ፈልግ

ብፁዕ ካርዲናል  ብርሃነየሱስ ሱራፌል  “ቤተሰብ እና ጋብቻ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ በመካሄድ ላይ ኮንፈረንስ እየተካፈሉ የምያሳይ ምስል ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል “ቤተሰብ እና ጋብቻ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ በመካሄድ ላይ ኮንፈረንስ እየተካፈሉ የምያሳይ ምስል 

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም አትባርክም መባሉ ተገለጸ!

በሰሜን አሜሪካ ኦስቲን የሚገኘው የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የቤተሰብ እና ባሕል ጥናት ማዕከል “ቤተሰብ እና ጋብቻ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ የሁለት ቀን ኮንፈረንስ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ግንቦት 20 እና 21 /2016 ዓ. ም “ጋብቻ እና ቤተሰብ” በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጰያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት የመጡ ካርዲናሎች፣ ጳጳሳት፣ ካህናት እና ሊቃውንት የተሳተፉበት ሲሆን የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ መሰረታዊ ስለሆነው ጋብ ቻና ቤተሰብ ትኩረት በሚያደርገው ዐውደ ጥናት ላይ ለመገኘት እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተቀበሏቸው ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስንና የካቶሊክ ትምህርተ ክርስቶስ (ኤፊ.5:21-6:4; ቆላ 3:18-21; 1Pጴ3:1-7) ካ.ት.ክ ቁጥር 2202-2204) በመመርኮዝ ‹‹ ወንድ እና ሴት በጋብቻ ሲጣመሩ ከልጆቻቸው ጋር ቤተሰብ ይመሰርታሉ፡፡ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴትን በመፍጠሩ ቤተሰብን መሰረተ ….. ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ትንሿ ቤተክርስቲያን ተብሎ መጠራት አለበት ምክንያቱም የእምነት፣ የተስፋ እና የፍቅር ማኅበረሰብ ነውና›› ብለዋል። ብዙ ጥያቄ እያስነሳ ያለውን የተመሳሳይ ፆታ ጥምረትን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስንና ትምህርተ ክርስቶስን በመጥቀስ “….መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በመመርኮዝ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት የተመሳሳይ ፆታ ጥምረትን ሁልጊዜ የተፈጥሮ ህግን የሚቃረን በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ታስተምራለች›› (ዘፍ 19:1-29፤ ሮሜ 1:24-27፤ 1ቆሮ 6:10 1ጢሞ 1:10) ት.ም.ክ 2357 ይህ የቤተክርስቲያን አቋም እንዳልተቀየረም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ሰላም ካቶሊክ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ

29 May 2024, 15:30