ፈልግ

2018-04-17 Messa Santa Marta 2018-04-17 Messa Santa Marta  (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ኢየሱስን የምንከተለው የግል ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ብቻ ሊሆን አይገባም!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ኢየሱስን መከተል የሚገባን የግል ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ብቻ ብለን ሳይሆን እመነታችንን ለማጠንከር ጭምር ሊሆን የገባል ማለታቸው ተገለጸ።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ፡ ኢየሱስን የምንከተለው የግል ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ብቻ ሊሆን አይገባም!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ኢየሱስን መከተል የሚገባን የግል ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ብቻ ብለን ሳይሆን እመነታችንን ለማጠንከር ጭምር ሊሆን የገባል ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱነታቸው ይህንን የተናገሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዚያ 08/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተሰበሰቡበት ባሳረጉት ማስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን  በወቅቱ  ያሰሙት ስብከት ትኩረርቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ ከዩሐንስ ወንጌል 6:22-29 ላይ ተወዶ በተነበበው እና ኢየሱስ በአምስት እንጄራ እና በሁለት ዓሳ አምስት ሺ ሰው መመገቡን በሚገልጸው የቅዱስ የወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል። በወቅቱ ይህንን ታላቅ ተዕምር ያየ ሕዝብ ኢየሱስን ንጉሳቸው አድርጎ ለማንገስ በፈለጉበት ወቅት ኢየሱስ ከእዛ ሸሽቶ መሄዱን እና ከቆይታ በኃላም ሕዝቡ ኢየሱስን ፈልጎ እንዳገኙት በሚገልጸው የወንጌል ክፍል ዙሪያ ያጠነጠነ ስብከት እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።  

“ኢየሱስን የምክተለው የግል ጥቅሜን ለሟሟላት በማሰብ ብቻ ነው? ወይስ ለእምነቴ ስል ነው?” ኢየሱስ በእኔ ሕይወት ውስጥ ምን ዓይነት ተግባራትን ፈጽሙዋል? ኢየሱስ ላሳየኝ ፍቅር እንዴት ነው ምላሽ ለመስጠት የምችለው? የሚሉትን ጥያቄዎች ቅዱስነታቸው በወቅቱ ማንሳታቸው ተግልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው “ኢየሱስን የምንከተለው የግል ፍላጎቶቻችንን ብቻ ለሟሟላት በማሰብ፣ ለምሳሌም ተዕምራትን በሕይወታችን ውስጥ እንዲፈጽም በማሰብ ብቻ ነው? ወይስ እምነታችን እንዲጠነክር የእርሱን ቃል ለመሰማት ነው? በማለት ጥይቄን ማንሳታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህንንም በጥልቀት ለመረዳት ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ የፈጸማቸውን ድንቅ ተግባራት እና ፍቅር ማስታወስ ይገባል ብለዋል።

ኢየሱስን የምንፈልገው ተዕምራትን  በሕይወታችን ውስጥ እንዲያከናውን በማሰብ ወይም በመፈለግ ብቻ ሊሆን እንደ ማይገባ የገለጹት ቅዱንስታቸው በእለቱ ከዩሐንስ ወንጌል (6: 22-29) ተወስዶ በተነበበው የወንጌል ክፍል ላይ ቀደም ሲል እንደ ገለጽነው ኢየሱስ በአምስት እንጄራ እና በሁለት ዓሳ አምስት ሺ ሰዎችን በመመገቡ የተነሳ ይህንን ተዕምር ያዩ ሰዎች በእዚህ ኢየሱስ ባሳያቸው ልዩ ተዕምር ተማርከው ንጉሣቸው ሊያደርጉት እንደ ፈለጉ፣ ኢየሱስ ባወቀበት ወቅት ለእመንት ሳይሆን ለግል ፍላጎታቸው ብቻ እንደ ሚፈልጉት ተርድቶ ከእዚያ አከባቢ እንደ ሸሸ  ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ሕዝቡ ኢየሱስን ፈልጎ ባገኘበት ወቅት “ረቢ መቼ ወደዚህ መጣህ” ብለው በጠየቁት ወቅት ኢየሱስም ““እውነት እላችኋለሁ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ እንጂ፣ ታምራዊ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም” (ቁ.26) ብሎ መልሶላቸው እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ በወቅቱ ኢየሱስን ሲከተሉት የነበሩ ሕዝቦች ሁለት ዓይነት ገጽታ እንደ ነበራቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ኢየሱስ የሚናግራቸው ነገሮች ሁሉ ልብ የሚነኩ ጉዳዮች በመሆናቸው የተነሳ ይህንን የሕዝቡን ልብ የሚነካ የእርሱን ንግግር ለመስማት የሚከተሉት ሰዎች በአንድ ጎራ እንደ ሚመደቡ ይህም ማለት እምነታቸውን ለማጠንከር በማሰብ እርሱን የሚከተሉ ሰዎች በአንድ ጎራ የሚሰልፉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ አምስት ሺ ሰዎችን በመመገቡ የተነሳ የግል ፍላጎቶቻቸውን በእዚሁ መልኩ ለሟሟላት የሚከተሉት ሰዎች ደግሞ በሌላ ጎራ እንደ ሚሰለፉ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በአጠቃላይ በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱት ሕዝቦች መልካም የሚባል እምነት የነበራቸው፣ ነገር ግን ይህ እምነት በጥቂቱም ቢሆን ከግል ጥቅማቸው ጋር የተቆራኘ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ሁኔታ የሚታየውን አነስተኛ የሆነ እምነት ኢየሱስ እንደ ሚገስጸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

