ፈልግ

ሲስተር ኖርማ ፒመንቴል በሮም በተካሄደው የታሊታ ኩም ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ሲስተር ኖርማ ፒመንቴል በሮም በተካሄደው የታሊታ ኩም ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት 

ሲስተር ኖርማ ፒመንቴል በተልእኳቸው ላይ የተመሰረተ የህይወት ልምዳቸውን በታሊታኩም ጉባኤ ላይ አካፈሉ

ሲስተር ኖርማ ፒመንቴል በዩናይትድ ስቴትስ ድንበር አከባቢ ለሥራ ሲንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ያጋጠማቸውን የህይወት ተመክሮ በታሊታ ኩም 2ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለነበሩ ተሳታፊዎች አካፍለዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

“ዳርቻዎቹ ወደ እኛ መጡ” ሲሉ ነበር ሲስተር ኖርማ በሮም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ባለው መንደር ላይ በተካሄደው 2ኛው የታሊታ ኩም ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለነበሩ ተሳታፊዎች ማክሰኞ ጥዋት ያደረጉትን ንግግር ሲጀምሩ ፤ ሲስተር ኖርማ ፒሜንታል ሜክሲኳዊ-አሜሪካዊ የኢየሱስ ሚስዮናውያን አባል እና የሪዮ ግራንዴ ቫሊ የተባለ የካቶሊክ በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ናቸው።

በቴክሳስ-ሜክሲኮ ድንበር አከባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች የስደተኞች ጎርፍ ማየት የጀመሩት በ2006 ዓ.ም. ላይ እንደሆነ የተናገሩት ሲስተሯ፥ከረዥም እና አደገኛ ጉዞ በኋላ ሰዎች ከጥምቀት ጋር የሚመሳሰል የመጀመሪያውን በእንባ የታጀበ ሻወር ሲወስዱ እንደነበር አስታውሰዋል።

ሲስተር ኖርማ ንግግራቸውን በመቀጠል የሕፃናት ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ስለተፈጠረው ቀውስ በማንሳት፥ ይህ ብዙዎችን ያስጨነቀው ሁኔታ የተፈጠረው የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ህፃናቱን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲል ከወላጆቻቸው ለይቶ ለመውሰድ ባደረገው እርምጃ ነበር ብለዋል።

ወላጆቹ በልጆቻቸው ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል ለማወቅ ወደ እሳቸው ይመጡ እንደነበር በመጥቀስ፥ በዚህም ምክንያት “ወላጆቹ ይጠይቁኝ ስለነበረው ልጆች መረጃው ስላልነበረኝ ወደ አንዱ የማቆያ ማእከላት እንዲያስገቡኝ አንድ የአካባቢውን ዳኛ ጠየኳቸው” ብለዋል።

በልጆች ማቆያ ማእከል ውስጥ

“ከዚያ በፊት ማንም ሰው ወደ ማቆያ ቦታው ገብቶ አያውቅም” ያሉት ሲስተሯ፥ በመሠረቱ ከእኔ በኋላ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ወደ እነዚህ ማዕከላት እንዲገቡ የመግቢያ በሮችን ከፍቻለሁ… ያየሁት ነገር ለማመን የሚከብድ እና ልቤን የሰበረ ነገር እንደነበር እና እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከ10 ዓመት የማይበልጡ ትንንሽ ልጆችን እንዴት በእንደዚህ ዓይነት እስር ቤት ውስጥ እናቆያለን የሚለውን ለመረዳት ሞከርኩ። …. ይሄ ቦታ 300 ሰዎችን ብቻ ነው መያዝ የሚችለው …. ነገር ግን በቦታው ከ1000 በላይ ልጆች እንደነበሩ ግልጽ ነው… ለተወሰነ ጊዜያትም እዚያው ነበሩ” በማለት ነበር ስለ ማዕከሉ የገለጹት።

ሲስተር ኖርማ ልጆቹ ወደነበሩበት የመስታወት ግድግዳ ባላቸው ሴሎች ውስጥ መግባት ፈለገው ነበር። መግባት አይቻልም በተባሉ ጊዜም ለጥበቃ መኮንኑ ከልጆቹ ጋር መጸለይ እንደሚፈልጉ እንደነገሩት በማስታወስ፥ “መጸለይ የምትፈልግ መነኩሴን እንዴት እምቢ ትላለህ? ይሄ ትክክል ነው? አልኩት፥ ከዚህ በኋላ ወደ ውስጥ ገባሁ” ካሉ በኋላ፥ ያ ክስተት እስካሁን ካጋጠማቸው ሁሉ በጣም አስቸጋሪው ገጠመኝ እንደሆነ ተናግረው፣ ነገር ግን ከዚህም ባለፈ ይሄ ክስተት በተልዕኮዋቸው ‘ጽናት’ እንዲኖራቸው እንዳደረጋቸውም ገልጸዋል።

የተለወጡ ፖሊሲዎች እና አደጋዎች

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የኢሚግሬሽን ፖሊሲውን ሲቀይር፣ የተደራጁ ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችም በዛው ልክ ከስደተኞች ገንዘብ የሚበዘብዙበትን ስልት ቀይረዋል ሲሉ ሲስተር ኖርማ አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የሜክሲኮ ህገ ወጥ የሰው ዝውውር ወንጀለኞች ስደተኞቹ ወደብ ላይ የመግቢያ ፍቃድ በመጠባበቅ ባሉበት ወቅት በማገት እና ድብደባ በመፈጸም ለዘመዶቻቸው ስልክ ደውለው ብር እንዲያስልኩ ያደርጓቸዋል ብለዋል።

በድንበር ላይ ርህራሄን ማግኘት

ሲስተር ኖርማ ያቀረቡትን ንግግር ያጠናቀቁት ከብዙዎች አንዱ በሆነው የድንበር ጠባቂ መኮንን ታሪክ ሲሆን፥ አንድ ስደተኛ አባት ስለራሳቸው ከተናገሩት ታሪክ ጋር የማይመሳሰል አዲስ ጫማ አድርገው እሳቸው በነበሩበት የማክአለን ቴክሳስ ማእከል መምጣታቸውን አስታውሰው፥ ይህ ከመሆኑ በፊት ስደተኛውን “የያዘውና ስለ ጉዳያቸው የሚከታተለው” መኮንን ሰውዬው በቁስል ፕላስተር የታሸገ እና ባዶ እግሩን ወደ ድንበር መምጣቱን በማየት፥ ስለመጡበት ጉዳይ ሲነግሩት አባት ስደተኛውን ታሪክ እየሰማ “እንባውን ሲያፈስ” ነበር። መኮንኑ ወደ መኪናው በመሄድ አዲስ ውድ ጫማ ይዞ ተመለሰ፣ ከዚያም የራሱን ካልሲ አውልቆ፣ ካልሲውን እና ጫማውን ለአባት ስደተኛው አደረገ። ሲስተር ኖርማ ስለ አሜሪካዊው ደግነት በማስታወስ  “አሜሪካ ማለት ይህች ናት” ብለዋል።
 

22 May 2024, 22:07