ፈልግ

የህጻናትን ባርነት ለመቀልበስ ሰፊ የሆነ የሕዝብ ግንዛቤን መፍጠር ያስፈልጋል መባሉ ተገለጸ! የህጻናትን ባርነት ለመቀልበስ ሰፊ የሆነ የሕዝብ ግንዛቤን መፍጠር ያስፈልጋል መባሉ ተገለጸ!  ((c) Missio Österreich)

የህጻናትን ባርነት ለመቀልበስ ሰፊ የሆነ የሕዝብ ግንዛቤን መፍጠር ያስፈልጋል መባሉ ተገለጸ!

የ"ሚሲዮ ኦስትሪያ" ባልደረባ አቶ ክሪስቶፍ ሌኸርሜይር እንዳሉት የሸማቾች ግንዛቤ እና ባህሪ መረዳት በአለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናትን የሚጎዳውን የህጻናት ባርነት እና የጉልበት ስራን ለመዋጋት የመጀመሪያ እርምጃዎች ናቸው ያሉ ሲሆን ዓለም አቀፍ የሕፃናት ባርነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ሕፃናትን ከጉልበት ሥራ ለማላቀቅ የቤተ ክርስቲያን ድርጅቶች ስላደረጉት ሥራ አቶ ሌኸርማይር በሰፊው ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሚያዚያ 7/2016 በክርስቲያን የባህል ንቅናቄ (Movimiento Cultural Cristiano -MCC) በማህበራዊ ፍትህ እና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ላይ የተሰማራው በስፔን አገር የተመሰረተው የካቶሊክ ምዕመናን ድርጅት የሚያበረታታ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን እና በህፃናት ላይ የሚፈጸመውን ባርነት የሚቃወም አለም አቀፍ ቀን ተዘክሮ ማለፉ ይታወቃል።

ኢቅባል ማሲህ

የዚህ አመታዊ ክብረ በዓል አነሳሽ የ12 አመቱ ፓኪስታናዊ ክርስቲያን ባርያ ኢቅባል ማሲህ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 1995 ዓ.ም በርካታ ሕህፃናት እንደ ባሪያ አድርጎ ይጠቀም የነበረው 'ምንጣፍ ማፍያ' የተባለውን የወንጀለኞች ቡድን በማጋለጡ የተገደለው ነው።

ለስድስት ዓመታት በፑንጃብ ምንጣፍ ኢንዱስትሪ ውስጥ የባርነት ሰለባ የነበረው ኢቅባል ከ3,000 በላይ የፓኪስታን ህጻናትን ከአስገዳጅ ባርነት እንዲያመልጡ ረድቷል እና በመላው አለም ስለ ህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ንግግር አድርጓል። የእሱ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አስገኝቶለታል።

እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም የሪቦክ ወጣቶችን በተግባር ሽልማት ተቀበለ ። በእርሱ መንፈስ ተነሳሽነት እንደ "ልጆችን ነጻ ማውጣት" የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት በካናዳ እንዲመሰረት ማነሳሳቱ የተገለጸ ሲሆን ይህ ድርጅት በፓኪስታን ከ20 በላይ ትምህርት ቤቶች ያሉት ኢቅባል ማሲህ ሻሂድ የህፃናት ፋውንዴሽን ያሉ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ አነሳስቷል። እ.ኤ.አ. በ2000 ከሞት በኋላ “የዓለም የህፃናት ሽልማት ለህፃናት መብት” ተሸልሟል። የዩናይትድ ስቴትስ የሰራተኛ ክፍል የአለም አቀፍ ሰራተኛ ጉዳይ ቢሮ (ILAB) አመታዊ “የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለማስወገድ ኢቅባል ማሲህ የተሰኘ ዓመታዊ ሽልማት” በየዓመቱ እንምያዘጋጅ ይታወቃል።

