ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ “ማዕረገ ጵጵስናን የተቀበልነው መንጋውን ለመጥበቅ ነው”

የጵጵስና ማዕረግ ራሳችንን ለማገልገል የሚውል ማዕረግ ሊሆን አይገባም

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ “ማዕረገ ጵጵስናን የተቀበልነው ራሳችንን ለማገልገል ሳይሆን መንጋውን ለመጥበቅ ነው”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመና በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያስርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 07/2010 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የጵጵስና ማዕረግ ራሳችንን ለማገልገል የሚውል ማዕረግ ሳይሆን ነገር ግን መንጋዎችን ለመጠበቅ የተሰጠን ኃላፊነት ነው ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ ደንብ አቆጣጠ መሰረት በቀዳሚነት ከሐዋሪያት ሥራ 20፡17-27 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች “መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው” ስለእዚህ ወደ እዚያው መሄዴ ነው በማለት እንደ ተሰናበተ በሚገልጸው  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመስርተው ባደርጉት ስብከት እንደ ገለጹት ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመንፈስ ቅዱስ ታዛዥ የነበረ እና መንጋዎቹን የሚወድ ሰው እንደ ነበረ ጨምረው የገለጹት ቅዱስነታቸው ሁሉም ጳጳሳት ይህንን የቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስን ፈለግ ይከተሉ ዘንድ ልንጸልይላቸው ይገባል ብለዋል።

"ይህ ቆራጥ የሆነ እና በልበ ሙሉነት የሚደረግ ጉዞ ነው፣ ይህ ጉዞ የእያንዳንዱን ጳጳስ መንገድ የሚያሳይ እርምጃ ነው” በማለት ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ ከሐዋሪያት ሥራ ከምዕራፍ 20፡17-27 ተወስዶ በተነበበው ጳውሎስ በኤፌሶን የሚገኙትን የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን እና ደቀመዛሙርቱን  ስብስቦ  “መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው” ስለእዚህ ወደ እዚያው ሊሄድ የገባኛል ብሎ እንደ ተናግረ በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ጳውሎስ በእዚህ ረገድ በስብሰባው ላይ በመጀመሪያ ደረጃ የህሊናን ምርመራ በማድረግ ለኅብረተሰቡ ያበረከተውን በጎ ተግባራት በመግለጽ በእዚያ የተገኙ ሰዎች ውሳኔ እንዲሰጡበት እንዳቀረበላቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በእዚህ ረገድ ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህንን ነግግር በሚያደርግበት ወቅት የተሳካ ተግባር በመፈጸሙ የተነሳ ትንሽዬ ኩራት ቢጤ ነገር የተሰማው ይመስለኛል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ኩራት የመነጨው ከሁለት ነገሮች ነው “በእርሱ ኃጢአት እና እርሱን ከኃጢያት ነጻ ካደርገው በክርስቶስ መስቀል” የመነጨ ኩራት ነም ማለታቸው ተገልጹዋል።

“መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ ስላለኝ ወደ እዚያው ለመሄድ እፈልጋለሁ” የሚለውን የሐዋሪያው ጳውሎስ ቃል በማስታወስ ስብከታቸው የቀጠሉት ቅዱስነታችው “አንድ ጳጳስ ከእዚህ ከሐዋሪያው ጳውሎስ ተመክሮ እና ልምድ መማር እንደ ሚገባው፣ አንድ ጳጳስ መንፈስ ቅዱስን በማስተዋል ጥበብ ለይቶ ማወቅ እንዳለበት፣ አንድ ጳጳስ አንድ የሚናገር መንፈስ የመጣው ከእግዚኣብሔር ነው ወይስ ከዓለም ነው? የሚለውን ለይቶ የማወቅ ጥበብ ሊኖረው እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ መከራ እና መስቀል እንደ ሚጠብቀው  በሚገባ ትረድቶ እንደ ነበረ በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ የቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ስጋት ኢየሱስ ወደ ኢየስሩሳሌም በገባባት ወቅት ከነበረው ሁኔታ ጋር እንደ ሚመሳሰል ገልጸው ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው መከራን ለመቀበል ነው፣ በተመሳሳይ መልኩም ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ኢየስሩሳሌም የሄደው መከራን ለመቀበል በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ጉዞውን ለጌታ በአደራ መልክ በመስጠት ለእዚህ ጉዞ ታዛዥ ሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ ላቀረበለት ጥሪ ምላሽ እንደ ሰጠ በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩም አንድ ጳጳስ ያለምንም ስጋት ወደ ፊት መሄድ ይኖርበታል ነገር ግን ይህንን ጉዞ ማድረግ የሚገባው ልክ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዳደረገው በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በመጨረሻም ሐዋርያው ጳውሎስ በታላቅ ሐዘን በእዚያ የነበሩትን ሰዎችን ከተሰናበት በኃላ አንዳንድ  ምክሮችን ሰጥቱዋቸው እንደ ነበረ፣ እነዚህ ምክሮች እና ሐሳቦች ግን ዓለማዊ የሆኑ ምክሮች እና ሐሳቦች እንዳልነበሩ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ነገር መጣም ጥሩ ነገር ስለሆነ ይህንን ለአንተ ተዋለሁ፣ ይህንን ደግሞ ለእንተ ሰጣለሁ፣ ያንን ደግሞ ለአንተ እስጣለሁ” በማለት ዓለማዊ የሆኑ ነገሮችን እና ምክሮችን እንዳልሰጣቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ሐዋሪያው ጳውሎስ በወቅቱ ለኤፌሶን ሰዎች የሰጣቸው ትልቁ ስጦታ ታላቅ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር እና በእዚህ ፍቅር ላይ መሰረቱን ባደረገ መልኩ መንጋውን በሚገባ ጠብቆ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። “በቅድሚያ ራሳችሁ ከእዚያም መንጋችሁን አነቃቁ፣ በንቃት መነጋችሁን ጠብቁ፣ እናተ ጳጳስ የሆናችሁት ለመንጋው ነው፣ መንጋውን ለመጠበቅ ነው እንጂ እንዲዲሁ ዝም ብላችሁ ቤተክርስቲያን የሰጠቻችሁን ስልጣን ተቆናጣችሁ ለመኖር አይደለም፣ በፍጹም ለእዚህ አይደለም ማለታቸው ተገልጹዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን የነበሩትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች  በተሰናበተበት ወቅት እነሱን በእግዚኣብሔር ጥበቃ ሥር እንዲሆኑና እግዚኣብሔር እንዲረዳቸው ለእርሱ በአደራ ከሰጣቸው በኃላ ጉዞውን ወደ ኢየሩሳሌም አድርጎ እንደ ነበረ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ከዛን በኃላ እሱ ወደ እራሱ ተመክሮ በመመለስ «እኔ ብር ወይም ወርቅ ወይም ማንንም ልብስ አልፈለግም» በማለት ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች የሰጠው የመጨረሻ ቃል የምስክርነት ቃል ነበር። የምስራች ቃልም ነበር፣ በተጨማሪም ተግዳሮት የተሞላው ቃል ነበር። “እኔ ይህንን መነገድ ተጉዣለሁኝ እናንተም በእዚሁ መልኩ መጓዝ ቀጥሉ። ይህ ምስክርነት “ይህንን ለአንተ እተዋለሁ፣ ያንን ለአንተ እተውልሃለሁ” ከሚሉት እና ከመሳሉት ዓለማዊ ከሆነ አንድ ምስክርነት እንዴት በእጅጉ የራቀ ምስክርነት ነው። በእዚህ ረገድ ሐዋሪያው ከእግዚኣብሔር ጸጋ በቀር፣ ከሐዋሪያው ብርታት በቀር፣ ከእየሱስ ግልጸት በቀር እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርሱ ከሰጠው ደኽንነት በሰተቀር ሐዋሪያው ጳውሎስ ምንም ሌላ ነገር እንዳልነበረውም።

“ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በማንብበት ወቅት እኔ ራሴ ጳጳስ በመሆኔ የተነሳ ለእነዚህ ሐሳቦች ልገዛ ይገባኛል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል . . .

እኔም በእዚህ መልኩ መሰናበት እችል ዘንድ ጌታ ጸጋውን እንዲሰጠኝ እጠይቃለሁ። እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ የህሊና ምርመራ በማድረግ ብቻ ነገሮችን ለማሸነፍ አልችልም . . .ነገር ግን እግዚኣብሔር መልካም እና መኃሪ ነው። በእዚህ ረገድ ሁላችሁን ጳጳሳት አስባችኃለሁ። ጌታ በዚህ ፍቅር፣ በመንፈስ ቅዱስ በመታመን፣ በዚህ ጥንካሬ፣በእዚህ ኃይል በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ተሞልተን በዚህ መንገድ መሄድ እንድንችል ለሁላችንንም ጸጋውን ይስጠን” ።

17 May 2018, 13:16
ሁሉንም ያንብቡ >