር ግን ከሁሉም በላይ ሰላምን የሚያስገኝ ደስታ ነው ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. .

““ደስታ ማለት እንዲያው ሳቅ በሳቅ የሆነ፣ በሳቅ የተሞላ ኑሮ መኖር ማለት አይደለም። በፍጹም እንዲህ አይደለም! ደስታ ማለት እንዲያው ዝም ብሎ መዝናናት ማለት አይደለም። በፍጹም እንዲህ አይደለም! ደስታ ከእዚህ ይለያል። የክርስቲያን ደስታ ሰላም ነው። ይህ ሰላም ሥር መሰረት ያለው፣ ከልብ የመነጨ ሰላም፣ እግዚኣብሔር ብቻ ሊሰጠን የሚችለው ሰላም ነው። ይህንን ነው እንግዲህ የክርስቲያን ደስታ የምንለው። የእዚህ ዓይነቱን ደስታ ጠብቆ መኖር ግን ቀላል ነገር አይደለም።”

አሁን ያለው ዓለማችን ያለመታደል ሆኖ "ደስተኛ ያልሆነ ባህል" ያለው፣ ሰዎች እንዲዝናኑባቸው ለማስቻል ብዙ ቁሳቁሶች የሚመረቱበት ባሕል፣ አስደሳች ጣፋጭ ህይወት እንዲኖረን በማሰብ ጥቃቅን ነገሮች የሚከናወኑበት ባሕል በብዛት የሚንጸባረቁበት ወቅት ላይ ደርሰናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች ሁሉ የሰው ልጆች ምልኣት ባለው መልኩ ደስተኞች እንዲሆኑ በፍጹም እንደ ማይረዱዋቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በእርግጥ ደስታ እንዲሁ ከአንድ የገበያ ማዕከል የሚገዛ ነገር እንዳልሆነ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በተቃራኒው ደስታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው፣ የእዚህ ዓይነቱ ደስታ ደግሞ በፈተና ወቅት  እና በመከራ ውስጥ በምንገባበት ወቅት ሳይቀር ቀጣይ የሆነ ደስታ እንዲኖረን ያደርጋል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

“"ጥሩ የሆነ የመቅበጥበጥ ስሜት አለ፣ ነገር ግን ጥሩ ያልሆነ ነገርም አለ፣ ለደኽንነታችን የሚሆኑትን ነገሮች በየቦታው መፈለግ፣ ሁሉም ቦታ ደስታን መፈለግ። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው ወጣት ሀብታም ሰው ሀብቱን ቢተው ደስተኛ ሊሆን እንደማይችል በማሰብ ፈራ። ደስታ እና መጽናናት የክርስቲያን እስትንፋስ ሊሆን ይገባል።”

28 May 2018, 09:55
ሁሉንም ያንብቡ >