ኢየሱስ አጋንት ያደረበትን ሰው በፈወሰበት ወቅት (በማርቆስ ወንጌል 5:1-20 ላይ እንደ ተጠቀሰው ማለታቸው ነው) ከእዚህ ሰው የወጡት አጋንቶች በአቅራቢያውም በሚገኝ ኰረብታ ላይ ብዙ የዐሣማ መንጋ ውስጥ እንዲገቡ ባዘዘበት ወቅት ሁለት ሺህ ያህል ዐሣማዎችም በገደሉ አፋፍ በመንደርደር ቊልቊል ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው እንደ ሞቱ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱነታቸው በወቅቱ በእዚያ መንደር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ዓሳማዎቻቸው በመሞታቸው የተነሳ ምግኘት የሚገባቸውን ገቢ ወይም ገንዘብ በማጣታቸው የተነሳ ሕዝቡ አገራቸውን ለቆ እንዲሄድላቸው ኢየሱስን እንደ ጠየቁት ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። በተመሳሳይ መልኩም ከለመጽ በሽታ ከነጹ 10 ሰዎች (ሉቃስ 17፡11-19) መካከል እግዚኣብሔርን እያመስገነ ወደ ኢየሱስ የተመለሰው አንድ ሰው ብቻ እንደ ሆነ በስብከታቸው ወቅት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ቀሪዎቹ ዘጠኙ ግን ይህንን ተዕምር በእነርሱ እንዲፈጸም ያደርገውን ኢየሱስን ዘንግተው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። ለእዚህም ነው እንግዲህ በትላንታነው እለት ከዩሐንስ ወንጌል 6፡25 ጀምሮ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ ሕዝቡን “ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ” ብሎ የገሰጻቸው በእዚሁ ምክንያት እንደ ሆነው ያስርዱት ቅዱስነታቸው ሁል ጊዜም ቢሆን “የእግዚኣብሄርን ቃል እና የእርሱን ፍቅር በመፈለግ ብቻ መትጋት እንደ ሚኖርብን ጨምረው ገልጸዋል።

በመቀጠል በወቅቱ ከሐዋሪያት ሥራ 6፡8-15 በቀዳሚነት ተወስዶ በተነበበው እና ስለ ሰማዕቱ እስጢፋኖስ ሕይወት በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ እስጢፋኖስ ኢየሱስን መከተል የሚያስክትለውን መዘዝ በቅጡ ሳይረዳው ኢየሱስን መስበክ እንደ ጀምረ ገልጸው በወቅቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ የሚናግረው ንግግር በጣም ግልጽ የሆነ ንግግር እንደ ነበረ ገልጸው ይሁን እንጂ ሕዝቡ እርሱ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አለመቻለቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ቅዱስ እስጢፋኖስ ኢየሱስን መከተል የሚያስክትለውን መዘዝ በቅጡ ሳይረዳው ኢየሱስን መከተል እንደ ጀመረ በድጋሚ ያወሱት ቅዱስነታቸው “ይህ ጉዳይ ይመቸኛል፣ ይህ ጉዳይ ደግሞ አይመቸኝም” በማለት ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያስቀምጥ ኢየሱስን ተከትሎ እንደ ነበረ ገልጸው ኢየሱስን በጣም ከመወደዱ የተነሳ እርሱን እንደ ተከተለው፣ መጨረሻውም ኢየሱስን የገጠመው ዓይነት ገጠመኝ እንደ ሚገጥመው እርግጠኛ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በወቅቱ ሕዝቡ የቅዱስ እስጢፋኖስን ስም በሐሰት በማጥፋት እንደ ወንጀለኛ እንዲቆጠር በማድረግ በወጥመዳቸው ውስጥ እንዲገባ ካደርጉት በኃላ ስለኢየሱስ ምስክርነት በመስጠቱ የተነሳ ብቻ በድንጋይ ተወግሮ እንዲሞት እንዳደርጉት የገለጹት ቅዱነታቸው በእዚህ ረገድ ቅዱስ እስጢፋኖስ የራሱን የግሉን ፍላጎት ለሟሟላት ሳይሆን ሕይወቱንም በመስጠት ጭምር ኢየሱስን መመስከሩን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በእዚህም አግባብ ዛሬ እኛ ሁላችን ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባን ጉዳይ መሆን የሚገባው “እኔ ኢየሱስን የምክተለው ለምንድነው?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ከእዚህ ቀደም ኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ ያከናወናቸውን መልካም ተግባራት ማስታወስ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጭመረው ገልጸው ይህንን በምናደርግበት ወቅት ኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ የፈጸመው ታላላቅ ተግባራት እንዳሉ መረዳት እንችላለን  ብለዋል። ከእዚህ በመቀጠል ለራሳችን ማቅረብ የሚገባን ጥያቄ የሚሆነው ደግሞ ኢየሱስ ለእኔ እነዚህን ውብ ነገሮች በሕይወቴ ውስጥ ከፈጸመ፣ እኔ በበኩሌ ለኢየሱስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተግቢ እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ሆይ አንተ ለእኔ ብዙ ፍቅር ሰጥተህኛል እና እኔም በበኩሌ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጻለው ልንለው የገባል ካሉ በኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

16 April 2018, 13:15
ሁሉንም ያንብቡ >