ይህ ድርጅት ከግድያው ጀምሮ የክርስቲያን ባህል ንቅናቄ በአለም አቀፍ ደረጃ በህፃናት ባርነት ላይ ዘመቻ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን የእዚህ ዓይነት ብዝበዛ ከህጻናት ጉልበት ብዝበዛ የተለየ መሆኑን በማሳየት በዚህ ሁኔታ ህጻናት የቤተሰብን ዕዳ ለመክፈል እንዲሰሩ ስለሚገደዱና አሠሪውን ግለሰብ ጥለው መሄድ አይችሉም። እነሱን መበዝበዝ ይቀጥላሉ፣ ምንም እንኳን የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ በቀጠታ ባርነት ባይሆንም የልጆችን ትምህርት እና እድገትን የሚያደናቅፍ ነው እና በአስከፊው መልክ "አደገኛ ስራ" ጤንነታቸውን እና ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነው።

ቢያንስ 160 ሚሊዮን ህጻናት በአስገዳጅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል

ድህነት በአለም አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 160 ሚሊዮን ህጻናትን የሚያጠቃ ለተለያዩ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ዋና መንስሄ ነው። የጉልበት ብዝበዛ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እና እንግልት በአለም ላይ ላሉ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ህፃናት የእለት እንጀራ እንዳያገኙ የሚያደርግ ነው፣ በተለይ በምዕራቡ ዓለም።

የቫቲካን ዜና ሕፃናት ባሪያዎች በፓኪስታን በጡብ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዲሠሩ የሚገደዱበትን አስከፊ ሁኔታ በተመለከተ በርካታ ምርመራዎችን ያደረጉትን የኦስትሪያ ሚስዮ ድርጅት አሌዌልት መጽሔት ዋና አዘጋጅ አቶ ክሪስቶፍ ለኸርማይርን አነጋግሯል እና እንዲሁም ስለ ብዝበዛ ዘግቧል ። በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ውስጥ ኮልዌዚ በተባለው የኮባልት ማዕድን ማውጫ ውስጥ ያሉ ልጆች ሁኔታ ጨምሮ ዘግቧል።

የቤተ ክርስቲያን ድርጅቶች የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛንና ባርነትን ለማስወገድ የሚያደርጉት ጥረት

ከአቶ ከክሪስቲን ሴውስ ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ፣ ልጆችን ከባርነት ለማላቀቅ ስለ ቤተክርስቲያኗ ጥረት እና ተነሳሽነት ተናግሯል፣ ይህም በዋነኝነት ቤተሰቦቻቸውን አማራጭ የገቢ ምንጭ በማቅረብ ልጆቻቸው ከስራ ይልቅ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ነው። አቶ ከክሪስቲን ሴውስ እንዳብራሩት ከሆነ "ወላጆች ብዙውን ጊዜ ልጆቻቸውን እንዲሰሩ ያስገድዳሉ፣ ነገር ግን አማራጭ ገቢ ካላቸው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ተዘጋጅተዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ሌሄርማይር ከሌሎች አንጻር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙትን የመልካም እረኛ እህቶች ማሕበር በኮባልት መዕድን ማውጫ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ህጻናትን ከሰባት በላይ ትምህርት ቤቶች መስርተው እንዲማሩ ማድረጋቸውን  እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። በድጋሚ ለቤተሰቦቻቸው አማራጭ የገቢ ምንጮችን ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል “የክርስቲያን ማህበረሰቦች ይህንን ለማድረግ በጣም ንቁ ናቸው” ብለዋል ።

የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና የአለምአቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን መከታተል

አቶ ሌሄርማይር የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና ባርነት ለመግታት ከብዝበዛው ተጠቃሚ ጎን መረባረብ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ባደጉት ሀገራት ህብረተሰቡ ችግሩን እንዲገነዘብ ሲያደርጉ፡ “ቲሸርት በ3 ዩሮ ስንገዛ ከየት እንደመጣ እራሳችንን እንጠይቅ” ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ላይ በመሬት ላይ ተጨባጭ ሥራ የሚሰሩ የክርስቲያን ድርጅቶችን ጨምሮ በአለምአቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን ለመለየት እና ለመቀነስ እንዲረዱ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል።

 

18 April 2024, 22:24